ሁመራ፦ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም በአማራ ክልል ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በማይካድራ ከተማ ጥቅምት 30/ 2013 ዓ.ም በዘረኝነት በአፍቅሮተ ንዋይና አፍቅሮተ ስልጣን የተለከፉ የህውሀት ቡድን አባላት ጭካኔ በይፋ የታየበት ወቅት ነው ።
ለዓመታት በማስመሰያ ጭንብል ተሸፍኖ የቆየው የህውሃት እውነተኛ ባህሪ የዛሬ አራት ዓመት በጥቅምት ወር በማይካድራ ከተማ አደባባይ ላይ ወጣ።ሀውዜን ላይ የታየው የግፍ ጭፍጨፋ ሲያወግዝ የቆየው ሌላ ሀውዜን ማይካድራ ከተማ ውስጥ በይፋ ታየ።
ጥቅምት 30 የግፍ ደም የፈሰሰባት፣ የመከራ ድምጽ የተሰማባት፣ እናቶች አብዝተው ያለቀሱባት፣ ሕጻናት በዋይታ የተመሉባት፣ የጭካኔ ጥግ የታየባት፣ ያጎረሱ እጆች የተነከሱባት፣ ያለበሱ የተሰቃዩባት ምድር ማይካድራ 1ሺህ 563 ንፁሀን ተሰውባት፡፡
ደጎቹ ያለ ሐጥያታቸው ተቀጡባት፣ እንግዳ ተቀባዮቹ ያለ በደላቸው የግፍ ጽዋ ተቀበሉባት፤ ተበዳይ ኾነው ሳለ እንደ በዳይ የተቆጠሩባት፣ ደግ አድራጊዎች ኾነው ሳለ እንደ ክፉ አድራጊ የታዩባት ቀን ጥቅምት 30 ፡፡ እናት የአብራኳን ክፋዮች አጣች፤ ጧሪና ቀባሪዋን በግፍ ተነጠቀች፤ ልጆች ወላጆቻቸውን ተነጠቁ፤ በሞት ጥላ ሥር ተከበው ተጨነቁ፤ ምድሯ በደም ጎርፍ ፣ተጥለቀለቀች ፣በጣረሞት ድምጽ ተመላች፣ በሬሳ ብዛት ተጨናነቀች፣ አዳኝ እና ከልካይ በሌላቸው ንጹሐን ዋይታ ተናወጸች፣ጎዳናዎች በደም ታጠቡ፣ ለአስከሬን ማሳረፊያ ጠበቡ፡፡
ዘር ጠፋባት፤ ማንነት እየተጠየቀ የግፍ ግፍ ተፈጸመባት፤ የጭካኔ የመጨረሻው ጥግ ታየባት፡፡ ከሞታቸው አሟሟታቸው ያስጨንቃል፤ ከሞታቸው አገዳደላቸው ያሰቅቃል፡፡ ለምን ቢሊ አሰቃይተው ገድለዋቸዋል፤ ስቃያቸውን አብዝተው ነብሳቸውን ከስጋቸው ተለይተዋልና፡፡
“ሳምሪ” የተሰኜው ገዳይ ሰራዊት በሰላማዊ እናቶች፣አባቶች፣ወጣቶችና ህጻናት ላይ ብሄር ተኮር የግፍ ጭፍጨፋ አደረገ።በበርሀ ሲሰሩ የነበሩ የቀን ሰራተኞችን ሳይቀር ሰብስቦ በገጀራ አረደ።እናቶችና ህጻናት እያዩ አባቶቻቸውን በጥይት ግንባርና ደረታቸውን እየመታ ጣለ። በመቶዎች የሚቆጠሩ ልጆች ያለ ውላጅ ፤ ሴቶቹ ደግሞ ያለ ባል ቀሩ ። እናቶችም የልጆቻቸውን አስከሬን እንደ በግ ታርደው ወድቀው እያዩ የደም እንባ አፈሰሱ ።
ወያኔ ከራሱ አባላት ውጭ ሌላ ሰው ኢትዮጲያ ውስጥ መኖሩ አይታየው ፤በህውሃት ጎጠኞች እሳቤ መሰረት የአማራ ክልል ተወላጅ ማህበረሰብ ሰዎች አይደሉም፤ስለሆነም ያለ አንዳች ምክንያት በግፍ ተገደሉ።
ጥቅምር 30 /2013 ሰማዕታትን የምናነሳቸው በጥልቅ ሀዘን ብቻ ሳይሆን በቁጭትና እልህም ጭምር ነው።ወገኖቻችን እንደሰው ሳይቆጠሩ ተገደሉ፤ለኛ ግን ወገኖቻችን ሰው ብቻ ሳይሆኑ ሰማዕትም ጭምር ስለሆኑብን ሙት አመታቸውን በማክበር በየአመቱ ስንዘክራቸው እንኖራለን።
ሰማዕታት ወገኖቻችን የህይወት ዋጋ ከፍለው ዘረኝነት የማስወገድ ሸክም እኛ ላይ ጥለዋል።
ዘላለማዊ ክብር ለሰማእቶቻችን!`
Wolkayt tegedie setit humera zone communication በወቅቱ ቢልክልንም ወዲያ ባለማተማችን ይቅርታ እንጠይቃለን!