የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ያለአግባብ የመውጫ ቪዛ ክፍያ እንደጫነባቸው ጠቅሰው በኢትዮጵያ የሚኖሩ ኤርትራዊያን አቤቱታ አሰሙ። ተቋሙ በበኩሉ ዋናው መፍትሄ ህጋዊ ሆኖ መኖር ስለሆነ አሁንም ያልተመዘገቡ ካሉ ይመዝገቡ። ቀኑ እየጨመረ ሲሄድ ክፍያውም ይጨምራል ሲሉ አሰራሩ ማንንም ሳይለይ ተግባራዊ ይደረጋል ሲሉ መልስ ሰጥተዋል።
ስማቸው እንዳይገለጽ ጠይቀውና በገሃድ ስማቸውን ተናግረው ለአሜሪካ ሬዲዮ አቤቱታቸውን ያሰሙ የኤርትራ ተወላጆች እንዳሉት ለመውጫ ቪዛ እስከ አራት ሺህ ዶላር ይጠየቃሉ። ሪፖርቱን ያቀረበው ቪኦኤም ከ1400 እስከ 3445 ዶላር የተከፈለባቸውን ማስረጃዎች ማየቱን አመልክቷል።
የኢሚግሬሽና ዜግነት አገልግሎት አግባብነት ያላቸው ኃላፊ አቶ አዳነ ደበበ ክፍያው መተየቁን አላስተባበሉም። ክፍያው በህገወጥ መንገድ ሳይመዘገቡና ፈቃድ ሳያገኙ በድብቅ ለቆዩበት የተጣለ፣ ወጥነት ያለው አሰራር የተከተለ መሆኑን ነው የተናገሩት።
ቅሬታ ካሰሙት መካከል በሱዳን ሲኖር የነበረና በረብሻው ምክንያት በመተማ በኩል አዲስ አበባ የገባ ከኤርትራ ኤምባሲ ፓስፖርት አሳድሶ ወደ አንጎላ ለማቅናት የመውጫ ቪዛ ሲጠይቅ አራት ሺህ ዶላር መተየቁን አስታውቋል። ቢስተካከል በሚል እሳቤ ትንሽ ቆይቶ በድጋሚ ሲጠይቅ፣ 4800 ዶላር ክፍለ መባሉን፣ ከዛም ችግሩን አሰምቶ በመጨረሻ 3800 ዶላር ከፍሎ ቪዛውን ማግኘቱን ተናግሯል።
አቶ አዳነ ለዚህና መስለ ቅሬታዎች ሲመልሱ የተጋነነ ክፍያ እንደማይተየቅ ገልጸው ” አንድ፣ ሁለት፣ ሶስት ወይም አምስት ዓመት በህገወጥነት የኖረ እኩል አይከፍሉም። ክፍያው የመውጫ ቪዛ ሳይሆን ሳይመዘገቡ በህገወጥነት የኖሩበት ነው” ሲሉ ለሁሉም አገር የውጭ አገር ዜጎች ያለ አንዳች ልዩነት ተግብራዊ እንደሚደረግ አመልክተዋል።
ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡ ኤርትራውያን፣ ወደ ሌሎች ሀገራት ለመሄድ ሲፈልጉ፣ የመውጫ ቪዛ ለማስመታት እስከ 4 ሺህ ዶላር ድረስ እንደሚጠየቁ ገልጸዋል ላቀረቡት ቅሬታ ” መፍትሄው ህጋዊ ሆኖ ተመዝግቦ በመኖሪያ ፈቃድ መኖር ብቻ” እንደሆነ አቶ አዳነ ደግመው ተናግረዋል። የኢሚግሬሽና ዜግነት አገልግሎት በተቋም ደረጃ በኢትዮጵያ ሳይመዘገቡ በህገወጥ መንገድ የሚኖሩ የውጭ አገር ዜጎች በአካል ቀርበው ምዝገባ እንዲፈጽሙ በተደጋጋሚ ጥሪ መቅረቡን ሲያስታውቅ መረጃ እንዳለው ማስታወቁ አይዘነጋም።
የክፍያው ምክንያት ግልፅ እንዳልኾነና ወጥነትም እንደሌለው የተናገሩት ኤርትራውያኑ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የክፍያውን መጠን ዳግም እንዲመለከተው ተማጽነዋል። የተጠየቁትን ክፍያ ከፈጸሙ በሁዋላ ፓስፖርታቸው ላይ ” ከኢትዮጵያ ተባሯል” የሚል ምልክት ጨምረው በማተም በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ እንደሚሰጡዋቸው ገልጸው አሰራሩን ኮንነዋል። ከአምስት ዓመት በፊት ኢትዮጵያ መመለስ እንደማይችል ተነገሮት ፓስፖርቱ የተጠው ቅሬታ አቅራቢም ይን ሲናገር ተሰምቷል።
አቶ አዳነ ሁሉም ሳይሆኑ በጣት የሚቆጠሩ ጥቂት ግለሰቦች ላይ ይህ መደረጉን ገልጸው፣ “እንደ ወንጀሉ መጠን የሚደረግ ነው” ብለዋል። “ወንጀል” ያሉትን አላብራሩም። ቪኦኤም አልጠየቃቸውም።
በአገባቡ እንደማይስተናገዱና አላስፈላጊ የሆኑ ምላሾች እንደሚሰጣቸው ጠቅሰው ላቀረቡት ቅሬታ፣ ማንንም ሳንለይ ለሁሉም ህገወጦች እንደ ጊዜው ርዝማኔ የተጣለ ቅጣት በከፍተኛ መስተንግዶ እንደሚያስከፍሉ፣ ችግር ላለባቸውም ትብብር እያደረጉ እንደሆነ አቶ አዳነ አመልክተዋል። ከተቋሙ ባገኘነው መረጃ መሰረት የበርክታ አፍሪካ አገራት ህገወጦች በተመሳሳይ፣ ከዛም በላይ ቅጣት ይጣላል።
“በየትኛው የዓለም አገር ነው ህገወጥ ሆነው የሌላ አገር ዜጎች እየኖሩ ህጋዊ ጥያቄ የሚጠይቁት?” ተቋሙ ውስጥ የሚሰሩ የየህግ ባለሙያ “ህገወጥነት በየትኛውም ዓለም ያስቀጣል። ኢትዮጵያም ይህ አድርጋለች። እስከማውቀው ድረስ በተደጋጋሚ ጥሪ ቀርቧል። ገንዘቡን ለመክፈል ያለውን ችግር እረዳለሁ። ነገር ግን ህግን ማክበር ግድ ነው። ጉዳዩ በክፋት መታየት የለበትም። ህጋዊ የሆኑቱ በኢትዮጵያ ብር ይገበያያሉ፣ የከራያሉ። ይነገዳሉ። ይከፍላሉ። ክፍያ ይቀበላሉ። በዚህ ደረጃ በነሳነት እንደማንኛውም ዜጋ አገልግሎት ያለ ልዩነት የሚያገኙ ወገኖቻችን ብዛትና ለምን ተቀታን የሚሉት ሲወዳደሩ ጭራሽ ሚዛን ፊት አይቀርቡም” ብለውናል።
በቴሌግራም የከተሉን https://t.me/+f_kxmaPjD-9jYTdk