ኢትዮጵያ አልሸባብ ብሄራዊ ስጋት እንዳይሆንባት በየትኛውም ሁኔታ የማዳከምና የማሽመድመድ ስራዋን አጠናክራ እንደምትቀጥል ይፋ አደረገች። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ዛሬ በሰጡት መግለጫ “ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የማይነጣጠሉ ሕዝቦች እንደመሆናቸው ጊዜያዊ ችግሮችን የመባባስ ፍላጎት የለንም” ብለዋል።
አምባሳደሩ “አልሻባብ ብሔራዊ ደኅንነታችን ላይ ስጋት የማይሆንበት ደረጃ እስኪደርስ እንዲሁም እስካሁን የተመዘገቡ ድሎች እንዳይቀለበሱ አልሻባብን ለማዳከም የተሰሩ ወሳኝ ሥራዎች በማንኛውም መንገድ ይቀጥላሉ” ብለዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ኢትዮጵያ የሶማሊያውን ታጣቂ ቡድን አልሻባብን ለማሽመድመድ ለዘመናት ያደረገችው ዘመቻ እንደሚቀጥል ያስታውቁት ዛሬ በሰጡት መግለጫ ነው።
የሶማሊያ መከላከያ ሚኒስትር የኢትዮጵያ ሠራዊት በአዲሱ የአፍሪካ ሕብረት የድጋፍ እና የማረጋጋት ተልዕኮ ውጪ መሆኑን ባለፈው ሳምንት በይፋ ማስታወቃቸውን በተመለከተ የኢትዮጵያን አቋም እንዲያብራሩ በመግለጫው ወቅት ጥያቄ ቀርቦ ነበር። አምባሳደር ነብያት የሶማሊያ ባለስልጣናት ለተናገሩት በቀጥታ መልስ አልሰጡም። የዲፕሎማሲ ቋንቋ ተጠቅመው “አልሸባባን እናዳክማለ፣ የኢትዮጵያና የሶማሊያ ሕዝብ የማይነጣጠሉ በመሆናቸው ጊዜያዊ ችግሮችን የመባባስ ፍላጎት የለንም” የሚል ምላሽ ነው የሰጡት።
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ግንኙነታቸው የሻከረው ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ጋር የባህር በር ለማግኘት የመግባቢያ ሰንድ መፈረሙን ተከትሎ እንደሆነ ይታወሳል። ይህንኑ አለመግባባት ተከትሎ ግብጽና ኤርትራ በቀጥታ ህብረት ፈጥረው ኢትዮጵያ ላይ ያላቸውን የቆየ ፍላጎት ለማሳካት በገሃድ ሲንቀሳቀሱ መሰንበታቸውና ወታደራዊ ስምምነት ማድረጋቸው አይዘነጋም።
በቱርክ አሸማጋይነት ያልተሳካው የሁለቱ አገራት ልዩነት፣ ከጀርባ ባሉት አገራት ገፋፊነት የኢትዮጵያ ወታደሮች አዲስ በሚዋቀረው የአፍሪካ ሕብረት የድጋፍ እና የማረጋጋት ተልዕኮ ውጪ መሆናቸውን በይፋ እስከማስታወቅ አድርሷል። ለዓመታት የልጆቿን ድምና አጥንት ስትከሰክስ የኖረችው ኢትዮጵያ ከጥር በሁዋላ ከቀድሞ ተግባሯ እንድትሰናበት እንደሚደረግ በይፋ ፉከራ መሰማቱን ተከትሎ ምላሽ የሰጡት ቃል አቀባዩ፣ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ስጋት ከማስቀድመና አልሸባብ እንዳያንሰራራ በማንኛውም ሁኔታ የማዳከም ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከመግለጽ ውጪ ያሉት ነገር የለም። የሁለቱ አገራት ህዝብ እጅግ አንድ በመሆናቸው ችግር የሚያባብስ አካሄድ መከተል እንደማያስፈልግም አመልክተዋል።
በቅርቡ በፓርላማ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የሶማሌ ባለስልጣና ወደ ቀልባቸው እንዲመለሱ በትእግስ መተበቅ አግባብ እንደሆነ መናጋራቸው አይዘነጋም። በዚሁ ሰፊ ማብራሪያቸው ኢትዮጵያን መንካትም ሆነ ብሄራዊ ጥቅሟ ላይ እንቅፋት ለሚሆኑ ግን በአግባቡ ምላሽ እንደሚሰጥ አስታውቀው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የባህር በር ፍላጎቷን ፍጹም ሰላማዊ በሆነ የሰጥቶ መቀበል መርህ ከማሳካት ውጭ አንዳችም ዓይነት የጦርነት ፍላጎት እንደሌላት መግለጻቸው አይዘነጋም።
አምባሳደር ነቢያት መግለጫቸው ኢትዮጵያ ለቀጣናው ያደረገችውን አስተዋጽኦን አስረድተዋል። አሸባሪው አልሻባብ በቀጣናው የጋረጠውን ስጋት በመግታት ረገድ ኢትዮጵያ እየተጫወተችው ያለው ቁልፍ ሚናን ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሚያውቀው እና የሚገነዘበው እንደሆነም አመልክተዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው “ኢትዮጵያ አልሸባብን ማደከሟን ግን ትቀጥልበታለች” ማለታቸውን ተከትሎ አስተያየት የሰጡ “ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲያዊ ቋንቋ ከሶማሊያ እንደማትወጣ እንቅጩን ተናግራለች” ብለዋል።
ሊጠናቀቅ ጥቂት ሳምንታት የቀሩትን የአፍሪካ ሕብረት የሽግግር ተልዕኮ በሶማሊያ (ATMIS)ን በመተካት በሶማሊያ የሰላም ማስከበር ሚናን ይወጣል ተብሎ የሚጠበቀው የአፍሪካ ሕብረት የድጋፍ እና የማረጋጋት ተልዕኮ የተሳትፎ ጉዳይ ላይ ብያኔ ሰጪው ማን ነው? የሚለው ጥያቄ ቁልፍ ጥያቄ ነው።
ለጀርመን ድምጽ ምላሽ የሰጡ የዓለም አቀፍ ሕግ እና የዲፕሎማሲ ጉዳዮች አዋቂ “ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ የምንለው፣ የተባበሩት መንግሥታትን የመሰሉ፣ የአፍሪካ ሕብረትን የመሰሉ ተቋማት እንዲሁም አስተዋጽዖ የሚያደርጉ ሀገራት ብያኔ አሰጣጡትላይ ሚና ይኖራቸዋል” ብለዋል። አክለውም “ጠንካራ የመንግሥት ተክለ ቁመና ሲኖር ማንኛውም መንግሥት ይሁንታ የመስጠትም ሆነ የመከልከልም መብት አለው” በማለት መንግስታዊ ቁመና ወሳኝ መሆኑን አመልክተዋል።
“የዚህ መነሻ ምክንያቱም ዓለም አቀፍ ሰላም አስከባሪ ኃይል ወደ አንድ ሀገር ሲሰማራ ጉዳዩ ከማዕከላዊ መንግሥት አቅም በላይ ነው የሚል መደምደሚያና ግንዛቤን ታሳቢ ተድርጎ ነው ” ያሉት አስተያየት ሰጪ ሶማሊያ በአንድ በኩል ኢትዮጵያን አላሳትፍም ብትችልም፣ በተግባር ግን ይህንን ማለት የሰላም አስከባሪ ኃይሉን ሙሉ ያደርገዋል ዎይ?” የሚል ጥያቄ እንደሚያስነሳ ገልጸዋል። በቀላል አገላለጽ አስተያየት ሰጪው ደካማ መንግስት የመወሰን አቅም እንደሌለው ነው ያመለከቱት።
ዋና ከተማዋን እንኳን በወጉ ማስተዳደር የማትችለው ሶማሊያ፣ ለቀጣዩ የሰላም ማስከበር ስራ እስካሁን በቂ በጀት እንዳልተገኘላትና በጀቱን ለሚለቁት አገራት ውሳኔ ተገዢ ከመሆን የዘለለ አማራጭ እንደሌላት ቀደም ሲል መገለጹ ይታወሳል። ለዚህ ይመስላል የወቅቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ” መንግስት አክቲቪስት ሲሆን አስቸጋሪ ነው” ሲሉ የሶማሊያን ባለስልጣናት የየቀን ፉከራ የገለጹት።
በስማሊያ እስካሁን ይፋ እንደሆነው ሶስት ግዛቶች ሞቃዲሾ ቁጭ ካለው የሃሰን ሼኽ መንግስት ጋር ግንኙነታቸውን በይፋ ማቋረጣቸው፣ ሶስቱም ግዛቶች ከኢትዮጵያ ጋር መስራት እንደሚፈልጉና የኢትዮጵያ ወታደሮች ለቀው እንዳይወጡ ፋልጎታቸውን ማሳየታቸውን ገልሰን መዘገባችን ይታወስል።
በሌላ ዜና ኢትዮጵያ በኮንፈረንስ ዲፕሎማሲ ውጤታማ ሥራ ማከናወኗን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመልክቷል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ በኢትዮጵያ የተካሄዱት ዓለምአቀፍ ጉባኤና ኮንፍረሶች አዲስ አበባ የዲፕሎማሲ መዲናነቷን ያስመሰከረችበት ነው።
በኮንፍረንስ ቱሪዝምና ዲፕሎማሲ ባለፈው ሩብ አመት ከ30 በላይ ዓለምአቀፍ ጉባኤና ኮንፍረሶች በአዲስ አበባ ተካሂደዋል ያሉት ቃል አቀባዩ ከረሀብ ነጻ ዓለም መፍጠር ጉባኤ የካፍ ጉባኤን ጨምሮ ዓለምአቀፍ የሃይማኖቶች አንድነት ጉባኤና ሌሎችም ተካሂደዋል ብለዋል።
የኮንፍረንሶቹ በተሳካ ሁኔታ መካሄድ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ አቅምና ሚና ያሳየ መሆኑን ጠቅሰው አዲስአበባ በኮንፍረስ ቱሪዝምና ዲፕሎማሲን በመሳብ ረገድ አቅሟ እያደገ መምጣቱን ያስመሰከረችበት መሆኑን ገልጸዋል።
አዲስ አበባ ትልልቅ ጉባኤዎችንና ኮንፍረንሶችን በተሻለ መልኩ ማስተናገዷን የቀጠለችበት መሆኑን በመግለጽ የዲፕሎማሲ መዲናነቷንም ያስመሰከረችበት መሆኑዋን አስረድተዋል።
ኮንፍረንሶቹ ከገጽታ ግንባታ የቱሪዝምን ገቢ ከማሳደግ አኳያና የተለያዩ ልምዶችን ለማጋራት ከፍተኛ ሚና እንደነበራቸው ጠቁመዋል።
ጉባኤዎቹ ኢትዮጵያ ዳግም የአፍሪካ ድምጽና ወኪል መሆኑዋን ያስመሰከረችበት ነው ያሉት ቃል አቀባዩ አዲስአበባም በማያወላዳ መልኩ የዲፕሎማሲ መዲና መሆኑዋን ያሳየ ነው ብለዋል።
ከ30 በላይ ዓለም አቀፍ ጉባኤና ኮንፍረሶቹ የተሳተፉ መሪዎችና ተሳታፊዎች የልማት እንቅስቃሴዎችን መጎብኘ።
በተጨማሪም ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው የመጀመሪያው የሩሲያ አፍሪካ አጋርነት ፎረም የሚኒስትሮች ሰብሰባና የኢትዮጵያ ተሳትፎ ኢኮኖሚ ዲፕሎማሲና በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ እንቅስቃሴዎች ላይ ገለጻ አድርገዋል።
በቴሌግራም የከተሉን https://t.me/+f_kxmaPjD-9jYTdk