ከአባይ ወንዝ ግድብ ጋር ተያያዞ ግብጽ የአረብ ሊግን እያስተባበረች ኢትዮጵያ ላይ ተደጋጋሚ ጫና ስትፈጥር፣ ኢትዮጵያ የአረብ ሊግ አባል ልትሆን ይገባ እንደነበር ተደጋጋሚ አሳብ ሲሰነዘር እንደነበር ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድም ይህንኑ አንስተው ዝርዝር ባይናገሩም የአረብ ሊግ ውስጥ በአባልነት መካተት አስፈላጊ መሆኑን ማስታውቃቸው አይዘነጋም።
የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ቀደም ሲል ከአረብ ሊግ ተጠባባቂ ፀሐፊ ጋር ምክክር አድርገው እንደነበር ተጠቅሶ ዛሬ ይፋ የሆነ ዜና እንደሚያስረዳው፣ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለአረብ ሊግ የሚቀርበውን ደብዳቤ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስገብቷል። ከውጭ ጉዳይ ሚንኪስር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ጋርም መክረዋል።
የአርብ ሊግ ተጠባባቂ ጸሐፊ ከእስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮች ጋር ባደረጉት ውይይት “የኢትዮጵያ መንግስት ጥያቄውን በይፋ ካቀረበ ምላሽ እንሰጣለን” ማለታቸውን እስልምና ጠቅላይ ምክር ቤቱን ጠቅሰው ዜናውን ያሰራጩት ሪፖርት አድርገዋል። በዚህ መሰረት ደብዳቤው ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስቴር መቅረቡ ተረጋግጧል።
ደብዳቤውን ያቀረቡት የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዬስ በ17/03/2017 በጽ/ቤታቸው ባደረጉት ምክክር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ ተቀዳሚ ም/ፕሬዝዳንት ሸይኽ አብድልከሪም ሸህ በድረዲን፣ የጠቅላይ ም/ቤቱ ዋና ፀሐፊ ሸህ ሃሚድ ሙሣ እና የጠቅላይ ም/ቤቱ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ የሆኑት ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ተገኝተው እንደነበር ታዝውቋል።
በውይይቱም የተነሱ ዋና ዋና ጉዳዩች ሲጨመቁ
- ኢትዮጵያ የአረብ ሊግ አባል እንድትሆን በጠቅላይ ም/ቤቱ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ከአረብ ሊግ ተጠባባቂ ፀሐፊ ጋር በነበረው ውይይት የኢትዮጵያ መንግስት ጥያቄውን በይፋ ካቀረበ ምላሽ እንደሚሰጡ በገለፁልን መሠረት በጽሑፍ የተዘጋጀውን ደብዳቤ ለክቡር ሚ/ሩ መቅረቡ
- በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋና መ/ቤትና በተለያዩ አገራት በተመደቡ ዲፕሎማቶች ዙሪያ የሙስሊሙ አካታችና አሳታፊነት ምን እንደሚመስል? ለማካተትስ ምን እየተሰራ ነው? የሚለው ጥያቄ
- በፌዴራል መንግስት አዋጅ ቁጥር 1207/2012 ለጠቅላይ ም/ቤቱ በተሰጠው ስልጣን መሠረት በውጭ አገር ቅርንጫፍ ቢሮዎችን የመክፈት እና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውዮን ሙስሊሞች የሚያቋቁሙት ጽ/ቤቶች ለመክፈት እንዲያስችላቸው በውጭ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስፈላጊውን እገዛና ትብብር እንዲያደርግላቸው።
- በሳዑዲ አረቢያ ጅዳ ከተማ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ውስጥ የሐጅና ዑምራ ጉዳይ የሚያስተባብርና የሚከታተል ዲፕሎማት እንዲሾምልን ከዚህ በፊት ለነበሩ 2 ሚኒስትሮች ጥያቄው ቀርቦ ምላሽ ያላገኘ ሲሆን አሁን ካስፈላጊነቱ እንፃር ተገንዝበው ተወካይ እንዲመደብ የሚጠይቅ።
- ከላይ የተጠቀሱትን ጥያቄዎች አፈፃፀም ላይ ሁሌም ስለምንቸገር ከሚ/ር መ/ቤቱና ከጠቅላይ ም/ቤቱ ጋር በጋራ የሚሰሩ ተወካዮች እንዲመደቡ በየእለቱ በመገናኘት እንዲያስፈጽሙ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል እና በጠቅላይ ም/ቤቱ በኩል ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ተመድበው ስራዎች እንዲያከናውኑ ስምምነት ላይ መደረሱም ነው የተገለፀው
በአጠቃላይ በነበረው ውይይት አዎንታዊ ምላሽ የተሰጠ መሆኑን ጠቁመው፣ ውጤቱን በቀጣይ ይፋ መሆን ሲገባው ለህዝብ እንደሚያሳውቁ አመልክተዋል። የኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሳይሆን ጥያቄውን ማቅረብና የአባልነት ምላሹንም መቀበል የመንግስት ስራ እንደሆነ ያነጋገርናቸው የእስልምና ጠቅላይ ጽህፈት ቤት አንድ ኃላፊ ነግረውናል።
” እንቅስቃሴው የአገላለጽ ችግር አለበት” ያሉን እነዚህ ወገኖች “የኢትዮጵያ እስልምና ምክር ቤት ይህን ጉዳይ አጀንዳ አድርጎና ከመንግስት ጋር ተናቦ የሚሰራው አገሩ አስቦና አልሞ ነው” ብለዋል። አያዝወም በሊጉ ተቀባይነት ከተገኘ የምትወከለው ኢትዮጵያ፣ በስብሰባ የምትሳተፈው ኢትዮጵያ እንጂ ምክር ቤቱ እንዳልሆነ ግልጽ ስለህነ ዜናውን ወደ አንድ በኩል መሳብ ተገቢ እንዳልሆነና ሆን ተብሎ ብዥታ ለመፍጠር የሚደረግ እንደሆነ ተናግረዋል።
የአረብ ኦሊግ አገራት እንጂ የኃይማኖት ተቋማት ስለሌሉበት ጥያቄውን ኢትዮጵያ በኦፊሳል እንድታቀርብ ራሱ አረብ ሊግ ምክር የሰጠው በዚሁ መነሻ መሆኑን አስተያየት እንዲሰጡን የጠየቅናቸው ነግረውናል። አያዘውም ይህ “የተመረጠ አካሄድ ነዎው። ውጤቱ ሲታይ እንዴት ታስቦ እነተፈጸመ ህዝብ እንዲያውቅ ይደረጋል” ብለዋል።
በአሁኑ ሰዓት ያሉት የሊጉ አባላት Algeria, Bahrain, Comoros, Djibouti, Egypt, Iraq, Jordan, Kuwait, Lebanon, Libya, Mauritania, Morocco, Oman, Palestine, Qatar, Saudi Arabia, Somalia, Sudan, Syria, Tunisia, the United Arab Emirates, and Yemen.
ኢትዮጵያ ከሞሮኮ፣ አልጀሪያ፣ አረብ ኤምሬትስ፣ ኮሞሮስ፣ ኢራቅ፣ ሊቢያ፣ ጆርዳን፣ ኪዌት ከመሳሰሉት አገራት ጋር ወዳጅ መሆኗ አይዘነጋም።