ሃሰን ሼክ መሀመድ የሚመሯት ሞቃዲሾ አዲስ ዜና አሰምታለች። ኢትዮጵያን ለሶማሊያ ስጋትና ተላት አድርጎ የሚያሳይ የታሪክና የኢትዮጵያን ምስራቅ ክልልና ሶምሌ ክልልን ወደ ሶማሊያ የሚያካትት የጂኦግራፊ መጽሃፍ በማሳተም ወጣቶች እንዲማሩበት አድርገዋል።
ሶማሊያ ኢትዮጵያን የሶማሊያ የሕልውና ሥጋት ተደረጋ እንድትታይና ይህንኑ እየተማረ የሚያድግ ትውልድ ለመቅረጽ የመማሪያ መጽሃፍት አዘጋጅታ ማስተማር መጀመሯን የዘገበው ኢንሳይድ አፍሪካ ሲሆን ዜናውን በተንቀሳቃሽ ቪዲዮ አስደግፎ በኤክስ ገጹ ይፋ አግርጓል።

ላለፉት ሃያ ዓመታት ሶማሊያ እንዳትበተን ታሪክ የማይዘነጋውን ውለታ ላስቀመጠችና አሁንም ይህንኑ ተግብሯን እያከናውነች የምትገኘውን ኢትዮጵያ በህልውና ስጋት ፈርጆ ህጻናትን ለማስተማር አዲስ መጽሃፍ መታተሙ አነጋጋሪ ሆኗል።
በሶማሊያ የፈሰሰው የኢትዮጵያዊያን ደም፣ የተጎዳው አካላቸውና በበረሃ በስቃይ ውስጥ ሆነው የከፈሉት ዋጋ በአብዛኛው የሶማሊያ ህዝብና ግዛቶች ዘንዳ ክብር እየተሰጠው ቢሆንም፣ አንድ ቀበሌ የሚመሩት ሃሰን ሼክ በዚ ደረጃ ማበዳቸው መቸረጫው ምን ሊሆን ይችላል የሚል ጥያቄም እያስነሳ ነው።
“መንግስት አክቲቪስት ከሆነ ችግር ነው” ሲሎኡ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ከወራት በፊት እንዳስታወቁት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በቅርቡ በፓርላማ ይፋ እንዳደረጉት “ወደ ቀልቡ እስኪመለስ” የተባለው የሞቃዲሾ መንግስት እንኳን ቀልቡን ሊሰበስብ ሌላ ዘመቻ ጀምሯል። ጉዳዩን አስመልክቶ ከመንግስትም ሆነ ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ምንም የተባለ ነገር የለም።
“በሞቃዲሾ የሚገኘው የሶማሊያ መንግስት ኢትዮጵያ የህልውና ስጋት እና የሶማሊያ ታሪካዊ ጠላት እንደሆነች እንዲያምኑ በትምህርት ቤት ህጻናት ላይ ማስረፅ ጀምሯል” ያለው ዜናው በምስል ባሰራጨው መረጃ መምህሩ በማመላከቻ ዱላ እየጠቆመ ቃላቶቹን ሲያስቆጥር በልህና በወኔ ነው።
ይህንን አዲስ ትረካ ለመደገፍ የሞቃዲሹ አስተዳደር ለመካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የታሪክ እና የጂኦግራፊ መማሪያ መፃህፍትን (Rewrite ) አሻሽሎ ዳግም በአፍሪካ ደረጃ ማቅረቡን አረጋግጧል።
“ተሻሻሉ” የተባሉት የታሪክ መማሪያ መጽሃፍት፣ ወጣት የሶማሌ ተማሪዎች በተለይ በኢትዮጵያ ላይ ጥላቻን እንዲያዳብሩ የሚያስችሉ ክፍሎች አሉበት። ጥላቻን እንዲሞሉና በጥላቻ እንዲነደፉ የሚያስችሉ ጉዳዮች በተለይ የተካተቱባቸው አዳዲስ መጽሃፍት ተማሪዎች ትምህርታቸውን እየተከታተሉበት ነው።
በሌላም በኩል የጂኦግራፊ መማሪያ መፃህፍቱ በሶማሊያ ትምህርት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በሶማሊያ ድንበሮች ውስጥ እንዲካተት አድርጓል። ይህም የሶማሌ ብሄርተኞች የይገባኛል ጥያቄን የ”ታላቋን ሶማሊያ ስሜት የለሽ ጽንሰ ሀሳብ በትክክል ያሳያሉ” ሲል ኢንሳይድ አፍሪካ ዘግቧል።
“ይህ አይን ያወጣ ሙከራ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በሱማሌ የይገባኛል ጥያቄ ሊነሳ ይገባል የሚለውን አስተሳሰብ የሚያበረታታ ሲሆን አስፈላጊ ከሆነም በሃይል አዲሱን ትውልድ ለማነሳሳት ያለመ ነው” ነው ሲል ዜናው የእሳቤውን ዓላማ አስፍሯል።
በቪዲዮው ላይ የሚታየው አንድ መምህር እነዚህን የተሻሻሉ የመማሪያ መጽሃፍትን በመጠቀም በሞቃዲሾ አንድ ትምህርት ቤት ውስጥ ታዳጊ ህጻናት ሲያስተምር ያሳያል። ይህም አስደንጋጭ ድርሰት የሚያስተምረው መምህር ስሜቱና እንቅስቃሴው የታዳጊዎቹን ፍላጎት ለማነሳሳት ኃይልና ወኔ የተሞላው እንደሆነ ከቪዲዮው ለመረዳት ተችሏል።
በቴሌግራም ተከታተሉን https://t.me/+f_kxmaPjD-9jYTdk