የሶማሊያው የመከላከያ ሚኒስትር የሚል ማዕረግ አላቸው። ሰባ ከመቶ አገራቸውን ብቻዋን ኢትዮጵያ የምትጠብቅላቸው እንህ የመከላከያ ሚኒስትር ተጠቅሰው በኤፒና በቢቢሲ በተላለፈው ዜና “እስካሁን እንደምናውቀው በአዲሱ [የአፍሪካ ኅብረት] ተልዕኮ ውስጥ የማትሳተፈው አገር ኢትዮጵያ ብቻ ናት” ማለታቸው ተስምቷል።
ሞቃዲሾ ቤተመግስቱ አጥር ጎን ባለው የቴሌቪዥን ጣቢያ ቃለ ምልልስ በማድረግ ኢትዮጵያ በቀታዩ የሰማ ማስከበር ስራ ተሳታፊ እንደማትሆን ያመለክቱት የሞቃዲሾና አካባቢዋ የመከላከያ ሚኒስትር፣ ይህ ሲሉ ጎን ለጎን “ኢትዮጵያን” ያሉ የተለያዩ ግዛቶች በይፋ ከሃሰን ሼኽ መንግስት ራሳቸውን ማግለላቸውን አስታውቀዋል።
“በቀጣዩ የሶማሊያ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ የሚሳተፉ ወታደሮች፣ የሶማሊያን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ከሚያከብሩ አገሮች ብቻ እንደሚውጣጡ የአፍሪካ ኅብረት ወሰነ” ሲል ሪፖርተር የውሳኔውን መግለጫ ሳያያዝ እሁድ ዕለት በግንባር ዜናው ላይ መዘገቡ ይታወሳል። የአፍሪካ ህብረት የሰላም ካውንስል የድረ ገጽ ይህ እስከተጻፈ ድረስ በገሃድ ያሰፈረው መረጃ የለም። ምን አልባትም ለሪፖርተር በተለይ ልኮት እንደሆነም ዜናው አልገለጸም። በተመሳሳይ ሶማሊያ ከአዲሱ ዓመት ጀምሮ ኢትዮጵያን እንደማትፈልግ ማስታወቋን ጫፍ እየፈለጉ የሚዘግቡ ሚዲያዎችም ይህ እስከተጻፈ ድረስ ምንም አላሉም።
ከላይ የተጠቀሱት የሶማሊያ መከላከያ ሚኒስትር ኤርትራ ያስለጠነችላቸውን ታጣቂ ተማምነው ይሁን በሌላ ኃይል ትከሻ እምነት አሳድረው በይፋ ባይገለጽም የሰላም አስከባሪ ኃይሎች ቁጥር እንደሚቀንስና በውስን አካባቢዎች ብቻ እንደሚሰፍሩም አሳስበዋል። ለጊዜው ኢትዮጵያ በቀጣይ የማትካተት መሆኗን ሲያስታውቁ ስም ሳይተቅሱ አዳዲስ አገራት እንደሚጨመሩ አመልክተዋል። ኤርትራና ግብጽን ስለመሆኑ ግልስ ቢሆንም የኢትዮሪቪው የመረጃ ምንጮች ፕሬዚዳንት ኢሳያስ የወታደር እጥረት እንዳለባቸውና ኢትዮጵያን በሚተካ ደረጃ ወታደር ለማዋጣት እንደማይችሉ፣ ይልቁኑም የወታደር እጥረት እንዳለባቸው፣ እስከ ስላሳ ዓመት ያሉ ሳይቀሩ በተጠንቀቅ መሆናቸውን ገልሰዋል።
ይህ በንዲህ እንዳለ ነው ሶማሊያ ከውስጥ መቀደዷ የተሰማው። ቀድሞም የመለያየት ዜና ቢኖርም አሁን ላይ ሚናቸውን ለይተው “ኢትዮጵያን” በሚል ውግንናቸውን ያሳዩ ግዛቶች ሶስት ደርሰዋል።
ጋሮዌይ እንደዘገበው የደቡብ ምዕራብ ሶማሊያ ግዛት ህዝብና መንግስት ከኢትዮጵያ ጎን መሆናቸውን በድጋፉ ሰልፍ አረጋግጠዋል። ይህን ያደረጉት ለሁለተኛ ጊዜ ነው። በግልጽ የኢትዮጵያ ጦር ጥሏቸው እንዳይወታም ተይቀዋል። የግዛቷ ፕሬዝዳንት አሲስ ላፍታግሪን “ኢትዮጵያን ብትነኩ ለአፍታም አንታገስም። ከእኛ ጋር ዋጋን የከፈለው የኢትዮጵያ ሰራዊት ነው” በሚል በይፋ አቋማቸውን አስታውቀዋል። በምንም ዓይነት የግብጽ ጦር የኢትዮጵያን ጦር እንደማይተካ በማስጠንቀቂያ ጭምር አሳስበዋል። ኢትዮጵያዊያን ነን የሚሉ ፖለቲካቸውን አምታተውት በአሜሪካ ሰልፍ ሲያደርጉ የሞቃዲሾን ባንዲራ ይዘው ኢትዮጵያ ላይ ዘምተዋል። በትግራይ የአገር መከላከያ ሃያ ሁለት ዓመት ጉድጓድ ውስጥ ሆኖ አገር ሲጠብቅ ከጀርባው ተመቷል። በተቃራኒ የሶማሊያ ህዝብ ለአገር መከላከያ ያለውን ክብር በዚህ ደረጃ መግለጹ በርካቶችን አስደንቋል።
በሌላ መልኩ የፑንትላንድ ህዝብና መንግስት ከኢትዮጵያ ጎን ቆመዋል። የግዛቱ ፕሬዝዳንት አቡድላሂ ደኔ ከብሔራዊ ምክክር ካውንስሉ ራሳቸውን ያገለሉ ሲሆን፣ ሀሰን ሼክ ከሚመሩት የሶማሊያ ፌድራል መንግስት “እራሴን አግልያለሁ” ብለዋል።
ሦስተኛዋ የሶማሊያ ግዛት ጁባላንድ ስትሆን፣ የጁባላንድ ግዛት ፕሬዝዳንት ልክ እንደፑንትላንድ ሁሉ ከሶማሊያ ፌደራል መንግስት ጋር ያለውን ግንኙነት ሙሉ ለሙሉ ያቋረጠ ሲሆን፣ በዛሬው ቀን ሀሰን ሸክ መሀመድ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት (ENDF) እና በኬንያ መከላከያ ሃይል (KDF) ለሚመራው በቀጠና ስድስት ለሰፈረው የ ATMIS ጦር የጁባላንድ ኤርፖርትን እንዲቆታጠሩ ትዕዛዝ ቢሰጡም ጦሩ “በሶማሊያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት ከኃላፊነታችን ውጨ ነው” የሚል ምላሽ እንደሰጡዋቸው ዘገባዎች አመልክተዋል።
ከሀሰን ሸክ ጋር በመሆን የቀድሞው የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ፎርማጆን ያሰናበቱት የጁባላንድ ፕሬዝዳንት አህመድ ማዶቤ “ሀሰን ሸክን ሳላሰናበት አልተኛም” ሲሉ መገዘታቸውን ከክልሉ የሚወጡ መረጃዎች ያስረዳሉ።
የሶማሊያ ጠቅላይ ሚንስትር ሀምዛ ባሬ፣ ሃሰን ሼኽ በግል ስሜት እየጋለበ ሶማሊያን ወደ ገደል ሲከታት ተባባሪ አልሆንም” በማለት የመልቀቂያ ደብዳቤ አስገብተው ወደ ጁባላንድ (ኪስማዩ) መመለሳቸው ተሰምቷል። ፕሬዚዳንቱ ሀሰን ሼኽ “የስልጣን መልቀቂያህን አልተቀበልኩትም” የሚል ምላሽ ቢሰጠውም ሀምዛ ባሬ በበኩላቸው “ከጎሳህ ውስጥ አንዱን መርጠህ ስጠው” ሲሉ ምላሽ ሰጥቶ ስልኩን ጆሯቸው ላይእንደዘጉባቸው ተቀማጭነታቸው ጁባ የሆኑ ዘግበዋል።