የኢኳቶሪያል ጊኒ ከፍተኛ ባለስልጣን ባልታዛር ኤባንግ ኤንጎንጋ በቢሮ ውስጥ ሳይቀር የፈጸሙዋቸው ከፍተኛ የወሲብ ቅሌት ይፋ መሆኑን ተከትሎ በትግራይ “የኢኳተራልክ ጊኒውን የሚያስንቅ በድብቅ የተቀረጸ የወሲብ ቅሌት አለ” በሚል ማስፈራሪያ ተሰራጨ። ዋና ዒላማ የሆኑት የክልሉ ጊዜያዊ መሪ አቶ ጌታቸው ረዳና እሳቸው ዙሪያ ያሉ ናቸው። ዜናውን የሰሙ ” መረጃው እውነት ከሆነ አሳዛኝ የሚሆነው ለምን እስከዛሬ ተደበቀ? በትግራይ አስገድደው የሚደፍሩ ነጻ ሲለቀቁና እህቶች አደባባይ ወጥተው ፍትህ ሲጠይቁ ለምን ዝም ተባለ?” የሚል የሞራል ጥያቄ አንስቷል።
የኢኳቶሪያል ጊኒ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣን የነበሩት ግለሰብ የወሲብ ድርጊቶች ቅሌት በማኅበራዊ መገናኛ መድረኮች ላይ መሠራጨታቸውን ተከትሎ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ተከትሎ ዛራ ሚዲያ ላይ ስታሊን ገብረስላሴ “ጌታቸው ረዳ የሚመራው የህወሓት አንጃ አባላትን ቅሌት የሚያሳዩ በድብቅ የተቀረፁ በርካታ የወሲብ ፊልሞች ላፕቶፔ ውስጥ አሉኝ ።እነሱን Viral ማድረግ እችላለሁ” በሚል በዛቻና ማስፈራሪያ መልክ በትግርኛ አስጠንቅቋል።
እዚህ ጉዳይ ላይ ከተናገረውና ተቀንጭቦ ከወጣው ቪዲዮ ስራ አስፋው አብርሃም እንደተረጎመውና በግልጽ ለመረዳት በማያስቸግር መልኩ ስታሊን “አደብ ግዙ ።ቅሌታችሁን አደባባይ አውጥተን ልናጋልጣችሁ እንችላለን እኮ” ሲል ተደምጧል። ይህን ያለው በትግራይ ያለውን የፖለቲካና ፍትጊያ ተከትሎ ስለመሆኑ “አደብ ግዙ” ሲል ማስተንቀቁ ያሳያል። ዛቻውም አቶ ጌታቸው ረዳ ላይ ያተኮረ ነው።
አንድ ጊኒያዊ 400 ሴቶችን ሲያማግጥ እንደሚያሳዩት ቪዲዮዎች አይነት በርካታ የእናንተ የወሲብ ፊልሞች ላፕቶፓችን ውስጥ አለ። አርካይቭ በአርካይቭ ነው” ሲል በትግራይ ሰፊ የወሲብ ቅሌት በባለስልጣናት መፈጸሙን የሚያሳይ በድብቅ የተቀረጸ መረጃ እንዳለው ደጋግሞ ስታሊን በቪዲዮው ያወራል።
ስታሊን ይህን አለኝ የሚለውን የጊኒውን ባለስልታን የሚያስንቅ የባለስልጣናት ወሲብ ቅሌት እስካሁን ይፋ ያላደረገው ከጨዋነት የተነሳ ስለመሆኑ ሲናገር “እኛ ሆነን ነው እንጂ “ESAT”ን ብንሆን ኖሮ ቪዲዮዎቹን ለጥፈን አንድ ባንድ እናጋልጣችሁ ነበር” ነው ያለው።
“ጉዳዩ የሞራል ነው። ሞራል ቀን እየተበቀ የሚሰወርና የሚከሰት ነገር ዓይደለም። ስታሊን ይህን ሲል በአደባባይ ሞራል የሌለው፣ ስለሞራል ምንም የማያውቅ፣ አደራውን የማይወጣ፣ ስልጣን ለማግኘት ሲል ባለስልጣናትን በካድሬነት ሲያገለግል የኖረ፣ ለትግራይ ህዝብ በተለይም በዚያ ችግር ወቅት በባለስልጣናት ደረጃ የወሲብ ቅሌት እንደተፈጸመባቸው የሚያረጋግጥ መረጃ ተልኮለት አፍኖ በመያዝ የወንጀል ተባባሪ መሆኑን በራሱ አንደበት ከማረጋገጡ ውጪ መረጃው ሌላ ትልቅ ዜና የለውም” በማለት ሃዘኑን ገልጾ የማነ ኪሮስ የተባለ የስዊዲን ነዋሪ ፋይሉን አያይዞ ልኮልናል።
ስታሊን የት ነበረ? ለምን ዛሬ? ማንን ለማስፈራራት?
በጁን 9 ቀን 2021 ኢትዮሪቪው ከአራት ዓመት በፊት የወጣ የማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ መረጃ ጠቅሰውው ተባባሪ ፕሮፌሰር ግሩም ያሰፈሩትን ሃቅ አትመን ነበር። ይህ ሁሉ ሲሆን ስታሊንና ባልደረቦቹ የት ነበሩ? መረጃው እንደሚለው አስገድዶ መድፈር የጠቅላላ የትግራይ ክልል የሰነበተ ችግር መሆኑን ነው። በትግራይ ክልል 12 በመቶ ሴቶች በየዕለቱ ፆታዊ ጥቃት ያስተናግዳሉ።
ሪፖርቱ እንደሚለው “A 12.7% (117) rape prevalence was reported among women who visited Gynecologic Outpatient Departments of Selected Hospital in Tigray region” በእ.አ.አ በ2015 ብቻ 12.7 በመቶ ወይም 117 ሴቶች የአስገድዶ መድፈር ጥቃት እንደደረሰባቸው በትግራይ ክልል (መቀሌ) የማህፀን ሕክምና የተመላላሽ ሕክምና ክፍልን ከጎበኙ ሴቶች ሪፖርት አድርገው ነበረ። በዚህ ወቅት የህዋሃት ባለስልጣኖች የፌዴራል መንግስትንም የትግራይ ክልልንም በሙሉ የበላይነት በሚመሩበት ወቅት የተከሰተ ቢሆንም ማንም የክልሉ ባለስልጣን ሃላፊነት ያልወሰደባቸው ወንጀሎች ነበሩ። “በዚህ ደረጃ ችግሩ ሲገለጽ ስታሊን ዛሬ በድብቅ ተቀድቶ ‘ደረሰኝ’ ያለውን መረጃ በግሉ ሲዝናናበት ወይስ እያስፈራራ ብር ሲሰራበት ነበር” ሲል መረጃውን የላከልን የሲውዲኒ ነዋሪ ይጠይቃል። እሱ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ባልደረቦቹንም ይወቅሳል።
“በትግራይ ክልል ከሚኖሩ ያገቡ ሴቶች መካከል 18.7 በመቶ ከዚህ በተጨማሪ 81 በመቶ በትግራይ ገጠር አካባቢ የሚኖሩ ሴቶች በወላጆቻቸው ወይም አሳዳጊዎቻቸው ወይም የቅርብ ሰው ከተደፈሩ በኋላ ደፋሪዎቻቸውን እንዲያገቡ ይደረጋል” በሚል የቀረበው ጥናት እረፍት የሚነሳ ጉዳይ ቢሆንም ለእነ ስታሊን ጊዜ ጠብቆ የኃይል ሚዛን ማስጠበቂያ በትር እስካልጠቀመ ድረስ ምናቸውም እንደሆነ የሚገልጸው የማነ፣ በጉዳዩ ላይ ወደፊት በስፋት እንደሚመለስበት ገልጿል።
ስታሊን “የሕዝብ ድምጽ” ተብሎ በድለኞችን እንዲያጋልጥ የተላከለት መረጃ ላይ ተኝቶ ለመኖር ያስቻለው ጉዳይ ቢመረመር ከፍተኛ የሞራል ልዕልና ጥያቄ እንደሚያስነሳ የጠቆመው የማነ፣ “አንድ ማሰብ የሚችል ሰው፣ አንድ የህዝብ ድምጽ ነኝ፣ ሚዲያዬን እርዱ የሚል ባለሙያ ባለስልጣናት ሲታሉ ጠብቆ ለማስፈራሪያ እንዲህ ያለውን ኃያል ጉዳይ ማንሳቱ ሊያሳፍረው ይገባል። ይህ እሳቤ እንደ አንድ የትግራይ ተወላጅ በግል የቁም ሞት ነው። ስታሊንም ይቅር ሊባል የማይችል ውንጀለኛ መሆኑን መስክሯል። ፍትህ የምትናፍቁ ተነሱ” ብሏል።

ለስታሊን ማስፈራሪያ መነሻ የሆነው ቢቢሲ ሪፖርት ያደረገው የኢኳቶሪያል ጊኒ ባለስልጣን ጉዳይ ያንብቡ። ባለትዳር እና የልጆች አባት የሆነው ባልታዛር ኤባንግ ኤንጎንጋ የተባለው ግለሰብ በኢኳቶሮያል ጊኒ መንግሥት የገንዘብ ሚኒስቴር ውስጥ ከፍተኛ ባለሥልጣን የነበረ ሲሆን፣ በቢሮው ውስጥ ከተለያዩ ሴቶች ጋር ወሲብ ሲፈጽም የሚያሳዩ ቪዲዮዎች በማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ ተሠራጭተዋል።
የወሲብ ቪዲዮዎቹ ከመላዋ ኢኳቶሪያ ጊኒ ውጪ ጭምር በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት መሠራጨታቸውን ተከትሎ የአገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ውስጥ እንዲህ ያለ ድርጊቶችን በሚፈጽሙ ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወሰድ በመግለጽ ማስጠንቀቂያ መስጠታቸው ይታወሳል።
ባልታዛር ቪዲዮዎቹ ይፋ ከመሆናቸው በፊት በሙስና ወንጀል ተጠርጥሮ በዋና ከተማዋ ማላቡ ውስጥ በሚገኘው ብላክ ቢች በተባለ እስር ቤት ታስሮ የሚገኝ ሲሆን፣ እስካሁን በጉዳዩ ላይ የሰጠው ምላሽ የለም።
ባለሥልጣኑ ከአገሪቱ ፕሬዝዳንት ቴዎዶር ኦቢያንግ ንጉዌማ ጋር ዝምድና ያለው ቢሆንም፣ የቪዲዮዎቹ ይፋ መሆንን ተከትሎ በፕሬዝዳንቱ በተፈረመ ደብዳቤ ከሥልጣኑ መባረሩ ተገልጿል።
በኢኳቶሪያል ጊኒ ዜጎች ዘንድ ቆንጆ መሆኑ የሚነገርለት ባተልታዛር ኤባንግ ኤንጎንጋ ለዚህም በቅጽል ስም ‘ቤሎ’ በመባል ይጠራል።
ግለሰቡ በመቶዎች ከሚቆጠሩ እና ከበርካታ የአገሪቱ ባለሥልጣናት ሚስቶች ጋር ወሲብ ሲፈጽም የቀረጻቸው ቪዲዮዎች በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ይፋ መሆናቸው በአገሪቱ ውስጥ መነጋገሪያ ከመሆን አልፎ መንግሥት ማስጠንቀቂያ እና ሌሎች እርምጃዎችን እንዲወስድ አድርጎታል።
ከእነዚህ ቪዲዮዎች ውስጥ የተወሰኑት በአገሪቱ የገንዘብ ሚኒስቴር ውስጥ በሚገኘው ጽህፈት ቤቱ ውስጥ የተቀረጹ የወሲብ ድርጊቶች መሆናቸው ተገልጿል።
አንዳንዶች የቪዲዮዎቹ ይፋ መሆን እና የባልታዛር ከሥልጣን መባረር ቀጣዩ ፕሬዝዳንት ለመሆን በአገሪቱ መንግሥት ውስጥ ካለው የሥልጣን ሽሚያ ጋር የሚያያዝ ነው ብለው እንደሚያምኑ ይናገራሉ።
የባተልታዛር ኤባንግ ኤንጎንጋ አባት ለ45 ዓመታት ያህል የኢኳቶሪያል ጊኒ ፕሬዝዳንት ሆነው የቆዩትን እና በዕድሜ የገፉትን ቴዎዶር ኦቢያንግ ንጉዌማን ይተካሉ ተብሎ ሲጠበቅ ነበር።
አሁን በልጃቸው ባልታዛር ላይ የቀረበው የሙስና እና የወሲብ ቅሌት የፕሬዝዳንቱ ልጅ እና የአገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ቴዎዶሮ ኦቢያንግ ማንጉ በቀጣይ ሥልጣኑን እንዲረከብ በር ሊከፍት ይችላል ተብሎ ይታሰባል።
ምክትል ፕሬዝዳንቱ በሥራ ቦታ ላይ ወሲባዊ ግንኙነት ሲፈጽሙ የሚያዙ የመንግሥት ሠራተኞች “ከባድ እርምጃ” እንደሚጠብቃቸው ከቀናት በፊት ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል።
ምክትል ፕሬዝደንቱ ወሲባዊ ይዘት ያላቸው ቪድዮዎች ከተለቀቁ በኋላ ባወጡት መግለጫ ወሲባዊ ግንኙነት ሲፈጽሙ የሚያዙ የመንግሥት ሠራተኞች “ከባድ እርምጃ” እንደሚጠብቃቸው ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል።
ምክትል ፕሬዝደንቱ እንደተናገሩት ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ በሥራ ቦታ ወሲብ ሲፈጽም ከተገኘ “የሥነ ምግባር ደንቡን በመጣስ” ምክንያት ከሥራው ይታገዳል ብለዋል።
“ሥነ ምግባር የጎደላቸውን እና ሕገወጥ ድርጊቶችን” ለመከላከልም የደኅንነት ካሜራዎች በፍርድ ቤቶች እና በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች እንዲተከሉ አዘዋል።
የምክትል ፕሬዝዳንቱ ጽህፈት ቤት መግለጫ እንዳስታወቀው ውሳኔው የተላለፈው “የአገሪቷን ገጽታ የሚያንቋሽሹ ቪዲዮዎች” በሰፊው በመሰራጨታቸው ነው።
በቴሌግራም የከተሉን https://t.me/+f_kxmaPjD-9jYTdk