የገንዘብ ሚኒስቴር ዛሬ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና ለጉምሩክ ኮሚሽን በፃፈው ደብዳቤ ፍራንኮ ቫሉታ ከዛሬ ጀምሮ መከልከሉን ጠቅሷል፡፡
የብር የመግዛት አቅም በገበያው እንዲወሰን ከተደረገ በኋላ ለተወሰነ ጊዜ የነዳጅ ተሽከርካሪዎችን እና የፀጥታ ተቋማት መሳሪያዎችን ሳይጨምር ሌሎች ምርቶችን በፍራንኮ ቫሉታ ወደ ሀገር ማስገባት ተፈቅዶ እንደነበር ይታወሳል፡፡
ይሁንና ከሳምንታት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በፓርላማ ተገኝተው ማብራሪያ ሲሰጡ የተፈቀደው ፍራንኮ ቫሉታ ሀብት ከሀገር እንዲሸሽ ምክንያት እየሆነ በመሆኑ ሊታገድ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥተው እንደነበር ይታወሳል፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር ዛሬ ለተጠቀሱት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤም ከዚህ ቀደም በፍራንኮ ቫሉታ ሸቀጦችን ከውጪ ያዘዙ ካሉ ከዛሬ ጀምሮ በ2 ሳምንት ጊዜ ውስጥ ግዢ የተፈፀመባቸው ህጋዊ ሰነዶችን ለጉምሩክ ኮሚሽን በማቅረብ ተቀባይነት አቅርበው የንግድ ሸቀጦቹ ወደ ሀገር እንዲገቡ ይደረጋል፡፡
(Via- ሸገር)
