እስራኤል በ5 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር ተዋጊ ጀቶችን ለመግዛት ውል መፈራረሟን የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሀገሪቷ 25 ዘመናዊ አሜሪካን ሰራሽ ኤፍ-15 ጀቶችን ከአሜሪካው ቦይንግ ኩባንያ ለመግዛት ነው የተፈራረመችው።
የግዢ ክፍያም ከአሜሪካ በድጋፍ ከሚገኝ ገንዘብ እንደሚፈጸም ተገልጿል። ውሉ ለወደፊት ተጨማሪ 25 ጀቶችን የመግዛት ምርጫንም እንደሚጨምር ተጠቅሷል።
እስራኤል ዛሬ ጠዋት በጋዛ በፈጸመችው ጥቃት 27 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን በቤሩት በፈጸመችው የአየር ጥቃት ደግሞ 40 ሰዎች መገደላቸውንና 53 ሰዎች መቁሰላቸውን አልጃዚራ ዘግቧል።
ቦይንግ “ኤፍ -15” ጄቶቹን ለእስራኤል ከአውሮፓዊያኑ 2031 ጀምሮ ማቅረብ እንደሚጀመርና በየዓመቱም ከአራት እስከ ስድስት ጄቶችን አጠናቆ እንደሚያስረክብ የመከላከያ ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
Via walta