በአጭር ጊዜ በምግብ ራሳችን በመቻል ለዓለም ተምሳሌት እንሆናለን – የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
በአጭር ጊዜ በምግብ ራሳችን በመቻል ለዓለም ተምሳሌት ሀገር እንሆናለን ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።
አገልግሎቱ ባወጣው መግለጫ፤ አሁን የታዩ አበረታች ውጤቶችን በማስቀጠል ከምግብ እርዳታ ጥገኝነት ተላቀን ራሳችን መቻል ሉዓላዊነታችንን የተሟላና የፀና ያደርገዋል ብሏል።
በአባቶቻችን ተጠብቆ የቆየ ሉዓላዊነታችን በጀግኖች አርሶ አደሮቻችን፣ በየእርከኑ ባሉ አመራሮች፣ ባለሙያዎችና በሌሎች ባለድርሻ አካላት ላብ ሉዓላዊነታችን ፀንቶ ይቀጥላል በማለት ገልጾ፤ በአጭር ጊዜ በምግብ ራሳችን በመቻልም ለዓለም ተምሳሌት ሀገር እንሆናለን ሲል አስታውቋል።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ያወጣው መግለጫ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል:-
በደማችን ተከብሮ የቆየው ሉዓላዊነታችን በላባችን ፀንቶ ይቀጥላል!
ኢትዮጵያ በተለያዩ ወቅቶች በውጭ ወራሪዎችና ጠላቶች የሚቃጡባትን ጥቃቶች በጀግኖች ኢትዮጵያዊያን ደምና አጥንት ሉዓላዊነቷ ተከብሮ፣ የነፃነት ተምሳሌት ሆና ኖራለች፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያ የቀደምት ስልጣኔዎች ባለቤት፣ በተፈጥሮ ሀብቶች የበለጸገች፣ የሰው ልጅ እና የቡና መገኛ፣ በቅኝ ያልተገዛች የነፃነት ተምሳሌት ናት፡፡
ይሁን እንጂ ይህ አኩሪ ታሪካችንና ማንነታችን በተለያዩ ውስብስብ ምክንያቶች በኢኮኖሚያዊ እድገታችን ከዓለም ሀገራት ወደኋላ ቀርተናል፡፡ ይህ ሄኔታ ወደኋላ መቅረት ብቻም ሳይሆን በስንዴ ምፅዋት እንድንኖር አድርጎናል፡፡ በአባቶቻችን ደምና አጥንት ተጠብቆና ተከብሮ የኖረው ሉዓላዊነታችን በላባችን ማፅናት ባለመቻላችን በስንዴ ልመና እና እርዳታ ነፃናታችን ተሸራርፏል፡፡ ሕዝቡን ለመመገብ የሌለውን እጅ የሚጠብቅ ነፃነቱና ሉዓላዊነቱ የተሟላ አይሆንምና፡፡
በመሆኑም ይህንን የእርዳታ ጥገኝነት ሁኔታን ለመቀየር፣ “በደም የተጠበቀውን ሉዓላዊነት በላባችን እናፀናል” በሚል ቁርጠኛ አቋምና ርዕይ በምግብ ራስን ለመቻል ተግባራዊ እርምጃዎችን መውሰድ ተጀምሯል፡፡ በምግብ እህል ራሳችንን ለመቻል በልዩ ትኩረት መስራት ከተጀመረ ጊዜ ወዲህ ተጨባጭ ለውጦች እየተመዘገቡ መጥተዋል።
ቁርጠኝነት በተሞላበት የመንግሥት አቅጣጫን በመከተል ሀገሪቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ በስንዴ ምርት ራስን ለመቻል በተደረገው ርብርብ ሀገራችን ስንዴን ከመሸመት ወጥታ ለውጭ ገበያ ማቅረብ ጭምር ችላለች፡፡ በዘርፉ በተመዘገበው ውጤት እውቅናና ሽልማትም ተችሯታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በምግብ ራስን ለመቻል ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎች ተጀምሯል፡፡
በተለይም ባለፉት ሦስት እና አራት ዓመታት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር፣ የበጋ ስንዴ፣ የሌማት ትሩፋትና መሰል ስኬታማ ንቅናቄዎች በምግብ ራስን ለመቻል የተደረጉ ጥረቶች ማሳያዎች ናቸው፡፡
በመስኖ በሚለማ የበጋ ስንዴ ምርት አስደናቂ እመርታ በማስመዝገብ ከውጭ በሚገቡ ምርቶች ላይ ያለውን ጥገኝነት በእጅጉ በመቀነስ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ወጪን ማዳን ተችሏል። በአትክልትና ፍራፍሬ ልማትም ራስን ከመቻል ባሻገር እንደ አቮካዶ ያሉ ምርቶችን ለዓለም ገበያ ማቅረብ ጀምረናል፡፡
በግብርናዉ ዘርፍም ቴክኖሎጂ እና ሌሎች ዘመኑን የዋጁ ግብዓቶችን መጠቀም መጀመራችን ይበልጥ መደላድልን ፈጥሯል፡፡ ለዚህ አመቺ መደላድል ለመፍጠርም የግብርና ቴክኖሎጂዎች ከቀረጥ ነፃ የሚገቡበት የሕግ ማሻሻያ በለውጡ ማግሥት ተደርጓል፡፡ እንደ አፈር ማዳበሪያ ያሉ ግብዓቶችም በበርካታ ቢሊዮን ብር የመንግሥት ድጎማ ለአርሶ አደሩ እየቀረቡ ይገኛል፡፡ በዚህም ኢትዮጵያ ከዓለማችን በግብርና ምርት ፈጣን ለውጥ ካመጡ ሀገራት መካከል በግንባር ቀደምትነት ትጠቀሳለች።
አሁን የታዩ አበረታች ውጤቶች በማስቀጠል ከምግብ እርዳታ ጥገኝነት ተላቀን ራሳችን መቻል ሉዓላዊነታችንን የተሟላና የፀና ያደርገዋል፡፡ በአባቶቻችን ተጠብቆ የቆየ ሉዓላዊነታችን በጀግኖች አርሶ አደሮቻችን፣ በየእርከኑ ባሉ አመራሮች፣ ባለሙያዎችና በሌሎች ባለድርሻ አካላት ላብ ሉዓላዊነታችን ፀንቶ ይቀጥላል፡፡ በአጭር ጊዜ በምግብ ራሳችን በመቻልም ለዓለም ተምሳሌት ሀገር እንሆናለን፡፡
ሰሞኑን ኢትዮጵያ ከረሃብ ነፃ ዓለም ጉባኤን የማስተናገዷ አንዱ ምሥጢርም በግብርናዉ ዘርፍ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ያስመዘገበችዉ ስኬት ነው፡፡
ጉባኤዉ በርካታ ተሞክሮዎች የቀረበቡበት፣ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ አብነት ተደርጋ የተወሰደችበት፣ መሰል ዓለማቀፍ ጉባኤዎችን የማስተናገድ የመሠረተ ልማትና የመስተንግዶ ባህል ዐቅሟና ልምዷ በእጅጉ ማደጉን ያሳየችበት ሆኖም በስኬት ተጠናቅቋል፡፡
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
TIPS
Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security