በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ መምህራን ለከተማ መስተዳድሩ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት፤ ለመምህራን አገልግሎት የሚውል ሆስፒታል ግንባታ ፕሮጀክት መጀመሩን የአዲስ አበባ መምህራን ማሕበር አስታውቋል።ፕሮጀክቱ ለመምህራን ልዩ ድጋፍ ለማድረግ ያለመ ሲሆን፤ ሆስፒታልን ጨምሮ ለንግድ ሥራ የሚውል ሁለገብ ሕንፃ በግንባታ ላይ መሆኑን የማሕበሩ የኮሙኒኬሽን ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ሙሴ ለአሐዱ ተናግረዋል።
በአዲስ አበባ ይገነባል የተባለውን የመምህራን ሁለገብ ሕንፃ ኡራኤል አካባቢ የሚገነባ ሲሆን፤ ከአዲስአበባ ከተማ መስተዳድር 50 ሚልየን ብር ድጋፍ እንደተደረገለት አቶ ሳሙኤል ሙሴ ገልጸዋል።ሕንፃው በ36 ካሬ ሜትር ያረፈ ስለመሆኑም ተናግረዋል።የመምህራን ሆስፒታሉ ማስገንብያ መዋእለ ንዋይ ከህብረተሰቡና ከደጋፊ ተቋማት ለማሰባሰብ ውጥን የተያዘለት መሆኑን አሐዱ ከኮሙኒኬሽን ኃላፊው መረዳት ችሏል።
ለመምህራን የቤት ግንባታ አበዳሪ የፋይናንስ ተቋምና አነስተኛ ወለድ የሚያገኙበት ባንክ በማፈላለግ ላይ መሆኑንም ማሕበሩ ገልጿል።ከመምህራን የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመፍታት ማሕበሩ በብርቱ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የገለጹት የኮሚኬሽን ኃላፊው፤ ከዚህ በተጨማሪም የመምህራን ባንክ ለማቋቋም ውጥን መያዙንም አንስተዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ መምህራን ማሕበር በሥሩ ወደ 33 ሺሕ የሚጠጉ አባላት ያለው መሆኑንና፤ በየጊዜው ከመምህራን የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመፍታት እየሰራ መሆኑን የኮሙኒኬሽን ኃላፊው ገልጸዋል።በኢትዮጵያ ተቋቁመው ሥራ ላይ ከሚገኙ የሙያ ማሕበራት መካከል የአዲስ አበባ ከተማ መምህራን ማሕበር ግንባር ቀደሙ ተጠቃሽ መሆኑን ይታወቃል።
Via : Ahadu
TIPS
Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security