የአማራ ክልል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች ጽንፈኛ ኃይሎች በፈጠሩት ቀዉስ የሰላም እጦት ገጥሞት የቆየ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሰዉ ጽንፈኛ ቡድን፣ በሕዝብ ስም እየማለ እታገልለታለሁ የሚለዉን የአማራ ሕዝብ ለከፋ ጉዳት እና አሰቃቂ ችግሮች እየዳረገዉ ይገኛል፡፡
ጽንፈኛው ቡድን የሰዎች እና የምርት እንቅስቃሴ በክልሉ ዉስጥ እንዳይኖር መሰናክል ፈጥሯል፤ ሰዉ እያገተ የድኻ ገንዘብ ዘርፏል፤ ሕፃናትን በማገት የቤተሰብ ጥሪት ከማሟጠጥ ጀምሮ ያገታቸዉን ሕፃናት በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሏል፤ አካባቢያቸዉ ሰላም እንዲሆን የጠየቁ የሀገር ሽማግሌዎችን አግቶ ገንዘባቸዉን ከመዝረፍ በተጨማሪ በእንብርክክ አስኪዶ ገድሏቸዋል፤ አዳጊ ሕፃናትን ከትምህርት ገበታቸዉ እንዲነጠሉ አድርጓል፤ የሞያ ሥነ ምግባራቸዉን እና ሀገራዊ ኃላፊነታቸዉን ለመወጣት በትምህርት ገበታ ላይ የተገኙ መምህራንን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሏቸዋል፤ በመማሪያ ክፍሎች ዉስጥ ቦንብ በማፈንዳት በተማሪዎች ላይ አካላዊ እና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት አድርሷል፡፡ ከዚህም በላይ የሆኑ፣ የሰሚን ጆሮ ጭው የሚያደርጉ ዘግናኝ ወንጀሎችን ፈጽሟል።
ይህ በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች የሚንቀሳቀስ ጽንፈኛ ኃይል፣ ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን እና የሕዝብ አብሮነትን የማይቀበል ኋላ ቀር ኃይል ነው። ይልቁኑም መቃቃርን የሚፈጥር፤ የኅብረተሰቡን ዕሴት በመሸርሸር እና አሰቃቂ ጥፋቶችን በመፈጸም የተጠመደ አረመኔያዊ ቡድን ነዉ፡፡
በተመሳሳይ መልኩ በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሰዉ ሽብርተኛዉ የሸኔ ቡድንም እታገልለታለሁ የሚለዉን የኦሮሞ ሕዝብ እጅግ መራር እና አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ግድያ፤ እገታ፤ ዝርፊያ፤ አፈና እየፈጸመበት ይገኛል፡፡ ሁለቱም ጽንፈኛ ኃይሎች ለአንድ አሰቃቂ ዓላማ ሁለት ቦታ የተሰለፉ ዕኩይ ቡድኖች ናቸው። እየፈጸሙት የሚገኙት እኩይ ተግባር በጦር ሜዳ የደረሰባቸዉን ኪሳራ ለማስቀየሻ የሚፈጽሙት ነው።
መቃብራቸው የሚቆፈረው በሕዝቦች ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ላይ በመሆኑ፣ ሕዝብን እርስ በርስ ማጋጨት እና ንጹሐንን መጨፍጨፍ የትግል ስልታቸው ነው።
እነዚህ መቃብራቸው የተማሰ፣ ልጣቸው የተራሰ ጽንፈኛ እና ሽብርተኛ ቡድኖች፤ ከሰሞኑ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን፣ ደራ ወረዳ ያደረሱትን ዘግናኝ እና አሰቃቂ ድርጊት የአማራ ክልል መንግሥት እና ሕዝብ በጽኑ ያወግዛሉ፡፡ ይህ ወንጀል ሰዉ የሆነ ፍጡር የማይፈጽመው የአዉሬነት ተግባር ነው።
እነዚህ በጣዕረ ሞት ላይ የሚገኙ ጽንፈኛ ኃይሎች፣ ለዘመናት ማንም በማይበጥሰው የወንድማማች እና እኅትማማች ገመድ የተሣሠሩትን የአማራ እና የኦሮሞ ሕዝቦች ለመነጣጠል እና ወደ ግጭት ለማስገባት የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም። ነገር ግን ሰላም ወዳዱ እና አርቆ አሳቢዉ ሕዝባችን ነገሮችን በጥንቃቄ እና በአስተዉሎት በማየት፣ ድርጊታቸዉን እና ዓላማቸዉን ቀድሞ በመረዳት፣ የጽንፈኞችን እና የሤረኞችን እኩይ እና አጸያፊ ተግባር በንቃት እየመከተ ይገኛል፡፡
የአማራ ሕዝብና የአማራ ክልል መንግሥት ከኦሮሞ ሕዝብና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት እንዲሁም ከፌዴራል መንግሥት ጋር በመሆን እነዚህ ዘግናኝ ተግባር የፈጸሙ ጽንፈኛ እና አሸባሪ ቡድኖች ለሕግ ቀርበው አስፈላጊዉን ቅጣት እንዲያገኙ አበክረን እየሠራን መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡
የአማራ ክልላዊ መንግሥት ከዉጭና ከዉስጥ ጠላቶቻችን ጋር በጋራ የሚሠሩ፣ እንዲሁም እርስ በርሳቸዉ የሚናበቡ ጽንፈኛ ኃይሎች፤ በንጹሐን ዜጎች ላይ በአሰቃቂ ሁኔታ ግድያ በመፈጸም በሕዝቦች መካከል ግጭት ለመፍጠር የሚፈጽሙትን እኩይ ተግባር በአስተማማኝ ሁኔታ በመቀልበስ ብርቱ ክንዳችንን እያሳረፍንባቸዉ እንገኛለን።
ወደፊትም ይህን ጠንካራ የሕግ ማስከበር ሥራ አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል፡፡
መላዉ የክልላችን ሕዝብና ሌሎች ወንድም እና እኅት ኢትዮጵያዉያን የሕግ የበላይነት እንዲከበር ከመንግሥት ጎን በመሰለፍ የበኩላችሁን እንድትወጡ በዚሁ አጋጣሚ ጥሪያችንን እናስተላፋለን፡፡
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
ኅዳር 15/ 2017 ዓ.ም
ባሕርዳር
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring