በተለያዩ ክፍለ ከተሞች በመንቀሳቀስ የውንብድና እና የቅሚያ ወንጀል ሲፈፅሙ የቆዩ 17 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ፤ የተለያዩ ንብረቶችም ከተጠርጣሪዎቹ እጅ ላይ በኤግዚቢትነት ተይዘዋል።
የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ መስለው በተሽከርካሪ እየተንቀሳቀሱ የሃይል ተግባር በመጠቀም በተለያዩ ግለሰቦች ላይ የቅሚያ እና የውንብድና ወንጀል ፈፅመዋል የተባሉ 17 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ የገለፀው በየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የአድዋ ድልድይ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ነው፡፡
ተጠርጣሪዎቹ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-30785 ኦሮ በሆነ ሚኒባስ ተሽከርካሪ እየተንቀሳቀሱ ምሽት ላይ አንድን ግለሰብ ከቦሌ ጌታሁን በሻህ ህንፃ አካባቢ ጭነው ከወሰዱ በኋላ አመቺ ቦታ ሲደርሱ የግለሰቡን እግር በጫማ ገመድ አስረው እና በስለት አስፈራርተው ሞባይል ስልክ እና ጥሬ ገንዘብን ጨምሮ በአጠቃላይ 21ሺህ 500 ብር የዋጋ ግምት ያላቸውን ንብረቶች ወስደው ተሰውረዋል፡፡
አቤቱታው የደረሰው ፖሊስ ጣቢያው የተለያዩ መረጃዎችን በማሰባሰብ ባደረገው ክትትል ወንጀሉ የተፈፀመበትን ተሽከርካሪ በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡ የወላጆቹ በሆነው ተሽከርካሪ በቀኑ ክፍለ ጊዜ የትራንስፖርት አገልግሎት ሲሰጥ ውሎ ምሽት ላይ እስከ 10 ሺህ ብር የሚደርስ ገንዘብ እየተቀበለ መኪናውን አሳልፎ ለወንጀል ፈፃሚዎቹ ሲሰጥ የነበረ ግለሰብን ጨምሮ በወንጀሉ ተሳትፎ አላቸው የተባሉ 17 ተጠርጣሪዎች ፖሊስ ባደረገው ክትትል ተይዘዋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ከምሽቱ አንድ ሰዓት እስከ አራት ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች እና አካባቢዎች እየተንቀሳቀሱ ወንጀሉን ሲፈፅሙ የቆዩ እና በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ እና በሌሎች ፖሊስ ጣቢያዎች ተጨማሪ የምርመራ መዝገብ የተደራጀባቸው ስለመሆናቸው ከፖሊስ ጣቢያው የተገኘው መረጃ አመልክቷል ፡፡
34 የተለያዩ አይነት ሞዴል ያላቸው ሞባይል ስልኮች፣ ላፕቶፕ ኮምፒውተር እና ሌሎች ልዩ ልዩ ንብረቶች በተጠርጣሪዎቹ እጅ ላይ ተገኝተው የምርመራው ስራ መቀጠሉ ተገልጿል፡፡ ግለሰቦቹ በተለያዩ አካባቢዎች እየተንቀሳቀሱ ወንጀሉን ሲፈፅሙ መቆየታቸውን የገለፀው ፖሊስ በግለሰቦቹ ተመሳሳይ ወንጀል የተፈፀበትና ፈፃሚዎቹን ለይቶ የሚያውቅ የካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ በአካል በመምጣት መረጃ መስጠት እንደሚችል አስታውቋል ።
የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች ባለ ንብረቶች የመኪናቸውን ውሎ እና ተግባር ትኩረት ሰጥተው ከመከታተል ባሻገር በአሽከርካሪዎቹ ላይ ተገቢውን ቁጥጥር በማድረግ መሰል ወንጀሎችን ለመከላከል የበኩላቸውን ሃላፊነት ሊወጡ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል፡፡
TIPS
Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security