አቶ አብነት ገብረመስቀል ከሳሽ በነበሩበት የቦሌ ታወርስ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል መሕበርን በባለአንድ አክሲዮን ሆኖ እንድጠቀልለው ይወሰንልኝ ብለው ያቀረቡት ክስን ፍርድ ቤት ሳይቀበለው ቀርቷል ።
በአቶ አብነት ከላይ በተጠቀሰው ምክንያት ተከሰው የነበሩት አላሙዲ የተከሳሽ ከሳሽ በመሆን በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ንግድና ኢንቨስትመንት ምድብ 5ኛ ንግድ ችሎት ሲከራከሩ ቆይተዋል ።
ጉዳዩን ለወራቶች ሲመለከት የቆየውም ፍርድ ቤቱም መጋቢት 30 ቀን 2016 አም በዋለው ችሎት ፍርድ ሰጥቶ ነበር ።
በወቅቱ ፍርድ ቤቱ በአቶ አብነትእና በሼኽ መሐመድ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ብርቱ በመሆኑ መሐበሩ ከሚፈርስ ቦሌ ታወርስ ኋላፊነቱ የተወሰነ የግል መሐበርን ሼኽ መሐመድ እንዲጠቀልሉት ሲል ፍርድ ሰጥቶ ነበር ።
ይህን የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ በመቃወም አቶ አብነት ገብረመስቀል ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 6ኛ ንግድ ይግባኝ ችሎት ይግባኝ በማለት ቅሬታ አቅርበው እንደነበር የውሳኔ መዝገቡ ይገልፃል ።
ይግባኙን ሲመለከት የቆየው ፍ / ቤቱም ማክሰኞ ታህሳስ 15 ቀን 2017 አም በቀረበው ይግባኝ ላይ ውሳኔ ሰጥታል ።
ፍርድ ቤቱ በውሳኔውም አቶ አብነት ገብረመስቀል የመሐበሩ ስራ አስኪያጅ ሆነው በሚሰሩበት ጊዜ መሐበሩ ከተመሠረተ ጊዜ ጀምሮ ከ20 አመታት በላይ ለሆነ ጊዜ ጠቅላላ ጉባኤ ጠርቶ እንደማያውቅ ፣ የመሐበሩን ሒሳብ በወቅቱ እንደማያሰሩ ፣ የመሐበሩ የሒሳብ ሚዛን የኦዲት ሪፖርት የስብሰባ ቃለ ጉባኤዎችና ሌሎች ሰነዶች ለሼኽ መሐመድ ያልሰጡ መሆናቸውና የስብሰባ ቃለ ጉባኤዎች የ15 አመታት የሒሳብ መዝገቦች አና ሰነዶች የየአመቱ ትርፍና ኪሳራ መግለጫ ፣ የየአመቱ የንብረት ዝርዝር ፣ የየአመቱ ሐብትና እዳ መግለጫ ወይም የሒሳብ ሚዛን የሌሉ መሆናቸው ና ፣ የየአመቱ የመሐበሩ አጠቃላይ እንቅስቃሴ የሚያሳይ ሰነድ የሌለ መሆኑ ፣ በመሐበሩና በይግባኝ ባይ መካከል ከፍተኛ የጥቅም ግጭት መኖሩን፣ የመሐበሩን ሰነዶች በአግባቡ አለመያዛቸው፣ መሐበሩን በተገቢው ጥንቃቄ እና ትጋት አለመምራታቸው፣ የማህበሩ ይዞታን የሆነ 2000ካ ሬ ሜትር ስመሀብት ወደ መሐበሩ አለመዞሩ ፣የመሐበሩ ካፒታል ከአስር ሚሊዮን ብር ወደ ስድስት መቶ ሚሊዮን ብር ያደገ መሆኑን ቢገልፅም ድርሻው ያደገው ግን ወደ አምስት መቶ አርባ አምስት ሚሊዮን ብር ብቻ መሆኑን ፣ለማህበሩ ህንፃ ግንባታዎች የተደረጉ ወጪዎች አለመመዝገባቸው ፣ ማህበሩ ከዳሽን ባንክ በሶስት ብድሮች የወሰደው አርባ አምስት ሚሊዮን ብር እና ከማህበሩ የባንክ ሒሳበሰ የተደረጉ ክፍያዎች፣ በማህበሩ ሒሳብ አለመመዝገባቸው፣ መሐበሩ ሲመሠረት የተከፈለው መዋጮ በመሐበሩ ስም በተከፈተ ዝግ ሒሳብ አሐመቀመጡ ፣ በኦዲት ሪፖርት መረጋገጡ ምክንያትነት በመጥቀስ ነው
ይግባኝ ባይ በማህበሩ ይዞታዎች ወደ ግላቸው ያዛወሩ መሆኑም ተረጋግጧል ።እነዚህ ተግባራት ይግባኝ ባይ በማህበሩ ጥፋትና ጉዳት ያደረሱ መሆኑ የሚያስረዱ ናቸው ።
እነዚህ የፈፀሟቸው ተግባራት በሁለቱ ባለአክሲዮኖች አለመተማመን የሚፈጥሩና አብረው መቀጠሉ ማህበሩ አላማውን ያሳካል ተብሎ ስለማይገመት ማህበሩ በቀጣይነት የተመሠረተበትን አላማ እንዲያሳካ ጥፋት የፈፀሙት ባለአክሲዮን አቶ አብነት ገብረመስቀል በመሆናቸው የስር ፍርድ ቤት እነዚህን ጥፋቶች ይግባኝ ባይ ከማህበሩ ለማስወጣት የሚያበቁ በቂ ምክንያት ነው ብሎ ይግባኝ ባይ ከመሐበሩ አባልነት እንዲሰናበቱ ውሳኔ መወሰኑ በማስረጃ ምዘና የፈፀመው ስህተት የለም ሲል ወስናል ።
ውሳኔው ሲቀጥልም አቶ አብነት ገብረመስቀል ከመሐበሩ እንዲሰናበቱ በመወሰኑ አክሲዮን ድርሻቸው በምን አግባብ ተሰልቶ እንደሚከፈላቸው በንግድ ህጉ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በሚመለከት በግልፅ የተቀመጠ ነገር የለም ።
ነገር ግን በን /ህ/ቁ 527(1)የን/ህ/ቁ403 ባለ አክሲዮን ከማህበሩ መውጣት በሚመለከት ከሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ተፈፃሚነት ያለው መሆኑ ስለደነገገ የስር ፍርድ ቤት አቶ አብነት ገብረመስቀል በቦሌ ታወርስ በመጨረሻ የሒሳብ አመት የሃብትና እዳ የሒሳብ መግለጫ ውስጥ በተመለከተው የማህበሩ ሐብት ውስጥ አክሲዮናቸው በሚመለከት መጠን ድርሻቸው ታስቦ እንዲከፈላቸው መወሰኑ የሚነቀፍበት ምክንያት የለም በመሆኑም አቶ አብነት በ29/09/2016 አም በፅሁፍ ያቀረቡትን የይግባኝ ቅሬታ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ንግድና ኢንቨስትመንት ምድብ 5ኛ ንግድ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 01605 በቀን 30/07/2016 ዓም በዋለው ችሎት የሰጠውን ውሳኔ ሊነቀፍበት የሚያስችል የህግም ሆነ የፍሬ ነገር ጉድለት ያልተገኘ በመሆኑ መልስ ሰጪን መጥራት ሳያስፈልግ በፍ/ብ/ስ/ ስ//ህ/ቁ 337 የይግባኝ ባይ አቤቱታን ፍርድ ቤቱ ሰርዟል ሲል ውሳኔ ሰጥቷል ።
Gazette plus