ለሁለት ተስንጥቀው ለመበላላት በየፊናቸው እየተወነጃጀሉና እየተካሰሱ ያኦኡት የትህነግ ወኪሎች፣ የፌደራል መንግስት የአገሪቱን ዓለም ዓቀፋዊ ወሰኖች የመጠበቅና የማስከበር ስልጣን ስላለው ይህንኑ ስልጣኑ ተጠቅሞ የሻዕቢያን ኃይል እንዲያስወጣ ጥያቄ ማቀረባቸው ተሰማ። በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ትህነግ የራሱን ምክር ቤት ማቋቋሙን ይፋ አደረገ።
የፌደራል መንግስት የሻዕቢያን ኃይል ከድንበር እንዲያስወጣና የአገሪቱን ሉዓላዊ አንድነት እንዲያስከብር ጥያቄ መቀረቡን ያስታወቁት የቀድሞ ሌ/ጄነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ ከድምጸ ወያኔ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው። ቃለ ምልልሱን ወደ አማርኛ የመለሰው ቲክቫህ ለዚህ ጥያቄ መንግስት የሰጠውን ማላሽ ስለመናገራቸው አልገለጸም።
መንግስት በአልጀርሱ ስምምነት መሰረት የድንበርና የይዞታ ይገባኛል ጥያቄው እንዲፈታ ኢሃዴግ በወሰነው መሰረት ቁርጠኛ አቋም እንዳለው ደጋግሞ ማስታወቁ አይዘነጋም። አቶ መለስ በፊርማቸው ያጸደቂት ስምምነት ባለፈ የሻዕቢያ ኃይሎች የያዙት ቦታ ካለ በንግግር ለማስተካከል እንደሚሰራ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለፓርላማ መናገራቸው አይዘነጋም።
እነ ድብረፅዮን በአዲስ አበባው ውይይት “ጌታቸውን ከፕሬዜዳንት እንሱልን እንጂ ጊዚያዊ አስተዳደሩ መልሰን በማደራጀት አብረናችሁ ለመስራት ዝግጁ ነን” ማለታቸውን ሌ/ጄነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ ተናግረዋል።
ሌ/ጄነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ የትግራይ አመራሮች በአዲስ አበባ ከጠቅላይ ሚንስትር ዐበይ አህመድ ጋር በወቅታዊ ጉዳይ በነበራቸው ቆይታ ክልሉን አስመልክቶ የሃሳብ ልዩነት እንዳልነበራቸው ገልጸዋል። ነገር ግን ” የትግራይ ፓለቲካ ከድጡ ወደ ማጡ እያመራ ነው ” እንቅጩን ተናግረዋል። በዚሁ የስጋት መንፈስ ” የፀጥታ ሃይሎች ከማንኛውም ጫና ነፃ ሆነው የህዝቡ ጥቅም ማረጋገጥ ይገባቸዋል ” ብለዋል።
በአዲስ አበባው ውይይት በእነ ደብረፅዮን ይሁን በእነ ጌታቸው የሚመሩት የህወሓት ልኡካን እንዲሁም የጊዚያዊ አስተዳደሩ ተወካዮች መካከል በትግራይ ወቅታዊ ሁኔታና ችግሮች ዙሪካ ያለልዩነት መስማማታቸውን ገልጸዋል። በወቅቱ ” የፌደራል መንግሰት የትግራይ ችግሮች እንዲፈቱ አላገዝክም ” በማለት ወቀሳ ማቅረባቸውንም ጠቁመዋል።
ለቀረበው ቅሬታ የፌደራል መንግስት ጉባኤ እንድናካሂድ ፤ የትግራይ ፓለቲካ እንድናስተካክል ጊዜ ይስጠን በማለት ዕድል እና ጊዚያችሁን አባክናቹሃል በማለት ችግሩ የራሳቸው መሆኑን እንዳስገነዘበ ገልጸዋል።
ሌተናል ጄነራሉ ” በመሃከላችን እየታየ ያለው ክፉኛ መሳሳብ የትግራይ ሉዓላዊ ግዛት እንዳይረጋገጥ ፣ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዳይመለሱ አደገኛ መሰናክል ሆኗል ” ብለዋል። ክልሎች ሉዓላዊ የሚባል ግዛት እንደሌላቸው እየታወቀ ይህን ማለታቸው ከምን መነሻ እንደሆነ ማብራሪያ አልቀረበም።
የፕሪቶሪያ ውል በይፋ የተቃወመ የለም ፤ በተግባር ግን ውሉን የሚያደናቅፍ አሉታዊ ተግባር የሚፈፀሙ አካላት አሉ ብለዋል። አክለውም ” የፕሪቶሪያ ውል በተሟላ መልኩ በመተግበር ብቻ ነው አቃፊ መንግስት ማቋቋም የሚቻለው ” በማለትም አስረግጠዋል።
” እነ ድብረፅዮን በአዲስ አበባው ውይይት ” ጌታቸውን ከፕሬዜዳንት ብቻ እንሱልን” ሲሉ መጥየቃቸውን ያስታወቁት ጻድቃን፣ አቶ ጌታቸው ከተነሱ፣ ጊዚያዊ አስተዳደሩ መልሶ ለማደራጀት አብረው ለምስራት ዝግጁ መሆናቸውን እነ ደብረጽዮን መናገራቸውን በግልጽ አስቀምጠዋል። ጊዜያዊ አስተዳደሩ ያሉበትን ፈተናዎች ተቋቁሞ የተገበራቸውን ስራዎች ዘርዝረው ቀደም ሲል የእነ ደብረጽዮን ቡድን “ከሃዲዎች በሚል ስማችንን ማጠልሸቱ ተገቢ አይደለም ” ሲሉ በምሬት ተናግረዋል።
በሌላ በኩል ፤ በፌደራል መ/ቤቶች የትግራይ ውክልና ባለመኖሩ ምክንያት የህዝቡ ድምፅ በተገቢው መንገድ ሊሰማ ባለመቻሉ ምክንያት ከጦርነቱ በፊት የነበረው የክልሉ ውክልና እንዲመለስ ለፌደራል መንግስት ጥያቄ መቅረቡን ሌተናል ጀነራሉ አሳውቀዋል።
በተጨማሪ ፤ ” የፕሪቶሪያ ውል አንቀፅ 8 ዓለምቀፍ ወሰኖች በፌደራል መንግስት እንዲጠበቁ ስለሚያዝ ኢትዮጵያ በትግራይ በኩል ከኤርትራ እና ከሱዳን የሚያገናኙ ወሰኖች ጠባቂ ስለሌላቸው የውጭ ሃይሎች እየገቡ ግፎች እየፈፀሙ ፣ ወርቅ ዝውውርን ጨምሮ ሌሎች ህገ-ወጥ ወንጀሎች እየተፈፀመባቸው በመሆኑ ወሰኖቹ በፌደራል መንግስት እንዲጠበቁ ” ሲሉ መጠየቃቸውን አሳውቀዋል።
በተመሳሳይ የትግራይ ዜና አቶ ጌታቸው የሚመሩት ትህነግ በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት የራሱን ምክር ቤት ማቋቋሙን አስታውቋል። ” የሃላቀርነት እና ወንጀል ቡድን ” ሲል የገለፀውን በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራውን የትህነግ ቡድን በፅኑ ለመታገል ቆርጦ እንደተነሳም አመልክቷል።
በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ትህነግ እስከ ቀጣዩ 14ኛው የደርጅቱ መደበኛ ጉባኤ የሚቆዩ ሊቀመንበር እና ምክትል ያቀፈ 7 አባላት ባሉት አስተባባሪ ኮሚቴ የሚመራ ም/ቤት ነው ያቋቋመው።
የደርጅቱን ምክትል ሊቀመንበር ማን አድርጎ እንደሰየመ ያልገለፀው መግለጫው ፤ አስተባባሪ ኮሚቴው የቀጣይ 3 ወራት እቅድ ማዘጋጀቱ አስታውቋል።
ደርጅቱ 14 ኛ ጉባኤውን መቼ እንደሚያካሂድ ያልገለፀ ሲሆን የተመሰረተው ምክር ቤት አባላት ሁሉም በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ከሚመራው ህወሓት ” አንሰለፍም ” ብለው የተቆራረጡ ናቸው።
በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት በከተማና ገጠር ከክልል ፣ ዞን ፣ ወረዳ እና እስከ ቀበሌ ድረስ አደራጃጀቶች በመዘርጋት ” የኃላቀርነት እና ወንጀል ቡድን ” ሲል የገለፀውን በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራውን ህወሓት በፅኑ ለመታገል ቆርጦ መነሳቱ ገልጿል።
መላው የትግራይ ህዝብ ፣ የህወሓት አባላት ፣ የፀጥታ ሃይሎች ፣ የአገር ሽማግሌዎች ፣ በተለይ ወጣቶች ፣ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ፣ የፓለቲካ ፓርቲዎች እና የዳያስፓራ ማህበረሰብ ከጎኑ እንዲሰለፉ ጥሪ ያቀረበው በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት ” በሰላማዊ ትግል የትግራይን ህዝብ ጥቅም ለማስክበር እታገላለሁ ” ብሏል።
ትህነግ ከፕሪቶሪያው ስምምነት ብሁዋላ ለሁለት ተክፍሎ ከባድ የቃላት ጦርነት ውስጥ መግባቱ በተለይም የትግራይን ህዝብ ወቅታዊ ፍላጎት ያላገናዘበና ፍጹም የሆነ የስልጣን ጥማት እንደሆነ እየተገለጸ ነው። በዚሁ አውራጃና መንደር በለየ ድጋፍ እተመራ ያለው የመበላላት ሩጫ ቃታ እንዳያማዝዝ ስጋት አለ።