“አቶ በቀለ ገርባ ስለ ጃዋር መናገር አይፍለጉም። ለዘብተኛውንና በአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ዘንድ የሚወደዱትን ፖለቲከኛ ነድፎ ጽንፍ ውስጥ ከተታቸው። በጩኸት አስክሮ፣ ሃብት እያሳየ በስተርጅና እንዲሰደዱ ምክንያት ሆነ። ይህ ማንም የማይክደው ሃቅ ነው። ኦፌኮንም እንደ ፓርቲ አርክሶታል። ይህ በቅርቡ ይፋ ይሆናል” ሲሉ አስተያየታቸውን የሰጡት የፓርቲው ቅርብ ሰው ናቸው። ጃዋር ለምንም ጉዳይ እንደማይታመን የሚገልጹ “ጃዋርን ያመነ ጉም የዘገነ” ሲሉ ይተርታሉ።
ጃዋር የኦሮሚያን ፖለቲካ አካልቦ፣ የኢትዮጵያን ፖለቲካ መርዞ ለዚህ ያበቃ፣ ለበርካቶች ዕልቂት በገሃድ ተጠያቂ መሆን የሚገባው፣ የወንጀል ክስ ፋይሉ ያልተዘጋ ተፈላጊ እንደሆነ በርካቶች ይናገራሉ። አንድ ሁለት ብለው ዘርዝረ ያቀርባሉ።
አዲስ ምንጭ ላይ ውብሸት ታዬ ዶክተር ኢተና ሃብቴ የሰጡትን ቃለ ምልልስ እየተረጎመ አቅርቧል። በዚሁ ቃለ ምልልስ የጃዋር የቀድሞ የቅርብ ሰውና የትግል አጋር የሆኑት ዶክተር ኢታና፣ ጃዋር ይህን በሚያጠናክር መልኩ ጃዋር “ሊጠየቅ ይገባል” ሲሉ ተደምጠዋል።
ደም ሲል በተመሳሳይ ባልደረቦቻቸው ዶክተር ጸጋዬ አራርሳና ሄኖክ ገቢሳ ጃዋር መሀመድን በፖለቲካ ግልሙትናና በሌብነት ሊጠየቅ እንደሚገባ በይፋ ምክንያታቸውን ዘርዝረው መናገራቸው ይታወሳል።
በህግ በሚያስጠይቁ በርካታ ጉዳዮችን በመፈጸሙና በንጹሃን ደም እንደተጨማለቀ ዝርዝር መረጃ እየቀረበበት የሚከሰሰው ጃዋር ” አልጸጸትም” የሚል መጽሃፍ ጽፎ ለማሰራጨት በዝግጅት ላይ ባለበት ወቅት ከቅርብ የትግል ባልደረቦቹ እየቀረበበት ያለው ጠንካራ ክስ የፖለቲካ ግብአተ መሬቱን ፍጻሜ አመላካች እንደሆነ ተደርጎም እየተወሰደ ነው።
“በነጮቹ አቆጣጠር ከ2018 ጀምሮ በኦሮሚያም ሆነ በመላው አገሪቱ ለተፈጠረው ቀውስና ኪሳራ ሁሉ ተጥያቂው ማን ነው” በሚል እየቀረበ ባለው መነጋገሪያ ጉዳይ ላይ የሚሰጠው ጠንካራ አስተያየት ” ጃዋር የብልጽግናን መንግስት ሊያስወግድ ነው” በሚል ሁሉንም ረስተው ከበሮ ለሚመቱት “የአማራ ነጻ አውጪ” ሚዲያዎችና “አክቲቪስት ነን” ባዮች መራራ ሃዘን እንደሆነም እየተሰማ ነው። አፍቃሪ ትህነግ ሆነው እየሰሩ ላሉና የጃዋርን ዳግም መከሰት እየሰበኩ ላሉ ሁሉ ጃዋር ላይ የተነሳው የህግ፣ የክህደትና የሌብነት ጥያቄ እንዳላስደሰታቸው እየተሰማ ነው።
ዶክተር ሄኖክ ገቢሳን ቃለ ምልልስ ያደረገው ርዕዮት ሚዲያም ጃዋርን ለማስተዋወቅና “ብልጽግናን የሚበላ ሰይፍ አለው” በሚል ሊያስቀምጥ የፍለገውን አጀንዳ “ጃዋር ያሳዝነኛል” በሚል አንኳሶና “በእኛ ዕድሜ ብልጽግናን የሚጥል ኃይል የለም” ብሎ መናገሩ ጠያቂውን የምጸት ሳቅ እንዲስቅ ሲያስገድደው ለማየት ትችሏል።
“ጃዋር ወዴት እየሄደ ነው” ብለው የጠይቁ የኦሮሞ ፖለቲካ በአዲስ ምንጭ የትርጉም ክፍለ ጊዜ ላይ ለራሳቸው ጥያቄ ሲመልሱ “የታሰረችበትን ገመድ እንደበጠሰች ጥጃ ይመሰላል” ብለዋል። “ከእስር ሲፈታ ዝምታን የመረጠው ጃዋር፣ ሰሞኑን ልጓሟ እንደወለቀላት ጥጃ እየቦረቀ ነው፣ ምን እስካሁን አንገቱን ሸብቦ እንዳያዘው የታወቀ ነገር የለም” ብለዋል።
ዶክተር ኢታና በበኩላቸው ዝምታው ጃዋር ከእስር ሲፈታ የገባው ውል እንደሆነ ጠቅሰዋል። በሽምግልና፣ በንግግር እሱና ሌሎች መፈታታቸውን እንደሚያውቁ የገለጹት የጃዋር የቅርብ ሰው፣ ጃዋር ግልጽ ያላደርገው ውለታ እንደነበረው፣ ይህን ድብቅ ስምምነት ይፋ ማድረግ እንደሚገባው ጠይቋል።
ተለጉሞ ጸጥታ ውስጥ ነበር። ምን ሆኖ ነበር? አይጽፍም ፣ አይናገርም ነበር። ለምን? ሲሉ ፖለቲከኛ ጠይቀዋል። ጃዋር ” ጥቁር ልበሱ” የተባለ ሰሞን ምክንያቱና ፍላጎቱ ግልጽ ያልሆነ ጭውውት ቢጤ ከደረጄ ኃይሌ ጋር አድርጎ ነበር። ጭውውቱ ናይሮቢ የተደርገ ሲሆን ደረጀ ጃዋርን እነከን አልባ፣ ተወዳጅና ድንቅ ፖለቲከኛ አድርጎ ነበር ያስተዋወቀው። በዚሁ ለስላሳ፣ ጃዋር ሊሞገትበት የሚገባቸውን ጉዳዮች ሆን ብሎ የዘለለና ጠያቂውን ትዝብት ላይ የጣለ ጭውውት ጃዋር ምን ተነጋግሮ ከስር እንደተፈታ አለመተንፈሱን ፖለቲከኞች ዘግየተውም ቢሆን እየተቹ ነው።
በተመሳሳይ ከአንድ ሌላ ሚዲያ ጋር ጭምት ስለመሆኑ ከመናገሩ ውጭ ሌላ የሚጠቀስ መረጃ ሳይሰጥ የቆየው ጃዋር “በዚህ በሁለት ሳስምንት ውስጥ ልክ እንደ ቮልካኖ ፈንድቷል። ምን ፈልጎ ነው” ለሚለው የፖለቲከኛው ጥያቄ ዶክተር ኢተና የቢዝነስ ኢምፓየሩን ለማስጠበቅ እንደሆነ አመልክተዋል።
የዶክተር ኢታና ሃብቴ ማብራሪያ ጃዋር በፍርድ ቤት የታገደበትን በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ማግኘት ባለመቻሉ መንግስትን ለማስገደድና ብሩን ለማስመለስ የፋኖና የትህነግ ኃይሎች ዳር ዳር የሚሉትን ህብረት ለመቀልቀል ማቀዱን ከሚናገሩት ጋር የሚመሳሰል ሆኗል።
እነዚህ ወገኖች ጃዋር ከአሁን ብሁዋላ በኦሮሞ ፖለቲካ ውስጥ አብቅቶለታል ባይ ናቸው። ጃዋርን አምኖ አብሮት የሚሰራ ኃይል ሊኖር እንደማይችል ጠቅሰው ብቻውን መቅረቱን አመልክተዋል።
በተደጋጋሚ ከጃዋር ጋር ቃለ ምልልስ በማድረግ የምትታወቀው ቤተልሄም ወይም ቤቲ ከወራት በፊት ነጽሃፏ ልካይ ተንተርሳ ባደርገችው ቃል ምልልስ ” ጃዋር መንግስት ይሆናል ብዬ አስቤ አላውቅም” በሚል ጀምራ ጃዋርን ” ቀበሮ መጣ” እያለ የውሸት የጩኸት ጥሪ ሲያሰማ ከነበረውና መንደረተኛው ጩኸቱን ሰምቶ ያገኘውን መስሪያ ይዞ ቀበሮ ሊያጠፋ ሲመጣ ” ውሸቴን ነው” ከሚለው እረኛ ጋር አመሳስላዋለች።
እረኛው በደበረውና ሙዱ በመጣ ቁጥር ኮረብታ ላይ እየወጣ ቀበሮ ሳይኖር “ቀበሮ መጣ” በማለት በተደጋጋሚ ሲጮህ፣ መንደረተኛው በተደጋጋሚ ግር ብሎ እየወጣ ውሸት መሆኑን ሲያረጋግጥ ተሰላቸና እውነተኛው ቀበሮ በመጣ ቁጥር እረናው “ኡ ኡ ድረሱልኝ፣ ቀበሮ በጎቹን ጨረሰ” ብሉ ቢጮኽ የተማረረው መንደፍረተኞቹ “ስራህ ያውጣህ፣ አንተ ውሸታም” በማለት ምላሽ ከለከሉት። ቀበሮውዎቹም በጐቹን ጨረሱዋቸው። ይህ ተረት ጃዋርን እንደሚገልጸው ቤቲ ጠቅሳ ጃዋር እንዳበቃለት አመልክታ ነበር።
ቤቲ ጃዋር ሲታሰር ወይም ቢታሰር ኦሮሚይ በተቃውሞ እንደምትቀጣጠል፣ የሰው አንገት እንደማይተርፍ ታስብ እንደነበር ጠቅሳ ወፍም አለመኖሩ ትናንት ዶክተር ሄኖክ እንዳለው፣ ቀደም ሲል ለጉዳዩ ቅርብ የርሆኑ እንዳሉት ቄሮ የጃዋር አደረጃጀት አካል እንዳልሆነ ማረጋገጫ ሆኗል። ቄሮ ዛሬ በኩታ ገጠም በአመት ሶስቴ እያመረተ እንደሚገኝም የሚናገሩ አሉ።
ከላይ ከተገለጹት ውጪ ያሉት ደግሞ ጃዋር ቀሪ ዕድሉ ፋኖዎችን መቀላቀል እንደሆነም እየተናገሩ ነው። ከቢቢሲ ጋር ባደረገው ስምምነት ላይ የተመሰረት በሚመስል “ጭውውት” ጃዋር ቅማንት፣ አገው፣ ቤኒሻንጉል ወዘውተ ነጻ አውጪ እያደራጀ፣ በሚዲያዎቹ የአየር ሰዓት ሰጥቶ እየቀሰቀሰ ሊያፈርሰው ሲሰራበት ለነበረው አማራ ክልልና የአማራ ህዝብ ተቆርቋሪ መስሎ በመቅረቡ፣ በአማራ ትግል ዙሪያ ያሉ አበባ እየረጩለት ቢሆንም ዓላማው የንግድ ኢምፓየሮቹን የማስጠበቀ መሆኑን ባልደረቦቹ ይፋ አድርገዋል።
ውብሸት ታዬ ተርጉሞ ባቀረበው የዶክተር ኢታና ቃለ ምልልስ ጃዋር በድርድር ከእስር እንደወጣ ደጋግመርው ያነሳሉ። ስለ ድርድሩ ጃዋር ትንፍሽ ያለው ነገር ባለመኖሩ የክህደት ስሜት መፈጠሩንም ያስታውቃሉ።
ኦቦ ሌንጮና ሌሎች በሽምግልናው ዙሪያ እንደነበሩ እውቀቱ እንደነበራቸው የገለጹት የዶክተር ኢታና “ጃዋር እንዲሁ አልተፈታም። በይቅርታ ሲፈታ ምን አደርጋለሁ ብሎ ነው የተፈታው” የሚል ጥያቄ በማንሳት ጃዋር ሊጠየቅ እንደሚገባ ይሞግታሉ። ሃያ ሶስት የሚታወቁና በፍርድ ቤት ክስ መዘገብ ላይ የቀረቡ የንግድ ተቋማት እንዳሉት ጠቅሰው ንግግሩ እነዚህን የንግድ ኢምፓየሮች የማዳን ሊሆን እንደሚችል ይናገራሉ።
“የኦሮሞ ፖለቲካ በየዋህነትና በቀናነት ብቻ የሚታይ ሊሆን አይገባም። የፖለቲካ ጮሌነት የሚባል ነገር አለ። ይህ ጮሌነት ህዝብ ልጁን እንዲገብር አስድርጓል። ጮሌዎቹ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አስችላቸዋል” ሲሉ ጃዋርን ጮሌ ያደረጉት ዶክተር ኢታና ” በድርድሩ ሂደት ማን ከምን ምን ተቀበል? የሚለው ጉዳይ ሊመረመር ይገባዋል.. ” ሲሉ ይጠይቃሉ።
“ብዙ ሚዲያዎች እያለባበሱ የሚያቀርቡት ቃለ ምልልስ መደበቂያ ነው። ያሉት የጃዋር የቀድሞ አጋር መደበቅ ሊቆም እንደሚገባ አበክረው ካስታወቁ በሁዋላ ” ዝም ብለው ለሚነዱት ሳይሆን፣ ማሰብ ለምትችሉ፣ መጠየቅ ለምትፈልጉ፣ መመርመር ለምትወዱና አቅሙ ላላችሁ ብቻ ሁሉ ጥያቄ አቀርባለሁ” ሲሉ ተደምጠዋል።
“ጥያቄው ህሊና ላለው ነው። ጥያቄውን የማቀርበው ለሚሞግተው ህዝብ ነው። እንጂ ለግሪሳው ዓይደለም” ብለው ደግመው ካስታወቁ በሁዋላ “ትላንት ልጆቻችንን የገበርንበት ጉዳይ ምን ሆነ ብላችሁ መርምራችሁ ታውቃላችሁ” ብለዋል። ዶክተር ኢታና አክለውም፣ ጃዋርን “ከእስር ቤት ከወጣህ በሁዋላ ያወጣኸውን አዲስ ዘፈን አቁምና እንደ አንድ የፖለቲካ መሪ የምትወስደው ኃላፊነት ምንድን ነው? ወይስ ተጠያቄነት የለብህም? በኦሮሞ ህዝብ ላይ የደረሰውን ሁሉ አስመልክቶ ምንድ ነው የአንተ ድርሻ?” ብለውታል።
እስር ቤት በነበረበት ወቅት የጻፈውንና አንድ በአዲስ ስታንሳርድ ላይ ተለጥፎ የነበረውን ጥሁፍ አንስትው “ጥፋቱን ሁሉ ሌሎች ላይ አላኮ እጅን አጣጥፎ ከደሙ ንጹህ ነኝ ማለት ወንጀል ነው” የሚል ትችት ዘርዝረውል። ለበጎው ነገር እውቅና በሚፈለግበት ደረጃ ለውደቀትና ኪሳራውም ኃላፊነት መውሰድ ግድ መሆኑን አመልክተዋል።
“እኔ ለምሳሌ ከ2018 በሁዋላ ተገኙ ለተባሉ ውጤቶች ድርሻ አለው ብዬ አምናለሁ። ስለዚህ ለተበላሸውም ነገር ኃላፊነት አለበት። በመሆኑም ለደረሱት ጉዳቶች ሁሉ አንድ ሁለት ተብሎ ኃላፊነት መውሰድ ድግ ነው” ሲሉ ጃዋር ሊጠየቅ እንደሚገብዋ ዶክተር ኢታና ተናግረዋል።
“በጎና መጥፎው ነገር ከተለየ በሁዋላ ቀጣዩ መንገድ ይቀየሳል እንጂ ውድቀቱን ጠቅልሎ ለሌሎች በመስጠት በጎውን ሁሉ ለራስ መውሰድ አግባብ አይደለም። ይህ ሳይሆን ቀርቶ አዲስ ዘፈን መዝፈን ዋጋ የለውም” በማለትም ጃዋርን ኮንነዋል።
“ለደረሱት ጉዳቶች ድርሻው ይለይ እንጂ የኦሮሞ የፖለቲካ ኤሊቶች ተጠያቂዎች ናቸው ይላሉ ዶክተር ኢታና። በዚህ እሳቤ ጃዋርም አለበት። ይህን የማይቀበል አመራር ለምንም ዓይነት ኃላፊነት አይበቃም። ኃላፊነት የሚወስድ ብቻ ነው መሪ የሚሆነው። የኦሮሞ ወጣቶች የሚከተሉትና ህዝብ አብሮ የሚሆነው ኃላፊነት ከሚሰማው መሪ ጋር ብቻ ነው” ሲሉ ጃዋር ኃላፊነት የማይሰማው፣ ለኃላፊነት የማይበቃ ንግዱን ብቻ የሚያሳድድ እንሽደሆነ አመልክተዋል።
“ሃላፊነት የማይወስድ ለራሱ፣ ለቤተሰቡ፣ ለብሄሩና ለአገር አይሆንም። ዕያንዳንዱን ጉዳይ አውቃለሁ; ይፋ አደርጋለሁ” ብለዋል ዶክተር ኢታና።
ጃዋር ከእስር እንደእወጣ የብልጽግናና የአብይ አሽከር ሆነ ይባል እንደነበር ዶክተር ኢታና አስታውሰው፣ ከእስር እንደተፈታ ጃዋር ዝምታን የመረጠው ጃዋር ጮሌ በመሆኑ እንደሆነ ገልጸዋል። “ጃዋር በጮሌነት ምን ባደርግ ነው ሃብት የማግበሰብሰው በሚል ስሌት ሲቀሳቅስ ነበር” በማለት በድፍረት ተናግረዋል።
ጃዋር የኃይል ሚዛኑንን በማስጠበቀ 23 የንግድ ድርጅቶችን ከፍቷል። ሲታሰር እነዚህን 23 ድርጅቶች ጥሎ ነው የታሰረው። ድርጅቶቹ ፍርድ ቤት በዝርዝር ችሎት ላይ ቀርበዋል። ማንም አይክድም፣ እኔም የፈጠርኳቸው አይደሉም” ያሉት ዶክተር ኢታና ይህ ያነሱት ጃዋር የንግድ ድርጅት ከፈተ ከሚል የክፋት እሳቤ ሳይሆን፣ የፖለቲካ መሪ ሆኖ ሳለ እነዚህን ድርጅቶች ለምን ተግባር ከፈታቸው የሚለው ጥያቄ መልስ ስለሚያስፈልገው እንደሆነ ዶክተር ኢታና አስታውቀዋል።
እነዚህን የንግድ ተቋማት ለማሳደግ የተኬደበት አግባብ ተጠያቂነትን ሊያስከትል እንደሚገባም በዝርዝር ትግሉን እንዴት እንደጎዱና ውሃ እንደደፉበት በማመላከት ተናግረዋል። ዛሬ ፊስ ቡክ ላይ ያለው ጩኸትና ይህ እውነት እንዳይነካ ለመከላከል የሚደረግ እንደሆነም ገልጸዋል።’
ጃዋር ‘ የቢዝነስ ኤምፓየሮችን ለማስጠበቅ እዛም እዚህም ጠጋ ጠጋ እንደሚል ያስታወቁት ዶክተር ኢታና፣ ቀደም ሲል “ኦሮሞ አንደኛ ሲል ነበር፤ ከዛም ኢትዮጵያ ማለት ጀመረ፣ አሁን ደግሞ ለፋኖ እየተከራከረ ነው ይህ ሁሉ መተጣጠፍ ማንነቱን ያሳያል” ብለዋል።
“ጃዋር በግልጽ ነግሮናል። ነጋዴ ነው የምሆነው ብሏል። እሱ ችግር የለውም ይህ ሁሉ ትርምስ የሚፈጠረውና የተፈጠረው ሃብት ለመሰብሰብ መሆኑ ወንጀል ነው” ሲሉ ባልደረባቸው ዶክተር ጸጋኤ አራርሳ ካሉት ጋር የሚዛመድ ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል።
የመንግስት ኃይል ከተዳከመ ኦሮሞ ጫንቃ ላይ እቀመጣለሁ። ኦሮሞን እገዛለሁ የሚል ህልምና ካልሆነም ሃብት የማሰባሰቡ ስሌት እገፋበታለሁ የሚል ሁለት ስሌቶችም ጃዋር ይዞ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ዶክተር ኢታና ከአልጸጸትም መጽሃፍ ህትመት ዜና ጎን ለጎን ይፋ አድርገዋል