በትግራይ ታጣቂዎችና የታጣቂዎች ከፍተኛ አመራሮች የሚሳተፉበት የተደራጀ ህገወጥ የወርቅ ንግድ እንደሚካሄድ በተለያዩ መገናኛዎች፣ ማህበራዊ ሚዲያ አውታሮችና የክልሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተደጋጋሚ በስፋት ሲያስታውቁ እንደነበር ይታወሳል። በክልሉ ጊዜያዊ መሪ አቶ ጌታቸውና በፌደራል መንግስት ደረጃ የዚህ ህገወጥ ንግድ ጉዳይ አሳሳቢነቱ ሲገለጽ መቆየቱ ይታውሳል። በተለይም ወርቅን ጨምሮ ማዕድናት በኤርትራ በኩል እንዲጋጋዝ መደረጉ ከአገር ኢኮኖሚና ጸጥታ ጋር እንደሚገናኝም ተመልክቶ ገድብ እንዲበጅለት ጥያቄ ሲቀርብ ነበር።በዚሁ ተደጋጋሚ ሮሮና ጥቆማ ይሁን በሌላ በግልጽ ባይገለጽም በወርቅ ማዕድን ቁፋሮ እና ዝውውር ዙሪያ መረጃዎች እንዲያሰባስቡና ሪፖርት እንዲያቀርቡ የተላኩ የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች ስፍራው ላይ ደርሰው መረጃ እያሰባሰቡ ባለበት ወቅት በታጣቂዎች መታገታቸውን ይፋ ሆኗል።
በስራ እያሉ የታገቱት የታገቱት ጋዜጠኞች ብዛት ሶስት መሆኑንን ገልጾ ያስታወቀው የትግራይ ቴሌቭዥን ነው። ጣቢያው ዜናውን ይፋ ሲያደርግ የታገቱት ሰራተኞች ሞባይላቸው ከአገልግሎት ውጪ እንዲሆን መደረጉንም አስታውቋል።
ትግራይ ቴሌቪዥን በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ከህገ ወጥ የወርቅ ማዕድን ፍለጋ እና ዝውውር ጋር ተያይዞ የሚነሳው ጉዳይ ለማጥራት የተሰማሩ ጋዜጠኞች መታገታቸውን ይፋ ሲያደርግ እንዳለው እገታው የተፈጸመው ከረፋዱ ሶስት ሰዓት አካባቢ ነው።
ታህሳስ 20/ 2017 ዓ.ም በአስገዳ ወረዳ ‘ ሜይሊ ‘ ተብሎ ከሚጠራ ልዩ ቦታ በምትገኘው መንደር ውስጥ መታገታቸውን አመልክቷል።
ጋዜጠኞቹ በአከባቢው ስላለው ህገ-ወጥ የወርቅ ማዕድን ቁፋሮና ዝውውር በማስመልከት በአካል ቦታው ድረስ በመሄድ የአከባቢውን ነዋሪዎች ፣ አርሶ አደሮችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ሲያነጋግሩ እንደሰነበቱ የገለፀው የትግራይ ቴሌቪዥን ” የጋዜጠኞች ቡድኑ በስራ እያለ በታጣቂዎች ሊታገት እና ሊታሰር ችሏል ” ብሏል።
የታገቱት የጋዜጠኞች ቡድን ከረፋዱ 4:00 ጀምሮ ሞባይላቸው ከአገልግሎት ውጪ በመደረጉ ምክንያት ያሉበት ሁኔታ እና ድህንነታቸው ማረጋገጥ እንዳልተቻለ አስታውቋል።
ጋዜጠኞቹን የሚመለከት መረጃ ለመጠይቅ በአከባቢው ለሚገኙ የመንግስት አመራሮች ተደጋጋሚ የስልክ ሙከራ ቢያደርግም እንዳልተሳከለት የትግራይ ቴሌቪዥን ባሰራጨው ዜና ይፋ አድርጓል። በዘገባው እገታውን ስለፈጸሙ ታጣቂዎች ማንነት በዝርዝር የተባለ ነገር የለም።
ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቃዎች የታገቱት ሦስት የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን አስገደ ወረዳ ሜይሊ ተብሎ በሚጠራ ቦታ በሚገኝ እስር ቤት እንደሚገኙ የትግራይ ቴሌቪዥን ማረጋገጡን አስታውቋል። መታሰራቸውን ቢያረጋግጥም አሁንም ያሰራቸውን ክፍል በስም አልጠራም።
ጋዜጠኞቹ ከህገ-ወጥ የወርቅ ማዕድን ፍለጋ፣ በአካባቢው ህዝብ ላይ ከኬሚካል ጋር በተያያዘ ስለተፈጠረው ስጋት ለማጥራትና መረጃ ከህዝብና ከሚመለከታቸው ወገኖች ለማሰባሰብ በሚል ወደ ስፍራው የተላኩት ሪፖርተሮች፣ ሜይሊ ተብሎ በሚጠራ ቦታ በሚገኝ እስር ቤት እንደሚገኙ የትግራይ ቴሌቪዥን ከደቂቃዎች በፊት ማረጋገጡን ያስታወሰው ቲክቫህ መጨረሻ ላይ “ሰማሁ” ብሎ እንደዘገበው ከእስር ሊለቀቁ ችለዋል።
የጋዜጠኞቹ መፈታት በማስመልከት ለቲክቫህ እንደጻፈው ጋዜጠኞቹ መረጃ በማሰባሰብ ስራ እያሉ የተያዙት በአከባቢው በሚገኙ ፓሊስ እና ሚሊሻዎች ነው። ከወረዳው የፀጥታ እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት መካከል በተደረሰ መግባባት ከሰዓታት እስር ሊለቀቁ እንደቻለ ተመልክቷል።
ጋዜጠኞቹ በአከባቢው ያለውን ህገ-ወጥ የወርቅ ማዕድን ቁፋሮና ዝውውር የሚመለከት የምርመራ ዘገባ በመስራት ላይ እንደነበሩ ለወረዳው የፀጥታ እና አስተዳደር አካላት የተናገሩ ሲሆን የጋዜጠኞች እስር እና እንግልት በክልሉ ካለው የፓለቲካ ቀውስ ጋር ቀጥተኛ ትስስር እንዳለው ተጠቁሟል።
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring