ኢትዮሪቪው – “ቱጃሩ” ሲሉ ጃዋርን የሚጠሩት የሚያውቁት ናቸው። ህዝብ ባለቀበት የኢሬቻ በአሳል ላይ “down down moyane” በሚል ሲያዘምር የነበረና ግብጽ እንደነበር የሚነገርለት ወጣት ወንድም እንደሚያንቀሳቀሰው የሚነገርለት የጃውር ሃብት ሰፊ ምርመር እንደሚያሻው በስፋት ጥቆማ መቀርብ ከመመረ ቆይቷል። ባልደረቦቹን ጨምሮ የጃዋርን ሃብት ውስጥ ውስጡ ከሚፈትሉት በቀር በገሃድ ለማጋለጥ አልደፈሩም። ሰሞኑንን ግን ዶክተር ጽጋሬ አራርሳ “ሌባ” ሲሉ የትግል አጋራቸውን አራክሰው ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ጃዋር ኦህዴድ ከትህነግ ጋር የውስጥ ለውስጥ ትግል ሲያካሂድ ሚዲያውን እንዲመራ ከተመለመለ በሁዋ አጋጣሚውን ተጠቅሞ የድርጅቱን መዋቅር እንደመነተፈና “መንግስት ነኝ” ለማለት መዳፈሩን የሚጠቅሱ ጃዋርን በሌብነት ብቻ ሳይሆን በፖለቲካም ግልሙትና ሲከሱት ቆይተዋል። ። ቄሮን የራሱ ኃይል አድርጎ ሲጠራ ቢቆይም ሲታሰር ቄሮ ዝም በማለቱ በርካቶች መጨረሻ ላይ መልስ አግኝተዋል። በትግል ወቅት አብረው ነዳጅ ሲያረከፈክፉ የነበሩት ዶክተር ሄኖክ ገቢሳ ሰሞኑን “ቄሮ የኦህዴድ መዋቅር ነበር” ሲሉ መስክረዋል። የጃዋርን ከዝምታ በሁዋላ ዳግም መወራጨት ፖለቲካዊ ውንብድና ዓይነት መሆኑንንም ገልጸዋል።

አጠገቡ የነበሩትን በሙሉ አራግፎ ብቻውን የሆነው ጃዋር አሁን ላይ ከየአቅጣጫው ዘመቻ ተከፍቶበታል። አንድም ቀን በሚሞግተው ሚዲያ ቀርቦ ቃለ ምልልስ ያላደረገውና ቢጠየቅም ፈቃደኛ የማይሆነው ጃዋር ሰሞኑንን በቢሲ ውይይት መሰል የተናበበ ቃለ ምልልስ ማድረጉን ተከትሎ ለሚሰነዘሩበት ወቀሳዎች እስካሁን በግልጽ ምላሽ አልሰጠም። በአገር ውስጥና በውጭ አገር ውድ ዋጋ ያላቸው ቤቶችና ድርጅት እንዳለው መረጃ የሚወጣበት ጃዋር ወደ ፖለቲካው ለመመልስ ቢንደርደርም በአብዣኛው ስንብቱ መቃረቡን እየገለጹ ነው። ኢትዮጵያ ፖለቲካ እንዲጋልብ ከግብጽ ጋር ቀጥታ ግንኙነትና ድጋፍ እንዳለውም በይፋ መረጃ የሚከሰሰው ጃዋር መጨረሻው አነጋጋሪ እየሆነ ነው። ዶክተር ሄኖክ ገቢሳ ” የወንድማቸን መጨረሻው ያሳዝነኛል” ሲሉ በምጸት ይህንኑ ያረጋገጡ የቅብ ወዳጁ ሆነዋል።
ሰሞኑንን “አልጸጸትም” የሚል መጽሃፍ መጻፉን ይፋ ካደረገ ወዲህ በማህበራዊ ሚዲያ ከፍተኛ ዘመቻ የጀመረው ጃዋር መሐመድ ያልጠበቀው ዘመቻ ተከፍቶበታል። በሌብነት፣ በክህደትና በዳግም የፖለቲካ ውንብድና እየተከሰሰ ነው። በግል አሉት የሚባሉ ሃብቶችም ይፋ እየሆኑበት ነው። በተለይም ዶክተር ጸጋዬ አራርሳ በህግ ሊጠየቅ እንደሚችል ጠቅሰው መረጃ ሰጥተዋል። ዶክተር ሄኖክ ገቢሳም ዘልፈውታል።
ቀደም ሲል ከጃዋር ጎን ሆነው መንግስትን፣ በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትሩን ያለማቋረጥ ሲዘልፉ ከነበሩት መካከል አንዱ የሆኑት የህግ ባለሙያው ዶክተ ሄኖክ ገቢሳ ርዕዮት ከሚባለው የትግራይ ፖለቲካ አቀንቃኝ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ሰፊ ቃለ ምልልስ ጃዋርን “ድጋሚ የማይሆን ቃል የገባ አሳዛኝ ሰው ” ሲሉት ተደምጠዋል። አሁን ላይ መንግስት ሊያናጋና ሊገለብጥ የሚችል ኃይል መሬት ኦላይ እንደሌለውም “እርግጠኛ ነኝ” ሲሉ አስታውቀዋል።
የርዕዮት ሚዲያ አዘጋጅ አአቅጣጫ በሚያሲዘው ቃለ ምልልሱ ዋና እንደምታው ሌላ ቢሆንም፣ ዶክተር ሄኖክ ገቢሳ ጃዋር ሊሳካለት እንደማይችል አብረው ሲሰሩ የሚያውቁት በርካታ መረጃ እንዳላቸው በመግለጽ ተናግረዋል። ” እውነቱን ልንገርህ” በማለት ” በኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ላይ መንግስት መገልበጥ የሚችል የተደራጀ ትግል የለም” ሲሉ ተደምጠዋል። ኦህዴድን አስመልክቶ ከጠያቂው ጋር ሰፊ ክርክር የገቡት ዶክተር ሄኖክ ” ይቅርታ ለቃሉ፣ ኦህዴድ ያልተማሩ ስብስብ ነው፣ የትህነግ ዓላማ አስፈጻሚ የነበረ ቡድን ነው፣ በስልጣን ላይ አካሉ እንጂ አቅሙና መወሰን የሚያስችል ኃል አልነበረውም” ሲሉ ጠያቂው ትህነግን ለመከላከል ያደረገውን ሙከራ መክተዋል። ባለፉት ሰላሳ ዓመታት በኦሮሞ ህዝብ ላይ የተፈጸመውን ግፍም ዘርዝረዋል።
ትህነግን የኦሮሞ ወዳጅና አጋር አስመስሎ ለማቅረብ በሚጥረው ጥያቄና መልስ ውስጥ የሚቀበሉትን እየተቀበሉ፣ ሳይመስላቸውም መልሰው እየጠየቁ፣ አንዳንዴም ጠንካራ መከራከውሪያ የሚሆን ማስረጃ እያቀረቡ ረዥም ቆይታ ያደረጉት ዶክተር ሄኖክ “ኦህዴድ ያለፉትን ሰላሳ ዓመታት ተጠቅሞበታል። ዛሬ ላይ ድሮን የሚያመሩት ምጡቅ ልጆች አምርቷል” ሲሉ የድሮውና የአሁን ኦህዴድ ልዩነት እንዳላቸው አመልክተዋል።
ጃዋርን አስመልክቶ ጠያቂው “ጃዋር አይሳካለትም እያልክ ነው?” ሲል ለጠየቀው ዶክተር ሄኖክ ” አዎ” በማለት ጃዋር በድጋሚ አጉል ተስፋ የሚሰጥ ትግል ውስጥ መግባቱን በማመላከት ተናግረዋል። አያይዘውም ብልጽግና ቢወገድ አገሪቱ ውስጥ ምን ዓይነት መንግስት፣ በእነማን አማካይነት፣ እንዴት እንደሚመሰረትና ምን እንደሚደረግ የሚያስረዳ አንዳችም ዝግጅት አለመኖሩን አስረድተዋል። ይህን ጊዜ ጠያቂው “ኢትዮጵያ ትበታተናለች” ሲሉ የተለመደውን የትህነግን ማስፈራሪያ አቅርቦ ጥያቄና መልሱን ለማስኬድ ሞክሯል። ይህን ጊዜ ዶክተር ሄኖክ ” በእኛ ዕድሜ ለውጥ ይኖራል ብዬ አላስብም” ሲሉ ከጠያቂው ምኞትና ፍላጎት ውጪ ሆነው መልሰዋል።
ጠያቂው ” … በኛ ዕድሜ ለውጥ አናይም እያልክ ነው? ብልጽግና …” ሲል ደረቅ ፈገግታ በማሳየት ሞገተ። ዶከተር ሄኖክ ገቢሳ ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሊቀየሩ መሪዎች ሊቀያየሩ እንደሚችሉ አመላክተው በአቋማቸው ሲጻኑ “ብልጽግና ያለ አብይ?” በሚል ጠያቃዊ ሳቀና …. ።
ጠይቂው የኦሮሞ ልሂቃን አሁን ላይ ዝምታን መርጠዋል። በዚህም እየተወቀሱ ነው። ይህ ለምን ይሆናል? ድምጻቸውን ልክ ከለውጡ በፊትና የለውጡ መጀመሪያ ዓመታት ሲያደርጉ እንደነበረው ማሰማት ይገባቸዋል። ብልጽግና የኦርሞን ህዝብ በድሮን እየጨረሰ ነው። በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ታስረዋል ወዘተ የሚሉ ትግልን የማነሳሳት አጀንዳ ለመትከል ያለመ ጥያቄ ቢያነሳም ዶክተር ሄኖክ በአንዳንዶቹ ጉዳዮች ድጋፍ እየሰጡ አንዳንዶቹን ጉዳዮች የጠያቂውን ፍላጎት በተረዳ መልኩ እየመከቱ ቆይታቸውን ጨርሰዋል።
አሁን ላይ በኦሮሚያ ያለው መንግስት የኦሮሞ መሆኑን ። እንደቀድሞው ከሁዋላ ሆኖ የሚነዳው እንደሌለ በመግለጽ የቀደመውንና የአሁኑን መንግስት ልዩነት ቢያስረዱም በርካታ ችግር እንዳለ ግን ” የግል አስተያየቴና ምልከታዬ ነው” ሲሉ ተናግረዋል። በሙያቸው የህግ ሰው የሆኑ ዶክተር ሄኖክ ኤሊቱ የሚባለው ክፍል “ለምን ተኛ” በሚል በተደጋጋሚ የቀረውን ልዩ ጥያቄ ” እኔም ጥያቄው አለኝ” በማለት አልፈውታል።
ሌላው የህግ ባለሙያ ዶክተር ጸጋዬ አራርሳ ጃዋር ላይ ያሰሙት የሌብነት ወቀሳ አንድም ቀን አብረው የሰሩ እስከማይመስል ድረስ የመረረ ነው። ጃዋር የሰብሰበውን ገንዘብ በሙሉ የት እንደከተተው ሊያስረዳ እንደሚገባ የጠየቁት ዶክተሩ ፣ ጃውር በዶላር ጭምር በብዙ ሚልዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ሰብስቦ ለኦሮሞ ህዝብ የሰራው አንዳችም ነገር እንደሌለ አመልክተዋል።
ኦ ኤም ኤን በሚባለው ሚዲያ ስም ሰፊ ሃብት መሰብሰቡን ዘርዝረው ይህ ሃብት የት እንደገባ በህግ አግባብ በተቋቋመበት አገር አሜሪካን ህግ መሰረት ጥያቄ እንደሚቀርብ አመልክተዋል።
በበርካታ የሌብነትና የማጭበርበር ወንጀል ጃዋርን የከሰሱት ዶክተር ጸጋዬ፣ ከህዝብ በሕብ ስም የተሰበሰበ ሃብት ውጦ ዝም ማለት እንደማይቻል ተናግረዋል። እየተከፈላቸው ከጃዋር ስር የሚያተፈትፉትን “ዝምቦች” ሲሉ የጠሩዋቸው ዶክተር ጸጋዬ አራርሳ፣ “ዝምብ ቆሻሻ ስር ነው የምትገኘው” ሲሉ አካሄዳቸው እንደማያዋጣቸው መክረዋል።
የኦሮሞ ህዝብ በተፈጥሮና ሰው ሰራጭ ችግሮች ሲሰቃይ የነበረባቸውን አካባቢዎች በመዘርዘር ጃዋር ለአንድ ሰው እንኳ ምንም ዓይነት ድጋፍ እንዳላደረገ ያስታወቁት ዶክተር ጸጋዬ፣ “ሁሉን እናውቃለን፣ እናጋልጣለን” ብለዋል።
ጃዋር “አልጸጸትም” የሚል መጽሃፍ መጻፉን ተከትሎ፣ ዶክተር ጸጋዬ በይፋ ባሰሙት ክስ ላይ “ጃዋርን እንጠብቀው፣ እንከልለው” የሚል አቋም ሲያራምዱ የነበሩ መኖራቸውን ይፋ አድርገዋል። ይህን ሲያደርጉ የነበሩትም በመንደረተኝነት፣ በስፈር ልጅነትና በክፍያ እንደሆነ አጋልጠዋል።
በውጭ አገር ያሉ ድጋፍ ሰጪ እንጂ ታጋይ እንዳልሆኑ ያመለከቱት ዶክተር ጸጋዬ፣ አገር ቤት ላለው ትግልና ህዝብ ድጋፍ ሳይውል በተቀረጠፈ ገንዘብ ዙሪያ ዝም ሊባል እንደማይገባ ሲጠቁሙ “በህዝብ ስም የሰበሰብከውን ገንዘብ በስሙ ለለመንክበት ህዝብ ታደርሳለህ ወይስ ቀርጥፈህ በልተህ ዝም ትላለህ?” በሚል ጥያቄ በማቅርብ ነው። ቦረና፣ጉጂ፣ አርሲ፣ ወለጋ ወዘተ ህብዝ መከራውን ሲያይ አንድም እርዳታ እንዳልተደረገ በማውሳት ይህ ወንጀል መሆኑንን አመልክተዋል።
ጃዋር ከእስር ሲፈታ የስልጣን ጥያቄ የያዘ ዝርዝር ፕሮፖዛል አቅርቦ እንደነበርና መንግስት ውድቅ እንዳደረገው በተደጋጋሚ የሚነገረውን ሲያጸኑ ዶክተር ጸጋዬ አራርሳ ” ሌባ ጀግና ይባላል፣ ከህዝብ ላይ እየዘረፉ የሚኖሩ ጀግኖች ተብለው ይወደሳሉ” ካሉ በሁውላ ጃዋር እሳቸውን ጭምር በስልጣን ለማማለል አስቦ እንዴት እንዳታለላቸው አመልክተዋል።
ከመንግስት ጋር መነጋገሩ ጠቅሶ ዶክተር ጸጋዬ አራርሳን መንግስት የጠቅላይ አቃቤ ህግ ወይም የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት የማድረግ ዕቅድ እንዳው እንደነገራቸው አመልክተዋል። እሳቸው ስልጣን ከሚሰጣቸው መካከል አንዱ እንደሆኑ አድረጎ ይወሰውሳቸውና የድለላ ስራ ይሰራ እንደነበር አመልክተዋል።
አክቲቪስ ምናምን የሚባሉት ሁሉ ለጥቅም ሲሉ ከሚርመጠመጡበት የሌብነት ማጥ ውስጥ እንዲወጡ ያስጠነቀቁት ዶክተር ጸጋዬ አራርሳ “እንከባበር” ሲሉ ተድምጠዋል። ሌሎች በስፋት በዚህ ዙሪያ እንደሚናገሩም ቃል ገብተዋል።