“የጁባላንድን ባለስልጣናት ያሳፈረ አውሮፕላን እንዲመታ ትዕዛዝ ተሰጥቶ ነበር” ሲሉ የጁባላንድ ደኅንነት ሚኒስትር ዩሱፍ ሁሴን ኦስማንን ጠቅሶ ኤኤፍፒ ዘገበ። ይህንኑ ትዕዛዝ ተከትሎ የኢትዮጵያ ጦር እርምጃ መውሰዱን ሳይገልጽ በደፈናው የሶማሊያ መንግስት የኢትዮጵያን መንግስት የከሰሰበትን መግለጫ አሰራጭቷል።
የኢትዮጵያና የሶማሊያ ባለስልጣናት የአንካራውን ስምምነት ለማጠንከር አዲስ አበባ እየመከሩ ባለበት ወቅት ጁባላንድ ዳውሎ ከተማ በተፈጠረ ጥቃት የሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ” የኢትዮጵያ ኃይሎች በሶማሊያ ብሔራዊ ጦር ላይ ጥቃት አድርሰዋል” ሲል ያሰራጨውን መግለጫ ኢትዮጵያ ስምምነቱ እንዳይጸና የሚመኙ አካላት የፈጠሩት ተራ ክስና አሉባልታ እንደሆነ ስትል አጣጥላዋለች።
አጋጣሚውን አስመልክቶ የጁባ ባለስልጣናት “በሥፍራው የሚገኙት የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ጣልቃ የገቡት ባለሥልጣናትን ለመጠበቅ ነበር” ማለታቸውን ኤኤፍፒ ከስፍራው ዘግቧል። የሶማሊያ መንግስት ኤኤፍፒ ለዘገበው ዘገባ ማስተባበያም ሆነ ተቃውሞ በመግለጫው አላካተተም። የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል በጁባ ላንድ መስፈሩ ይታወሳል።
ዘገባው አክሎ የጁባላንድ ደኅንነት ሚኒስትር ዩሱፍ ሁሴን ኦስማንን በዱሎው የሰጡትን ጋዜጣዊ መግለጫ ጠቅሶ እንዳለው “ክስተቱ የተፈጠረው (የፌዴራል) ኃይሎች የጁባላንድ ግዛት ልዑካንን የጫነች አውሮፕላን መትተው እንዲጥሉ ትዕዛዝ መሰጠቱን ተከትሎ ነው” የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባወጣው መግለጫ ጥቃቱን የኢትዮጵያ ኃይሎች መሰንዘራቸውን ከማስታውቁ ውጭ ምክንያቱን አላብራራም።
ሃሰን ሼክ የሚመሩት የሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት ከፊል ራስ ገዝ ከሆነችው ጁባላንድ ጋር ግጭት ውስጥ መግባታቸው የሚታወስ ነው።
የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰኞ አመሻሽ ላይ ባወጣው መግለጫ ዱሎው በተባለችው የጁባላንድ ከተማ የኢትዮጵያ ጦር ጥቃት ፈጽሞ ጉዳት ማድረሱን አመልክቷል። የኢትዮጵያ ኃይሎች ምንም ዓይነት ትንኮሳ ሳይደረግባቸው ዱሎው በሚገኘው የሶማሊያ ብሔራዊ ጦር መቀመጫ ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ያመልከተው መግለጫው የጉዳቱን መጠን አልገለጸም ።
መግለጫው ጥቃቱ የታቀደ ነው ብሎታል። ሲያብራራም ጥቃቱ ሶስት ቁፍል የሶማሊያ ጦር፣ የብሔራዊ ደኅንነት ኤጀንሲ እና የሶማሊያ ፖሊስ ኃይል መቀመጫዎች ላይ መፈጸሙን አመልክቷል።
በጥቃቱ የሶማሊያ ኃይሎች ሙትና ቁስለኛ መሆናቸውን፣ በአካባቢው ያሉ ነዋሪዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው አትቷል። የጥቃቱ መጠን አልተብራራም።
መግለጫው አክሎ የሶማሊያ መንግሥት በአንካራ ስምምነት መሠረት የሰላም ሂደቱን ለማጠናከር እየሰራ ባለበትና ከፍተኛ ልዑክ ወደ አዲስ አበባ ባለከበት ወቅት ጥቃቱ መፈርጸሙን ጠቅሶ ወንጅሏል።
የሶማሊያ የፌደራል መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዲሴምበር 23 ቀን 2024 ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት ማዘኑን አስታውቀ። በሶማሊያ ዶሎው ከተማ ተከሰተ ለተባለው ጉዳይ አስመልክቶ በኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ የቀርበውን ክስ ተራ ወሬ ወይም ትክክኛንተ የሌለው ውንጀላ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።

ክስተቱ የተቀሰቀሰው በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል የተጀመረውን ግንኙነት ለመቦርቦር ባሰቡ አንዳንድ አካላት ነው የተፈጸመ እንደሆነ መግለጫው አስታውቋል። መግለጫው እነዚህ ሶስተኛ ወገኖች የአፍሪካ ቀንድን ለማተራመስ ዓላማ ያላቸው እና የቀጣናው ሰላም ዘላለማዊ ጸሮች መሆናቸውንም አክሏል።
በአንካራው ስምምነት እንደተመለከተው የሁለቱ ሀገራት የተጀመረርውን የሰላም ቁርጠኝነት ለማሰናከል ለሚንቀሳቀሱ አካላት መመቻቸት ወይም ፈቃድ መስጠት እንደምይገባቸው መግለጫው አትቷል። የኢትዮጵያ መንግስት ተመሳሳይ አደጋዎችን ለመከላከል ከፌዴራል መንግስት የሚመለከታቸው አካላት ጋር ተባብሮ እንደሚሰራም ገልጿል።
“ኢትዮጵያ በአንካራ ዲክላሬሽን መንፈስ የሁለቱን ሀገራት ወንድማማችነት ግንኙነት ለማደስ እና ለማጠናከር ያላትን ቁርጠኝነት ከፍ አድርጋ ትጠብቃለች። የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ቁርጠኝነት እና ድፍረት የሁለትዮሽ አጋርነት እና ሰፊ ቀጠናዊ ትብብርን አጠናክሮ ይቀጥላል” ይላል የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ
ታህሳስ 24 ቀን 2024 አዲስ አበባ