“አምባገነንነትን አጥብቀው የሚወዱት ኢሳያስ ምርጫንም ሆነ የህግ የበላይነትን እምቢኝ እንዳሉ ወንበራቸው ላይ አርጅተዋል ” ይላል የመንግስት ልሳን የሆነው ፋና ቲቪ ኢሳያስ አፉወርቂ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰላ ትችቱን ሲያሰማ።
ፋና ቴሌቪዥን በኤርትራው የዕድሜ ልክ ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ላይ ” የአስመራው መንግሥት ነገር – የራሷ አሮባት ” በሚል ርዕስ ይፋ ያደረገው ዘገባ መነጋገሪያ ከመሆን አልፎ ውስጥ ውስጡን ሲነገር የነበረውን የሁለቱን አገሮች ግንኙነት ደረጃ ያመላከተ ሆኗል።
ለፋና ዘገባ መነሻ የሆነው ሰሞኑን ኢሳያስ አፉወርቂ በአገራቸው ሚዲያ ኢትዮጵያን አስመልክቶና መላው ዓለመን የዳሰሰ ትንተናቸውን ተከትሎ ነው።
ለኤርትራ ሕዝብ ህገምንግስት፣ ምርጫና ዴሞክራሲ እንደማያስፈልገው በአልጀዚራ በኩል በይፋ የተናገሩት የኤርትራው መሪ፣ ህገመንግስት፣ የዴሞክራሲ ተቋማት፣ ምርጫና የሚታወቅ ካቢኔና ነሳ ፕሬስ የለኤለባት፣ ሰዎች እምነታቸውን በነሳነት የማያራምዱባትን ጨለማ አገር እየመሩ ስለ ኢትዮጵያ ህገመንግስት መዘላበዳቸው በርካቶችን አስገርሟል።
ኢሳያስ በተለይ ከፕሪቶሪያው ስምምነት መፈረም በሁዋላ ” ስምምነቱ ትክክል አይደለም” በሚል በግልጽ የተቃወሙ ሲሆን በአሁኑ ዲስኩራቸው ” አያገባንም” ለማለት ሞክረዋል። በስምምነቱና ኢትዮጵያ የባህር ባለቤት መሆነ እንዳለባት በግልጽ አቋሟን ይፋ ካደረገች በኃላ ኤርትራ በገሃድ ከኢትዮጵያ ተላቶች ጋር መተባበሯን በይፋ አስታውቃለች። ፋናም በዚህ በተከማቸ ተደርራራቢ የኢሳያስ ሰነድ ላይ ሲመከሮ ቆይቶ ዝምታውን ሰብሯል»
” በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ያለውን እጅግ የሻከረ ወቅታዊ ሁኔታ ያሳያል ” የተባለለትን ዘገባ ይፋ ያደረገው ፋና ኢሳያስን በቡዙ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ችግር ውስጥ የተዘፈቀችውን የራሳቸውን ሀገር ረስተው ስለ ሌሎች ሀገራት እና ስለ ኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ፈተፋች መሂናቸውን ነግሯቸዋል።
“ኤርትራ በህገመንግስት መተዳደር ብርቅ የሆናባት ሀገር ናት። ይህ ሆኖ እያለ ህገመንግስት ያላትን ኢትዮጵያን መተቸታቸው አስገራሚ ነው” ሲል በፕሬዚዳንት ኢሳያስ ላይ የተሳለቀው የፋና ዘገባ፣ አንድ አምስተኛውን ህዝባቸውን ስደተኛ ያደረጉ ኢሳያስ በሰው ሀገር ጉዳይ በመፈትፈት የሚስተካከላቸው እንደማይገኝ አመልክቷል። ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ ከኤርትራ ከሰላሳ ሺህ በላይ ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው የሚታወስ ነው። በጥቅሉ አዲስ አበባ ብቻ በመቶ ሺህ የሚቆተሩ ኤርትራዊያን ስደተኞች ያለ አንዳች መድልዎ እንደሚኖሩ ይታወቃል።
ኤኢሳያስን አምባገነንት ሲያሳይ “ላለፉት 30 ዓመታት በላይ ያለ ምንም ተቀናቃኝ ኤርትራን የገዙ” ሲል የፈረጃቸው ፋና፣ “ኢሳያስ መንግሥታቸው ህገመንግስት ፣ ምርጫ ፣ ነጻና ገለልተኛ የዴሞክራሲ ተቋማት የሚባል ነገር አያውቅም ፤ ፍላጎትም የላቸውም። ደግሞ አፋቸውን ሞልተው ይህንኑ ይናገራሉ” የትዝብት ጅራፉን አውርዶባቸዋል።
ፋና ኢትዮጵያ ቢያስወቅስም ምርጫ የምታካሂድ አገር፣ ምርጫን የሚያካሂድ ተቋም፣ ምርጫ እንዲካሄድ የሚያስገድድ ህገመንግስት እንዳላት ለሰሚው ትቶ እንዳለው “ምርጫም ሆነ ተቀናቃኝ እንዳይኖር ለሶስት አስርት ዓመታት አፍነው እያስተዳደሩ ፣ በኢኮኖሚም ሆነ ፖለቲካም ከዓለም ኋላ ስለራቀች ሀገራቸ ኤርትራ መናገር ነውር ጉዳይ አድርገውታል” ሲል ለምን “የራሷ አሮባት” የሚል እርዕስ እንደመረጠ ገልጿል።
አልሸባብን አስመራ ሸሽገው በውክልና ሲያሰለጥኑና ሲያስታጥቁ እንደነበር በመረጃ የሚከሰሱት፣ በዚሁ ተግባራቸው ማዕቀብ ተትሎባቸው የነበሩት ኢሳያስ ለሰላም ደንታ ቢስ መሆናቸውን ፋና ሲያስታውቀ፣ ለቀጠናዊ ሰላም እና ትብብር ጆሮ የማይሰጡት፣ በቀጠናው ሰላም መደፍረስ ጣታቸውን ኢትዮጵያ ላይ የሚቀስሩ። የህገመንግስት አስተዳደር የሌላቸው፣ መሆኑን አመልክቶ ነው የኢትዮጵያን ህገመንግስት ለመተቸት መዳፈራቸውን ያተተው»
“ኤርትራ ህገመንግስት ካፀደቀች ሩብ ክፍለዘመን ቢሆናትም አምባገነንነትን አጥብቀው የሚወዱት ኢሳያስ ከመሳቢያቸው ስር ሽጉጠው ምርጫንም የህግ የበላይነትንም እምቢኝ እንዳሉ ወንበራቸው ላይ አርጅተዋል” ሲል ግምገማውን በማያስያ ያሰፈረው የፋና ዘገባ ይፋ በሆነ በደቂቃዎች ውስጥ በማህበራዊ ሚዲያዎች በስፋት የግብዣ ያህል ” ይስሙት” እየተባለ ተሰራጭቷል።
“ህገመንግስት የሌላቸው ሰው የኢትዮጵያ ህገመንግስት ላይ አስተያየት መስጠታቸው ስላቅ ይሆናል” ሲል ኢሳያስን ዘርጥጦ የተላለፈው ዘገባ፣ “አምባገነኑ ኢሳያስ በህግ ለመተዳደር፣ ለህጋዊ ጉዳዮች፣ ለህገመንግስት ባዕድ ናቸው” ሲል ከዘመኑ የራቁ እንደሆነ አመልክቷል።
ፋና በመደጋገም “አምባገነኑ ኢሳያስ” እያለ የጠራቸውን ኢሳያስን “የጎረቤቶቻቸው አገራት በህግ መመራት፣ የራሳቸውን ድካም የሚያጋልጥባቸው ይመስላቸዋል። ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ የሚያደረጉ የጎረቤት ሀገራትን አይወዱም” ሲል ጥላቻቸውና ሴራቸው ከስጋት እንደሚመነጭ ጠቁሟል።
ውስጥ ውስጡን ሲብላላ የነበረውን ዋና ጉዳይ አፍርጦ ” ኢሳያስ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠን መንግስት ለማወክ ከጀርባ ታጣቂ አሰልጥነው የሚልኩ መሆናቸውን ቴሌቪዥን ላይ ሲቀርቡ ይረሱታል” ሲል ይፋ ያስታወቀ ፋና፣ ” ኢሳያስ ራሳቸውን የቀጠናው ጠበቃ፣ ሰላም ወዳድ አድርገው የብልጣ ብልጥ ጨዋታ ይጫወታሉ” ሲል ፋና “ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ”ን ገሃድ አውጥቷል።
“ኤርትራን እንደ ሲንጋፖር አደርጋለሁ የሚለው ቅዠት ወደ ተግባር መለወጥ ሲያቅታቸው፣ የናቋት ጎረቤታቸው ኢትዮጵያ በየዓመቱ 8% በላይ እድገት እያስመዘገበች በኢኮኖሚ የቀጠናው ቁንጮ መሆኗ ቅናት ውስጥ ከቷቸዋል” በማለት በንፅጽር ሁለቱን አገራት ያወዳደረው ፋና፣ ኢትዮጵያ ዜጎቿን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ከማድረግ አልፋ ምስራቅ አፍሪካን በኃይል እያስተሳሰረች ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገራት የአፍሪካን ሁለተኛ ኢኮኖሚ ለመገንባት እያደረገች ያለውን ጥረት ለማራከስ መሞከራቸው የቅዠታቸው መነሻ ማዕከል መሆኑንን አሳይቷል።
ፋና ኢሳያስን ሲያሳጣና፣ ለኤርትራዊያን ፍርድ አንገዋሎ ሲሰታቸው፣ “ኢሳያስ ድፍን 30 ዓመታት የመሯት ሀገር ከ30 ዓመታት በፊት በተገነባ መሰረተ ልማት እየኖሩ ነው” በማለት ነው። ከለውጡ በሁዋላ ኤርትራ ደርሰው የተመለሱ በሰቱት ምስክርነት ኤርትራ እንዳለች ናት። በወጉ እንኳን ቀለም አልተቀባችም። አዳዲስ ፕሮጀክት ብሎ ነገር የለም። ሱቆቿና የገበያ ቦታዎቿ በሙሉ የደነዘዙ ናቸው የሚሉ አስደንጋጭ ምስክርነት ሲሰጡ እንደነበር ይታወሳል። ወታቶች መንገድ ላይ እንደማይታዩም ሲገልሱ ነበር። ፋና ይህን ባይዘርዘርም በደፈናው ይህን ጉድ ተሸክመው ኢትዮጵያ ላይ አፋቸውን መጉመጥመጥ የሚከጅላቸውን ኢሳያስ የሚመሯት አገር ከሰላሳ ዓመት በላይ ወደሁዋላ መምዘግዘጓን ነው።
ኤርትራ ኢንተርኔት እና ስልክ በቤተሰብ ኮታ እንደሚሰጥ። ገንዘብ በATM ማውጣት ብርቅ የሆነባት ። ዜጎች ሰርግ እንኳን ለመከወን የሚያወጡት ወጪ ኦዲት የሚደረግባት ሀገር መሆኗን ” ጠቅሶ ፋና እንደዘገበው ኢሳያስ በምን ሞራል ስለ ሌሎች አገራት የውስጥ ጉዳይ ትችት ለመስጠት እንደሚነሱ ዘገባውን የሚከታተሉ እንዲፈርዱ የሚጋብዝ ሆኗል።
“ኤርትራውያን ነገን ያለ ተስፋ ኑሮን በጨለማ ለመግፋት ተገደዋል” ሲል የኢሳያስን አስተዳደር ከጨለማ ጋር አመሳስሎ ያቀረበው የፋና ዘገባ፣ “ጉባ ላይ በተለኮሰው የብርሃን ችቦ (GERD) ዜጎቿን ከጨለማ ወደ ብርሃን ለማሻገር እየተጣደፈችን ያለችውን ጎረቤታቸውን (ኢትዮጵያን) ለመተቸት አንደበታቸውን ሲያላቅቁ ምንም የመሸማቀቅ ስሜት አይታይባቸውም” ሲል በአንድ ጀነሬተር ኤሌክትሪክ ለማሰራጨት የሚውተረተሩትን ኢሳያስ በግብራቸው ማንነታቸውን አሳይቷል።
ፋና ይህን ካለ በሁዋላ የኢሳያስን የተልዕኮ ሴራ በይፋ አስቀምጧል። “ኢሳያስ የሚመሩት መንግሥት የጀርባ እቅዱ ኢትዮጵያን አፈራርሶ ለመግዛት እንደነበር በተደጋጋሚ ከሚያሰሙት ንግግራቸው ተስተውሏል” ያለ ፋና ” ከግብፅ እና ሶማሊያ መሪዎች ጋር ቀጠናዊ ሰላም ለማምጣት በሚል የዳቦ ስም በሰጡት መርዛማ ቀጠናውን የማተራመስ ሃሳብ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ላይ ስጋት የደቀነ ስምምነት አስመራ ላይ ሲፈራረሙ ታይተዋል። ነገሩ ሆድ ሲያቅ .. መሆኑን ከ30 ዓመቷ ወጣት ሀገር መረዳት ይቻላል” ሲል የመንግስትን የትዕግስት በቃ ስሜት አሳይቷል።
ኢሳያስ አምርረው የሚጠሉት ለኢትዮጵያውያን የሰንደቅ አላማ ፕሮጀክት የሆነው የህዳሴ ግድብ ሪቫን ሊቆረጥ መቅረቡ እረፍት እንደነሳቸው ያተተው የፋና ዘገባ ” አስራ አምስት ሺህ የሚበልጡ ታታቂዎች የህዳሴው ግድብ እንዳይሰራ ሰልጥነውና ታጠቀው ተለከውብን ነበር” ሲሉ ተቅላይ ሚኒስትር አብይ የተናገሩትን በመካከሉ አስገብቷል።
ኢሳያስ ለጋላቢያቸው ደስታ ሲሉ ሊያጥጥሉት የሞከሩት የህዳሴውን ግድብ የዓለም ታዋቂ የፖለቲካ ተንታኞችና ታዋቂ ሚዲያዎች ” ኢትዮጵያ ኒኩሌር ታተቀች” ሲሉ ግድቡ ኤለኤክትሪክ ከማመንጨትም በላይ እንደሆነ አስታውቀዋል።
ይህ የፋና ዘገባ ” ሻዕቢያ እያለ ኢትዮጵያ ሰላም ልትሆን አትችልም” የሚለውን የበርካቶች መደምደሚያ መቃረብ ያሳይ እንደሆነ በግልጽ ባይገልጸም፣ ፋና እንዳለው ኢሳያስ እያካሄዱ ያለው በኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ላይ የተነጣጠረ ዘመቻ ገደብ ማለፉ “ቀታዩ ምን ሊሆን ይችላል” የሚለውን ጉዳይ ዜጎች እንዲያብላሉት የሚያደርግ ሆኗል»
ሻዕቢያ በባድመ ጦርነት ወቅት ዳግም የአገር ጥሪ ተቀብለው በተመለሱ ውድ የአገር መከላከያ አባላት ጥርሱ ወላልቆ ሊቀበር ሰዓታት ሲቀሩትና ጉዙን ጠቅልሎ ዳግም ወደ ሳህል ሊያነራ ሲል አቶ መለስ እንዳተረፉት የሚታወስ ነው። ” የደርግ ሰራዉት” በሚል ፈርጀው ያፈረሱት የኢትዮጵያ መከላከያ “ጦርነቱ ቆሟል። መሳሪያችሁን አውርዱ” ከተባለ በሁዋላ ኢሳያስ የጅምላ ጭፍጨፋ እንደፈሰሙባቸውም የሚታወስ ነው።