” ከታህሳስ 2 እስከ ታህሳስ 5 ቀን 2017 ዓ/ም ብቻ 6 ሹፌሮች ከነረዳታቸው በታጣቂዎች ተገድለዋል ” – ጣና የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኅበር
የከባድ መኪና ሹፌሮች በሃገር አቋራጭ እና ከተማ አቋራጭ ጉዞዎቻቸው ወቅት በታጣቂዎች የሚደርስባቸው እገታ እና ግድያ ተባብሶ መቀጠሉን ጣና የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኅበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታውቋል።
ባለፉት 5 አመታት በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተገደሉ ሹፌሮች ቁጥርም 230 መሻገሩን ስሜ አይጠቀስ ያሉ የማህበሩ አመራር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ከታህሳስ 2 እስከ 5 ቀን 2017 ዓ/ም ብቻ ስድስት ሹፌሮች ከነረዳታቸው በታጣቂዎች ተገድለዋል ብለዋል።
አራቱ ሹፌሬች የተገደሉት በመተማ ጎንደር መንገድ ጭልጋ አካባቢ ሲሆን ሁለቱ ደግሞ ከጎንደር ሳንጃ መንገድ ፈረስ መግሪያ አካባቢ ነው።
ፈረስ መግሪያ አካባቢ የተገደሉት ሹፌርና ረዳት ሲሆኑ ከታህሳስ 2 ጀምሮ አግተው ገንዘብ እንዲሰጣቸው ሲደራደሩ ቆይተው ታህሳስ 5/2017 ዓ/ም 120 ሺ ብር ከተቀበሉ በኋላ ገድለው እንደጧላቸው ሃላፊው አስረድተዋል።
የችግሩን ክብደት ሲያስረዱም ” አንዳንድ ቦታዎች ላይ መኪና ሲበላሽ የመጀመሪያ ስራ ወርዶ ዝቅ ብሎ ማየት አልሆነም የመጀመሪያ ስራ ወርዶ መሮጥ ነው ምክንያቱም እንደቆምክ አንድ ታጣቂ መጥቶ ሊያግትህ ወይም ሊገድልህ ይችላል ምን ተበላሸ ብለህ የምታየው አንድ ሚሊሻ ይዘህ ተመልሰህ መጥተህ ነው ” ብለዋክ።
ማዕከላዊ ጎንደር ታች አርማጭሆ ከሶረቃ እስከ ሳንጃ፣ ፈረስ መግሪያ ፣ ‘ ኢትዮጵያ ካርታ ‘ የሚባለው አካባቢ ድረስ ለሹፌሮች አስቸጋሪ ሆኖ መቀጠሉን ገልጸው ሳንጃ እና አሽሬ ባለው የመንገድ ክፍል ከህዳር 25 እስከ አሁን ድረስ 5 ሹፌሬች እንደታገቱ ተናግረዋል።
ሃላፊው ፤ ” ሰው የሹፌሮችን እገታ እና ግድያ አሁን በክልሉ ከሚታየው የጸጥታ ችግር ጋር ያያይዘዋል ነገር ግን እገታ በጠቀስናቸው አካባቢዎች 7 እና 8 ዓመት አልፎታል ሹፌርን ማገት የስራ ዘርፍ ሆኖ እየተኖረበት ነው ” ሲሉ አማረዋል።
” በብዛት የሹፌሮች እገታ ያለበት አካባቢ ግጭት ያለበት አካባቢ አይደለም ” ያሉት አመራሩ ” ታገትን ተገደልን ብለን ስንናገር : ግጭት ወዳለበት አካባቢ እያሽከረከራቹ በመሆኑ ነው ‘ እየተባለ ይደበሰበሳል እንባላለንም ነገር ግን ይህ ለወንበዴ ሽፋን መስጠት ነው ” ብለዋል።
በመተማ እና ጎንደር መሃል ቦና ፣ መቃ እና ግንታ አካባቢ አንድ ሹፌር እስከ 40 እና 50 ሺ ብር እንዲከፍል እንደሚገደድ አንስተው በ05/04/17 ሳይከፍሉ ያለፉ ሹፌር እና ረዳት በዚሁ አካባቢ መገደላቸውን አስታውሰዋል።
ለምንድነው የምትሰበስቡት ? ስንልም ” ከምናግታቹ ብለን ነው ” የሚል መልስ ይሰጠናል ብለዋል።
እገታ የሚፈጸምባቸው አካባቢዎች የፀጥታ ኃይል ካምፕ ያለበት ቢሆንም ለሹፌር ጥበቃ የሚያደርግ ሆነ ወንበዴዎችን የሚያጸዳ ሃይል እንደሌለ ተናግረዋል።
በዚህ ምክንያት በሳንጃ ሶረቃ መንገድ 2 ሺህ ብር በመክፈል በአጃቢ ሚሊሻ ለመንቀሳቀስ መገደዳቸውን ጠቅሰዋል።
በዚህ ጉዳይ ላይ የአካባቢውን የጸጥታ አመራሮች ምላሽ እንዳገኘን የምናካትት
TIPS
Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security