የግድያ ወንጀል እንደፈፀመች አምና በፖሊስ ቁጥጥር ሥር በነበረች የቤት ሰራተኛ ላይ በተደረገው እውነትን የማፈላለግ የምርመራ ሥራ የወንጀሉ ተጠርጣሪ አሰሪዋ ሆና እንደተገኘች የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።
ህፃን ሰላማዊት አስፋው የ12 ዓመት ታዳጊ ስትሆን ነዋሪነቷም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሐድያ ዞን ነው ።
በሐምሌ ወር 2016 ዓ.ም የአጎቷ ልጅ የሆነችው ወ/ሮ ዓለምፀሐይ ስላሴ ለህፃኗ ወላጆቿ እያስተማረች ልታሳድጋት ቃል በመግባት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው አለም ባንክ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መኖሪያ ቤቷ ይዛት በመምጣት መኖር ትጀምራለች፡፡
መስከረም 3ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 5 ሰአት ሲሆን ለግዜው የፀቡ መነሻ ባልታወቀ ምክንያት ህፃን ሰላማዊት አስፋው ህይወቷ ያልፋል፡፡
ህፃኗን እያስተማረች ልታሳድጋት ያመጣቻች ተጠርጣሪ ታዳጊዋን የተለያየ የሰውነት ክፍሏን በእንጨት በመደብደብ ከ20 ቦታ በላይ ጉዳት በማድረስ እና አንገቷን በማነቅ ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጓን የምርመራ መዝገቡ ያስረዳል፡፡
በህፃኗ ህልፈተ-ህይወት ተጠያቂ ላለመሆን ያሰቡት ተጠርጣሪዋ ግለሰብ ከባለቤቷ ጋር በመነጋገር በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ በመስራት ላይ የምትገኝ የ17 ዓመት ዕድሜ ያላት ተስፋነሽ ጀባኔን ህፃኗን በድንገት እንደገደለቻት ለፖሊስ ቃል እንድትሰጥና ለውለታዋም ደሞዟን በእጥፍ እንደሚጨምሩላት በተለያዩ መደለያዎች ያሳምናሉ።
በወንጀሉም ጉዳይ ጠበቃ እንደሚቀጥሩላት ካሳመኗት በኋላ ለፖሊስ የሰጠችው ቃል የወንጀል ድርጊቱን እንደፈፀመች የሚገልፅ ነበር፡፡
ሆኖም ፖሊስ የተስፋነሽ ጀባኔን ቃል መነሻ በማድረግ የምርመራ ስራውን በማስፋት ሂደት ለጊዜው ተጠርጣሪ የሆነችው የቤት ሰራተኛ ” እኔ ነኝ የገደልኳት ” ብትልም አንዳንድ አጠራጣሪ ነገሮች መኖራቸውን የደረሰበት ፖሊስ ባደረገው ጥልቅ እውነትን የማፈላለግ የምርመራ ሥራ የወንጀል ድርጊቱን የቤት ሰራተኛዋ እንዳልፈፀመች እና ልታሳድግ እና ልታስተምራት ባመጣቻት ግለሰብ በደረሰባት ድብደባ ህፃን ሰላማዊት አሰፋ ህይወቷ እንዳለፈ ይደርስበታል።
የምርመራ ሂደቱ ቀጥሎ ተጠርጣሪዋ ግለሰብም የወንጀል ድርጊቱን መፈፀሟን አምና በመኖሪያ ቤቷ ድርጊቱን እንዴት እንደፈፀመች መርታ ማሳየቷን የአዲስ አበባ ፓሊስ አስታውቋል።
ተጠርጣሪ ግለሰቧና ባለቤቷ ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከታተሉ ፍ/ቤት እንዳዘዘ ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል፡፡
ወንጀል ፈጽሞ ከህግ ተጠያቂነት የሚያመልጥ እንደማይኖር ያስታወቀው ፖሊስ ንዴትን በመቆጣጠርና በትዕግስት የወንጀል ድርጊትን መከላከል እንደሚቻል አስታውቆ ከቅድመ መከላከሉ ባሻገር ወንጀል ሲፈፀም በፍጥነት ለፖሊስ ማሳወቅ እንደሚገባም አስታውቋል፡፡
(የአዲስ አበባ ፖሊስ)
TIPS
Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security