ከአዲስ አበባ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ የሚመበር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ከባለቤቴ ጋር የተመደበልልን ቦታ ቀደም ብለን ይዘናል፡፡
ግዙፉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለቀጣይ አሰራ ሁለት ሰዓታት ለሚያደርገው ጉዞ ዝግጅቱን አጧጡፎታል፡፡
እኔና ባለቤቴ መቀመጫችንን የሚጋራውን ሶስተኛውን ሰው ስንጠብቅ አንዲት በአምሳዎቹ መጨረሻ ላይ የሚገኙ ሰው ከተፍ አሉ፡፡ በእጃቸው ከዘራ በሌላኛው እጃቸው የሚጎተት ሻንጣ ይዘዋል፡፡
ሻንጣቸውን ከላይ የሚገኘው ማስቀመጫ ላይ እንዳኖርላቸው ለጠየቁኝ እርዳታ ፈጠን ብዬ ተቀብዬ ሰቀልኩኝ፡፡
ምስጋናዬን ተቀብዬ ከመቀመጤ መዳረሻችን ስንደርስ ካወረድክላቸው በኃላ ላግዞት፣ ልግፍ አንዳትል አለች፡፡
ደግሞ ምን ችግር አለው፡፡ የሀገሬ ሰው ባግዝ፡፡ አንድ ሁለት ተባባልን፡፡
ቀጥላ ይህንን የአንዲት ተሳፋሪ ታሪክ አጫወተችኝ፡፡
አንድ መዳረሻውን ዱባይ ያደረገ አውሮፕላን ውስጥ ከእኔ ቀጥሎ አንዲት ተለቅ ያለች ሴት ትመጠጣና የያዘቸውን የእጅ ቦርሳ ከላይ ባለው የእቃ ማስቀመጫ ላይ እንዳኖርላት ትጠይቀኛለች፡፡ ነገር ግን ከእኔ ትይዩ ተቀምጦ የነበረው ሰው ቀልጠፍ ብሎ ተቀብሎ የተጠየኩትን ድጋፍ አደረገ፡፡
ሴትዩዋ ከጎኔ መቀመጫዋን ካመቻቸችና መታጠቂያ ቀበቶዋን ካሰረች በኃላ አክብሮት የተሞላ ወሬ ጀመረችኝ፡፡ በረራችን አንደተጀመረ ብዙም ሳንጓዝ ሆዷን ቁርጠት እንዳጣደፋት ነገረችኝ፡፡ የበረራ አስተናጋጅ ጠርቼ አባካችሁን እርዷት አልኩኝ፡፡ እነሱም መጥተው ድጋፍ አደረጉ፡፡ ከዚያች ቅፅበት ጀምሮ ሴትዩዋ ልጄ እያለች እኔን መጥራት ጀመረች፡፡ ያው ላደረጉት ነገር ይሆናል ብዬ ተቀበልኩ፡፡ ሁሉም ሰው አብረን እንደሆንን ማሰብ ጀመረ፡፡
ልክ ዱባይ ስንደርስ መጀመሪያ ሻንጣውን በማስቀመጥ የረዳት ሰው ሻንጣውን ካወረደላት በኃላ ወደእኔ ጠጋ ብሎ በፍጥነት ከሴትዮዋ እንድርቅና ለበረራ አስተናጋጆቹ አብረን እንዳልሆንን እንዳሳውቃቸው ነገረኝ፡፡
ማስጠንቀቂያው ዋጋ አልነበረውም፡፡
የበረራ አስተናጋጆቹ ከሴትዮዋ ጋር ያለንን ግንኙነት ጠየቁኝ፡፡ እዚሁ አውሮፕላን ላይ መገናኘታችንን ተናገርኩ፡፡ ሴትዮዋ የእጅ ቦርሳዋን እንዳግዛት ለመነችኝ፡፡ ትንሽ ተወዛገብኩ፡፡ ያ ሰው በምልክት እንዳላግዛት አልፎም የበረራ አስተናጋጆቹ አገዛ መጠየቅ እንደሚቻል በቃል ተናገረኝ፡፡
ስሜቱ ቀላል አልነበረም ድንገት የታመመ ሰው አግዙኝ ሲል ጥሎ መሄድ ግን የሰውየውን ምክር ተቀብዬ ዊልቼር እንድትጠብቅ አድርጌ ትቻት መራመዴን ቀጠልኩ፡፡ በደቂቃዎች ውስጥ ከባድ ረብሻ ተፈጠረ፡፡ ከመጣላት ዊልቸሩ ላይ ቦርሳዋን ይዛ ለመራመድ ስትሞክር የኤርፖርት ፖሊስ በቁጥጥር ስር አዋላት፡፡
ከመቅፅበት ልጄ ልጄ እያለች ወደእኔ መጣራት ጀመረች፡፡ ጥያት እየሄድኩ እንደሆነ ወነጀለችኝ፡፡
ለካንስ ሴትዮዋ ከህገወጥ አደንዛዥ እፅ ዝውውር በተያያዘ ተይዛ ነው፡፡
እኔም ተያዝኩ፡፡ የሆነውን አስረዳው፡፡ ፖሊስ ሙሉ ስሜን እንድትናገር ጠየቃት፡፡ መጥራት አልቻለችም፡፡ ቦርሳዬ ተበረበረ፡፡ አሻራዬ ተመሳከረ፡፡ ምንም አይነት ትስስሮች ማግኘት ስላልተቻለ በመጨረሻ ነፃ ወጣው፡፡
ይህ ገጠመኝ በህይወቴ ትልቁን ትምህርት አስተማረኝ፡፡ በጉዞ ላይ ምንም አንኳ ሰውን መርዳት ጥሩ ቢሆንም ቅሉ የራስ ሻንጣ የራስ ነው፡፡ የሰው ሻንጣ ደግሞ የሰው፡፡
ታሪኩን ሰምቼ ስጨርስ ከጎኔ የተቀመጡትን ሴትዬዋን ተመለከትኩ፡፡
ከአስራ ሁለት ሰዓት በረራ በኃላ ስንደርስ አንደመጀመሪያው ሳይሆን በግማሽ ልቤ የሰቀልኩትን ቦርሳ አውርጄ ሰጠውኝ፡፡
አመሰገኑኝ፡፡
የገረመኝ መዳረሻችን የሆነው Washington Dulles International Airport የተቀበለን ባለማቋረጥ የሚነገረው የሰው ሻንጣ እንዳትይዙ፣ እንዳትረዱ . . . የሚለው ማስጠንቀቂያ ነበር፡፡
መልካም ሁኑ ግን ህይወታችሁ መልካምነታችሁን ብቻ ዋጋ ሊያስከፍለው ይችላልና መጠንቀቁ አይከፋም፡፡
ደግ አይለፍችሁ
(ተስፋዬ ሐይሌ) sheger tube
TIPS
Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security