የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ በ2017 በጀት ዓመት ኤጀንሲው የመጨረሻ ያለውንና 8ኛውን የመሬት ይዞታ የማረጋገጥና የእወጃ መርሐግብር ሊጀመር መሆኑን ገልጿል።
የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ዋና ዳሬክተር የሆኑት አቶ ግፋወሰን ደሲሳ በሰጡት መግለጫ ኤጀንሲው የመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ከጀመረበት ከ 2007ዓ/ም እስከ 2016ዓ/ም በጀት ዓመት ድረስ በ 337 ቀጠናዎች ላይ የይዞታ ማረጋገጥ መርሐ ግብሮችን ማካሄዱን አስታውሰዋል።
በ2017 በጀት ዓመት 8 ኛውን ዙር የይዞታ ማረጋገጥ ስራ በ 136 ቀጠናዎች የሚገኙና ይዞታቸው ያልተረጋገጡ የከተማዋ ክፍት መሬቶች ምዝገባ በተመረጡ 6 ክፍለ ከተሞች እንደሚከናወን ነው የገለጹት።
የተመረጡት ክ/ከተሞች እና ወረዳዎች የትኞቹ ናቸው ?
1. የካ ክ/ከተማ በወረዳ 1,2,3,9,10,11,12 በ25 ቀጠናዎች፤
2. በለሚ ክ/ ከተማ በወረዳ 2,3,5,9,10,13 በ 44 ቀጠናዎች፤
3. በአቃቂ ክ/ከተማ ወረዳ 1,2,3,6,9,13 በ19 ቀጠናዎች፤
4. በንፋስ ስልክ ላፍቶ በ ወረዳ 6,7,10,11,14 የሚገኙ 22 ቀጠናዎች፤
5. በቦሌ ክ/ከተማ በወረዳ 3,12,13 በ15 ቀጠናዎች፤
6. በኮልፌ ቀራንዮ በወረዳ 3 በ11 ቀጠናዎች፤
ያልተረጋገጡ ይዞታዎችን የማረጋገጡ ስራ በስልታዊ ዘዴ /በመደዳ/ የማረጋገጥ ሥራ የሚከናወን ሲሆን ስራውም ከታህሳስ 10/04/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አምስት ወራት ውስጥ እስከ ሚያዝያ 15 /2017 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን ሙሉ ወጪውም በመንግስት እንደሚሸፈን ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም ከመሬት ይዞታዎች ጋር ተያይዞ ለመሬት ይዞታ ማረጋገጥ በተመረጡ ቀጠናዎችና ሰፈሮች ውስጥ ብቻ ስራው ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ባለው 5 ወራት ውስጥ የመረጃ ልዩነት እንዳይፈጠር ሲባል ምንም አይነት የስነ ንብረት ዝውውር እንደሚቆም ተናግረዋል።
በመጨረሻም ኤጀንሲው አረጋግጦ ላልመዘገበው ይዞታ ምንም ዓይነት ህጋዊ ዋስትና እንደማይሰጥ የገለፀው የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ከ ታህሳስ 20/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት በክ/ከተማ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አስፈላጊውን መረጃ ይዘው የይዞታ ይረጋገጥልኝ ማመልከቻ እንዲያቀርቡ ጥሪ አስተላልፏል።
@via – Addis Abeba adm
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring