“ጀዋር የአቋም ለውጥ አድርጓል” የሚል የመጀመሪያ ነጠላ ዜማ ተለቋል። ዜማው እንዲያሳካ የሚፈለገው ” ጀዋር የአማራ መብት ተሟጋች ሆነ በሚል የፋኖ ትግል ደጋፊ አድርጎ በማቅረብ በካምፑ ተቀባይነት እንዲያገኝ ነው
ገበያው አስገድዶታል Oromo first ጭንብሉን ለማውለቅ ተገዷል!
ሰዎች በፓለቲካ መድረክ ተፅዕኖ ፈጣሪ ነን የሚሉ ሰዎችን ጥልቅ ፍላጎት ለማወቅ ጥረት ሲያደርጉ አይስተዋልም ።
ከእያንዳንዱ እንቅስቃሴያቸው ጀርባ ምን ምን ፍላጎታቸውን ለማሳካት በምን ምክንያት ምንን መሠረት አድርጎው እንደሚቀሰቀሱ ባለመረዳት ለስህተት ሲደረጉ ይታያል።
በዚህም የብዙ ሰዎችን ስህተት አጋጠሚ በተደጋጋሚ በመጠቀም ከሚታወቁት ሰዎች አንዱ ጀዋር መሀመድ ነው።
ጀዋር የቢዝነስ ሰው እንጂ የመርህ ሰው አይደለም።
የፓለቲካ ቁማር ቢዝነሱን የመሠረተው በደረጃቸውና በስሜት በሚነዳቸው ግለሰቦች ላይ ነው።
ይህን ቁማር ለመብላት ጥልቅና ሰፊ የገበያ ስረዓትና መዳረሻ ጊዜ ሰጥቶ በሚገባ ያጠናልና ያስጠናል ። በምን አይነት አቀራረብ፣ በምን አጀንዳ፣ከነማንና በእነማን በኩል በምን ጊዜ ወደ ቁማር መጫወቻው መግባት እንዳለበት አውቆና አቅዶ ነው የሚጀምረው።
በአሁኑ ሰዓት በአማራ ዘረኛው ዲያስፖራ አከበቢ ሰፊና አዋጭ ገበያ ያለ በመሆኑ በጥናቱ አረጋግጧል በዚህም የመጀመሪያው ምርጫው አድርጓል።
የመርህም የአላማም ሰው ባለመሆኑ ቀድሞ በሌላ የቁማር መጫወቻ ገባያ ላይ እያራመደ ለነበረው አቋሞቹና አጀንዳዎቹ ደንታ የለውም ።
ሰውዬው ተለዋዋጭና ወላዋይ ባህርይ የገነባ ሰው በመሆኑ የትናንቱ እውነት ዛሬ ውሸት ለማለት፤ የዛሬው ውሸት እውነት ነው ብሎ ለማሳመን ከህሊና ጋር ተገጭቶም ፍንትው ብሎ የሚታየውን እውነት በመሸምጠጥ መካድ ይችልበታል ።
አሁን ውግንናውን በአማራው ፅንፈኛ ኤሊቶች አከባቢ አድርጓል ። ለእሱ እውነት ምኑም አይደለችም ።
የሚነገረውና የሚያቀርበው የሚነዛውና የሚረጨው
ጥቁር ፕሮፓጋንዳው የሚያሰራጨው የሀሰት መረጃው በአገር፣ በብሔር፣ በህብረተሰብም ይሁን ግለሰብ ላይ የሚያስከትለው የሞራል፣የስብዕና፣ ሰብዓዊና ህልውናዊ ጉዳት ከንዋይ ፍላጎቱ የማይበልጥ በመሆኑ ደንታው አይደለም።
የእሱ ገደብ የለሽ የንዋይ ፍላጎቱ ይሙላለት እንጂ የሰው መሞት፣ መፈናቀል፣ መሰደድ፣ መሰቃየት፣ መራብና መጠማት ለጃዋር ተራ ነገር ነው።
ሰሞኑን የገበያው መዳረሻ ወደ አደረገው ካምፕ በጥልቀት ለመግባት “Oromo first” የሚለውን ጭንብሉን አውልቆ መጣል ግድ ስላለው አላቅማማም ።
እናም የአማራ ፅንፈኛ ዲያስፖራ ኤሊቶችን የልብ ትርታ ጠንቅቆ አጥንቶ፣ አውቆ፣ አቅዶና ወስኖ ተቀላቅሏል ።
ለዚህም የአዲሱን ቢዝነስ ለማሳለጥ መደራጀት ያለበትን አደራጅቷል። የሰው ሃይል መዋቅሩን በሁሉም ዘርፍ ሚዲያዎችን ጨምሮ ተዘጋጅቶለታል።
ፕሮግራሞችና መድረኮች ተለይቷል ። አስተባባሪዎችም ተመድበዋል ። በበጀትም ተደግፎ ሥራው ጀምሯል ።
“ጀዋር የአቋም ለውጥ አድርጓል” የሚል የመጀመሪያ ነጠላ ዜማ ተለቋል።
ዜማው እንዲያሳካ የሚፈለገው ” ጀዋር የአማራ መብት ተሟጋች ሆነ በሚል የፋኖ ትግል ደጋፊ አድርጎ በማቅረብ በካምፑ ተቀባይነት እንዲያገኝ ነው።
ለትስስር እሳቤአቸው ስኬታማ መሆን ” የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው በሚል አንገት ማስገቢያቸው በዜማው ጎልቶ እንዲወጣ እያደረገ ነው።
የጋራ ጠላታቸው ብለው የሰየሙት ለጊዜው ብልፅግና ፓርቲን ነው። በተለይም የአገራችን ጠቅላይ ሚኒስትርና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች የመጀመሪያ ኢላማዎቹ ናቸው።
በዚህ ላይ በተመሠረተው የሴራ ትንተና አዘጋጅተዋል። በቀደመው ሚስጥራዊ ሥራቸው በጃል መሮ የሚመራውን WBO (ኦነግ)ና በደብረፅዮን የሚመራውን የህውሓት ክፋይ ከጃውሳው ፋኖ ጋር የማስተሳሰር ሥራ በሙከራ ደረጃ አቀናጅቷል።
ይህ የጥፋት ሴራ ውስጥ ውስጡን ሲሰራ የቆየ ቢሆንም በጃል ሰኚ የሚመራው WBO ከኦሮሚያ ክልል መንግስት ጋር በተፈራረመውና በተፈጠረው የሰላም ስምምነት መሠረት በነቂስ ወደ ካምፕ መግባት ያልጠበቁት በመሆኑ በእቅዳቸው ላይ “ጋሬጣ ” የፈጠረባቸው በመሆኑ ድርድሩን ለማደናቀፍ ያደረጉት መወራጨት ስለከሸፈባቸው መደናገጥ ውስጥ ገብተው ለመጠናቀቂያው ተቸግረው ቢቆዩም በመሮ እጅ የቀሩትን በጫካ ለማቆየት በጎጃም ጃውሳ አቋቁመናል ካሉ “ወለጋ ክፍለ አገር ፋኖ” ጋር ለማቀናጀት ላይ ታች ላይ እያሉ ነው።
የዚህን የሰሞኑ ሴራቸውን ውጤት በሰሞኑ ለጃዋር በሚዘጋጀው ፕሮግራምና መድረክ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል ።
ለማንኛውም የተተበተበ ሴራቸውን ከሥር ሥሩ እየተከታተልን በመበጣጠስ ኢትዮጵያን ከከሃዲያንና ከሆድ አደር ባንዳዎች የተንኮልና ጥፋት ለመታደግ ከየትኛውም ጊዜ በበለጠ እንታገላቸዋለን !
በጥፋት_ሀይሎች_ከንቱ_ሴራ_ኢትዮጵያ_አትፈርስም
ሁሴን ገዳ ከኦሮሚያ