” ባለፉት 15 ወራት ብቻ ከ38 ሺህ በላይ ወጣቶች ተሰደዋል ፤ ከ6 ሺህ በላይ የሚሆኑት ህይወታቸው አልፏል:: ያሉት ችግሮች ወጣቱን ተስፋ በማሳጣት ህገወጥ ስደትን እንደ ብቸኛ አማራጭ እንዲመለከት እያደረጉት ነው ! ” የትግራይ ስፖርትና ወጣቶች ቢሮ
በትግራይ በተካሄደው አስከፊና እውዳሚ ጦርነት ምክንያት የወጣቶች ህገ-ወጥ ስደት እንግልትና ሞት በእጅጉ ተባብሶ መቀጠሉ ተነግሯል።
የፕሪቶሪያ ውል ተሟልቶ አለመፈፀሙ ፣ የመልሶ ግንባታ ስራዎች አለመጀመራቸው ፣ ሰፊ የስራ እጦት መኖር ለህገ-ወጥ የወጣቶች ፍልሰት መባባስ ምክንያቶች ናቸው ተብለዋል።
ይህን የሰማነው የትግራይ የስፖርትና የወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ከለጋሽ ድርጅቶች በመተባበር ” ህገ-ወጥ ስደት ” በሚል ካዘጋጀው አንድ መድረክ ላይ ነው።
ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በኋላ የበርካታ ወጣቶች ህይወት እየነጠቀ ያለውን ህገ-ወጥ ስደት አስመልክቶ በ49 የክልሉ ወረዳዎች በተካሄደ ጥናት ባለፉት 15 ወራት ብቻ ከ38 ሺህ በላይ ወጣቶች መሰዳዳቸው ያሳያል።
ከ38 ሺህ ስደተኞች ከ6 ሺህ በላይ ባለፈው ዓመት በጉዞ እያሉ ለህልፈት ተዳርገዋል ፤ አካላቸው የጎደለ አሉ ፣ አድራሻቸው የጠፉም ብዙ ናቸው።
2017 ዓ.ም ከገባ ወዲህ ብቻ ከ6 ሺህ በላይ ወጣቶች በህገወጥ መንገድ ተሰደዋል ከነዚሁ ደግሞ 300 ገደማ ለህልፈት ተዳርገዋል።
አደጋው የክልሉ ከፍተኛ ስጋት ወደ መሆን ተሸጋግረዋል ሲል ቢሮው አሳውቋል።
በትግራይ በጦርነቱ ምክንያት ፦
– የኢኮኖሚ አውታሮች ወድመዋል ፣
– የብድር አገልግሎት መስጠት እጅግ የደከመ ነው፣
– ሰፊ የስራ እጦት አለ እነዚህን እና ሌሎች ችግሮች ወጣቱ ተስፋ በማሳጣት ህገወጥ ስደት እንደ ብቸኛ አማራጭ እንዲመለከት አድርገውታል።
ይህ ከፍተኛ ችግር እንዲቀረፍ የፌደራል መንግስትና ለጋሽ ድርጅቶች ድጋፋቸው እንዲቸሩ የትግራይ ክልል ስፖርትና ወጣቶች ቢሮ ጥሪ አቅርቧል።
Via Tikvah
TIPS
Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security