በቱርኪዬ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን አደራዳሪነት በአንካራ የተካሄደው የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ድርድር ተጠናቀቀ፡፡
ጠቅላይ ሚኒትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት የኢትዮጵያና የሶማሊያ ህዝቦች በቋንቋ በባህል እና በደም የተሳሰሩ መሆናቸውን አንስተው አገራቸው ለጋራ ሰላምና ልማት ከሶማሊያ ጋር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗን ተናግረዋል፡፡
https://www.youtube.com/live/uoSL2pAWx7M?si=qscGQ1OWMTvghQd_
ኢትዮጵያ የባህር በር በሰላማዊ መንገድ ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት ለቀጣናው ምጣኔ ሃብታዊ እና ማህበራዊ ትስስር የጎላ ሚና እንደሚጫወት አንስተዋል
የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሃሰን ሼክ ሞሃሙድ በበኩላቸው ለሁለቱ ሃገራት ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ሰላም ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን አንስተው ከኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ ጋር በጋራ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
መንግስታቸው የኢትዮጵያ ወታደሮች ለሶማሊያ ሰላም መጠበቅ የከፈሉትን መስዋዕትነት እንደማይዘነጋው እና በቀጣይም ሰላምን ለማፅናት ለሚረገው ጥረት ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን:- ሁለቱ ሃገራት የፈረሙት የስምምነት ሰነድ ትብብርን፣ ምጣኔ ሃብታዊ ልማትን እና ብልጽግናን የሚያረጋግጥ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በወንደሰን አረጋኸኝ fbc
ከሶማሊያ ወታደሮች ጋር የተካሄደውን ውጊያ ተከትሎ ጁባላንድ ራስካምቦኒን ተቆጣጠረች
በሶማሊያ ፌደራል መንግስት ወታደሮች እና ጁባላንድ ኃይሎች መካከል ትናንት ውጊያ መካሄዱን ተከትሎ የጁባላንድ ኃይሎች ራስካምቦኒ ከተማን ተቆጣጠሩ።
ውጊያው በሁለቱ አካላት መካከል ትናንት ታህሳስ 2 ቀን ጠዋት የተጀመረ ሲሆን የጁባላንድ የፌዴራል ኃይሎች ግጭት አስጀምረዋል ሲል ከሷል። የሟቾች ቁጥር ግልጽ ባይሆንም የመሠረተ ልማት ላይ ጉዳት እንደተከሰተ ሪፖርት ተደርጓል።
የሶማሊያ መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የጁባላንድ መሪ የሆኑትን አህመድ ኢስላም ሞሀመድ ማዶቤ ከአልሸባብ ጋር ተባብረዋል ሲል በመክሰስ በተሳታፊዎች ላይ “ህጋዊ እርምጃ” ሊወሰድ እንደሚችል አስጠንቅቋል ሲል ሶና ዘግቧል።
የጁባላንድ ባለስልጣናት ኃይላቸው ስትራቴጂካዊ አየርማረፊያን ጨምሮ በራስካምቦኒ ቁልፍ ቦታዎችን መቆጣጠሩን ገልጸዋል። ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት ከ300 በላይ የፌደራል ወታደሮች ወደ ኬንያ ተሻግረው በኬንያ ኃይሎች ትጥቅ እንዲፈቱ ተደርገዋል። በተጨማሪም 240 የፌደራል ወታደሮች በጁባላንድ ወታደሮች እጅ መግባታቸው ተነግሯል።