በኒውዮርክ ከ2022 ጀምሮ ስራ ላይ ነበር የተባለው ፖሊስ ጣቢያ በቻይና የህዝብ ደህንነት ሚኒስቴር የተደራጀ ነው ተብሏል።
የአሜሪካ ዜግነት ያለው ግለሰብ በኒውዮርክ ከተማ በቻይና መንግስት የተቋቋመ ድብቅ ፖሊስ ጣቢያን በማስተዳደር ተከሷል፡፡
ቼን ጂንፒንግ የተባለው አሜሪካዊ ከሌላ አንድ የስራ አጋሩ ጋር በመሆን በማንሀታን ቻይና ታውን ከሁለት አመታት በላይ ድብቅ ፖሊስ ጣቢያውን ሲያስተዳድሩ መቆየታቸውን በአቃቤ ህግ የክስ ምዝገብ ላይ ተጠቅሷል፡፡
ቤጂንግ አሜሪካን ጨምሮ በ53 ሀገራት 100 ተመሳሳይ ፖሊስ ጣቢያዎችን በድብቅ ማደራጀቷን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ዘገባው ፖሊስ ጣቢያዎቹ በዋናነት የመንግስት ተቃዋሚዎችን እንዲሁም የዴሞክራሲ አቀንቃኝ ቻይናውያንን መከታተል እና ማስፈራረት ላይ የሚሰሩ መሆናቸውን አስነብቧል ፡፡
ጉዳዩን ያስተባበለችው ቻይና ፖሊስ ጣቢያ የተባሉት ቢሮዎች በውጭ ሀገራት ለሚኖሩ ዜጎች አስተዳደራዊ አገልግሎቶችን ለማቅረብ የተመሰረቱ ናቸው ብላለች፡፡
የአሜሪካ ፍትህ ሚኒስቴር ምክትል ጠቅላይ አቃቤህግ ማቲው ኦልሴን ድርጊቱ የአሜሪካ ሉአላዊነትን የጣሰ እና የዜጎችን ደህንነት አደጋ ላይ የጣለ ከፍተኛ ጥፋት ነው ሲሉ አብራርተዋል፡፡
በቻይና የሀገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስቴር የተቋቋሙ ናቸው የተባሉት እነኚህ ድብቅ ፖሊስ ጣቢያዎች አስተዳደራዊ አገልግሎቶችን ለመሰጠት የተከፈቱ ናቸው ይባል እንጂ ይፋዊ የስራ ሰአት የሌላቸው እና የአሜሪካ ዜግነት ባለቸው ግለሰቦች የሚመሩ ናቸው ተብሏል፡፡
የአሜሪካ የፌደራል የወንጀል ምርመራ ቢሮ (ኤፍቢአይ) በኒውዮርክ የሚገኘውን ጣቢያ በሀላፊነት ሲመራ ነበር የተባለው ቼን ጂንፒንግ እና የስራ አጋሩ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከመዋላቸው በፊት ከቻይና የሀገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስቴር ጋር ሲያደርጉት የነበረውን የጽሁፍ መልዕክት ልውውጥ ከስልካቸው ላይ እንዳጠፉት ደርሰንበታል ብሏል፡፡
ከዚህ ባለፈም በዋናነት በመንግስት የሚፈለጉ ግለሰቦችን፣ ተቃዋሚዎችን ጨምሮ ከቻይና መንግስት በሚላክላቸው የስም ዝርዝር መሰረት ሰዎችን አፈላልጎ በማግኘት ዛቻ እና ማስፈራሪያዎችን ማድረስ ላይ ይሰሩ እንደነበር ተገልጿል፡፡
ግለሰቦቹ በድብቅ ስለላ በቀረበባቸው ክስ ጥፋተኛ መሆናቸውን አምነዋል፤ ይህን ተከትሎም እስከ አምስት አመት ድረስ እስር ይጠብቃቸዋል ተብሏል፡፡
Via : አል አይን
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring