አምና በዚህ ወቅት የኢትዮጵያ የቀይ ባህር ሃገርነት፣ አስተማማኝ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የባህር በር የማግኘት መብት፣ ከዚህ ጋር ተያይዞም የባህር ሃይል ቤዝ በሊዝም በልዋጭም የማግኘት አስፈላጊነት በጥቂት ምርጥ ኢትዮጵያዊያን አዕምሮ ውስጥ ካልሆነ በቀር በማንም ውስጥ አልነበረም። አለም አቀፉ ህብረተሰብማ ኢትዮጵያውያን የረሱትን አጀንዳ የሚያስታውስበት ሰበብም ምክንያትም አልነበረም።
እ.አ.አ. በ2018 “Red Sea Forum” በሳዑዲ አረቢያ አሰባሳቢነት ሲቋቋም፤ ከቀይ ባህር ዳርቻ በ60 ኪሎ ሜትር ብቻ ርቀት ላይ የምትገኘውን እና በቀይ ባህር ላይ ደግሞ ከ10 በላይ የንግድ መርከቦች ያላትን ሃገር በታዛቢነት እንኳን እንዳትገኝ የተቃወሙት ግብፅ፣ ኤርትራ እና ጂቡቲ ናቸው። ከኤርትራ ጋር “ሰላም ከወረደ” በኋላም በተደረጉ የፎረሙ ስብሰባዎች ላይ ራሷን ኤርትራን ጨምሮ ግብፅ እና ጂቡቲ ባላቸው ተቃውሞ ምክንያት ኢትዮጵያ መሳተፍ አልቻለችም። ሁኔታውን በተከታተሉ ኢትዮያውያን ዘንድ ይሄ ሁኔታ የፈጠረው ቁጭት እና ቁጣ ቀላል አልነበረም። “የቀይ ባህር አዋሳኝ ሃገርነታችንን ማስከበር አለብን።
ይህን ለማድረግም ያለንን ዲፕሎማሲያዊ አቅም ሁሉ አሟጠን እንጠቀም። አለዚያ ነገ ማንም ተነስቶ blockade ሊጭንብን ይችላል” የሚለው ድምዳሜ ላይ የተደረሰው ወዲያው ነበር። እናም ጠ/ሚ አብይ አህመድ ከኢሳያስ እስከ ፎርማጆ፤ ከኦማር ጌሌ እስከ አል ቡርሃን ያላናገረው እና የጋራ ጥቅምን ለሚያስገኝ ድርድር ያልጋበዘው ሀገር/መሪ አልነበረም። ግልፅ በሆነም ባልሆነም ምክንያት ግን አይደለም “ለሰጥቶ መቀበል” በጉዳዩ ላይ ለመነጋገር እንኳን ሁሉም ፈቃደኛ አልነበሩም። ስለዚህ ገበያው ላይ የቀረው አማራጭ አንድ እና አንድ ብቻ ነበር። ዲፕሎማሲውን አጡዞ ከገደል አፋፍ በማድረስ (brinkmanship) የሚፈልጉትን ማግኘት!
Brinkmanship በዲፕሎማሲው አለም risky ግን አማራጭ ሲጠፋ የሚመረጥ ውጤታማ መንገድ ነው። ውጤቱም pragmatic compromise ነው። በዚህም መሰረት የJanuary 1ዱ MOU ከሶማሊላንድ ጋር ተፈርሟል። እንደተጠበቀውም በአጭር ጊዜ የኢትዮጵያ አስተማማኝ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የባህር በር የማግኘት መብት እና መሻት ቀጠናዊ ብቻ ሳይሆን አለም አቀፋዊ አጀንዳ ለመሆን በቅቷል። የታላላቆቹን ሃገሮች ትኩረት አግኝቷል። እንደ ግብፅ ያሉ ሃገሮችን ደግሞ ለተሳሳተ ስሌት እና ምኞት አነሳስቷል። ከላይ እንደተገለፀው የbrinkmanship ተጠባቂ ነገሮች risኮቹን ጨምሮ በአብዛኛው ተከስተዋል።
በመጨረሻም ቱርኪዬ ለራሷም ጥቅም ለቀጠናውም መረጋጋት ስትል (በአሜሪካ እና በአውሮፓ አበረታችነት) ያለፉትን ወራት ቀጥተኛ ያልሆኑ ንግግሮችን facilitate ስታደርግ ነበር። በትናንትናው ዕለት ደግሞ “MOUው በቅድሚያ እና በይፋ ሳይቀደድ በፊት የፊት ለፊት ድርድር አይታሰብም…እንደውም ኢትዮጵያ ለሰላም ማስከበር ያሰማራችን ሰራዊቷንም አልፈልግም” እያለ ሲደነፋ የነበረውን ሀሰን ሼክን አንካራ ላይ ጠርታ አደራድራለች። ውጤቱም (ዝርዝሩ ገና ወደፊት የሚታይ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ) የሚያበረታታ ነው። የተከተልነው brinkmanship ውጤት የሚለካው የጠየቅነውን ሁሉ በማግኘት ወይም ባለማግኘታችን አይደለም። የጥያቄዎቻችንን legitimacy and urgency እስከየት አደረስነው የሚለው ነው ዋናው። ስለዚህ ምቀኝነት እና ባንዳነት በተጫጫነው ስሜት ውስጥ ሆነህ ካላነበብከው በቀር የአንካራው ዲክላሬሽን ይዘት ግልፅ እና ግልፅ ነው።
በመጨረሻም የJanuary 1ዱን MOU “ይሄ ለኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ዝቅታ ነው” እያሉ ሲያጣጥሉ እና ሲያላዝኑ የከረሙ ድኩማን፤ አሁን ደግሞ “የአንካራ ዲክላሬሽን MOUውን መና የሚያስቀር ስለሆነ ለኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ኪሳራ ነው” እያሉን ነው ምፅ! ለእነዚህ ፊደል-ቀመስ መሃይማን MOUው ግባችንን ከምናሳካባቸው tools አንዱ እንጂ በራሱ ግብ እንዳልሆነ ለማሰብ ስንፍናቸው አልፈቀደላቸውም። አንድ ሃገር ብሄራዊ ጥቅሙን ግቡን ለማሳካት አይደለም MOU፤ አሳሪ የሆነ ውል (treaty) ሊተው ወይም ሊጥስ እንደሚችል ለማሰብ ምቀኝነታቸው ጋርዷቸዋል። ከሁሉም በላይ በአለም አቀፍ ግንኙነት ቋሚ ጥቅም እንጂ ቋሚ ወዳጅነት እንደሌለ፤ ብሄራዊ ጥቅምን ለማሳካትም አማራጮች እንደየሁኔታው እንደሚወሰኑ ለመረዳት ከመንደር ያልዘለለው የአስተሳሰብ አድማሳቸው አልፈቀደላቸውም።
የሆነው ሆኖ የኢትዮጵያ አስተማማኝ እና ደህነቱ የተጠቀቀ የባህር በር የማግኘት መብት እና መሻት ከአሁን በኋላ (እንደ ኢህአዴግ ዘመን) የምርጫ ሰሞን የውስጥ ፖለቲካ ማጣፈጫ ሳይሆን፤ ቀጠናዊ እና አለም አቀፋዊ አጀንዳ ሆኗል። ባንዳም ሆንክ ባዳ ልክ እንደ ዛሬው ስለጉዳዩ ወይ እየተወያየህ አሊያም እያለቃቀስክ ከዕድሜህ ላይ ደቂቃም አመትም ስትገብርለት ትኖራለህ። ብትወድም። ባትወድም።
Oluma M. Wodajo ነጻ አስተያየት ከፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ የተወሰደ