በጎንደር ከተማ የጥምቀት በዓል የሚከበርበት የፋሲለደስ መጠመቂያ ስፍራ የእድሳት ስራ ተጠናቆ ለበዓሉ ዝግጁ መደረጉን የከተማው ባህልና ቱሪዝም መምሪያ አስታወቀ፡፡
የመምሪያው ተወካይ ኃላፊ አቶ ልዕልና አበበ እንደገለጹት፤ የጥምቀተ ባሕሩን የውኃ ስርገት ለመከላከል የሚያስችል የጥገና ስራ መከናወኑንና አሁን ላይም ከ10 ሺህ ሜትር ኪዩብ በላይ ውኃ የመሙላት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በጥምቀተ ባሕሩ መንበረ ታቦታቱ የሚያርፉባቸው ስፍራዎችን የማጽዳትና ለምዕመናኑ ምቹ የማድረግ ስራዎች በአብዛኛው መጠናቀቃቸውን ተናግረዋል፡፡
በበዓሉ የሚታደሙ የሀገር ውስጥና የውጪ ጎብኚዎችን ጨምሮ ለታላላቅ እንግዶች የሚውሉ የማረፊያ ስፍራዎች ደህንነታቸው በተጠበቀ መንገድ ዝግጁ መደረጋቸውን ጠቁመዋል፡፡
እስከ 400 እንግዶችን ማስተናገድ የሚያስችሉ የብረት አግዳሚ ወንበሮች ጥራታቸውን በጠበቀ መንገድ ተሰርተው ለአገልግሎት መዘጋጀታቸውንም አመልክተዋል፡፡
ክብረ በዓሉን በቀጥታ ስርጭት ለሀገር ውስጥና ለመላው ዓለም ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችሉ ጊዜያዊ የቴሌቪዠን ማሰራጫ ስቱዲዮዎች የሚተከሉባቸው ስፍራዎች መደራጀታቸውንም ጠቁመዋል፡፡
ጊዜያዊ መፀዳጃ ቤቶችን ጨምሮ የኤሌክትሪክ፣የውኃና የኢንተርኔት አገልግሎቶችን የማሟላት ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀው፤ የመጀመሪያ ደረጃ ሕክምና መስጫ ቦታዎችም ተዘጋጅተዋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ዘንድሮ በከተማው በሚከበረው የጥምቀት በዓል ላይ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ቱሪስቶችን ጨምሮ በርካታ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ይታደማሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ጥር 7 ቀን 2017 ዓም (ኢ ፕ ድ)
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring