ብታምኑም ባታምኑም!
አዲስ ዓመትን እንዲያከብሩ እስረኞችን ፈቶ የለቀቀው ፖሊስ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡
ድርጊቱ ፈገግታን ቢጭርም በስካር መንፈስ ውስጥ ሆኖ የአዲስ አመት ዋዜማን እንዲያከብሩ 13 ታሳሪዎችን ከፖሊስ ጣቢያ የለቀቀው የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር ውሎ የሀገሪቱ ፖሊስ የተለቀቁትን እስረኞች እያፈላለገ ነው ተብሏል፡፡
የዛምቢያ ፖሊስ አባል የሆነው መርማሪ ኢንስፔክተር ቲተስ ፊሪ የተባለው ፖሊስ በቁጥጥር ስር የሚገኙ ተጠርጣሪዎቹን በዋና ከተማዋ ሉሳካ ከሚገኘው ሊዮናርድ ቼሎ ፖሊስ ጣቢያ ነው ፈቶ የለቀቃቸው፡፡
ለረጅም ሰአታት በጠጣው መጠጥ በአልኮል ተጽዕኖ ውስጥ የነበረው ኢንስፔክተሩ ድርጊቱን ከፈጸመ በኋላ ከህግ ለማምለጥ ጥረት አድርጓል፡፡
ባልጠበቁት ሁኔታ ከእስር ቤት እንዲወጡ የተፈቀደላቸው ታሳሪዎች በዝርፊያ ፣ ስርቆት እና አካላዊ ጥቃት በማድረስ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የሚገኙ ነበሩ፡፡
በአሁኑ ወቅት ሉሳካ የሚገኘው የሊዮናርድ ቼሎ ፖሊስ ጣቢያ ፖሊስ አባላት ያመለጡትን ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ለማዋል በአደን ላይ ይገኛሉ፡፡
የፖሊስ ቃል አቀባይ ሬ ሀሙንጋ ድርጊቱን የፈጸመው ኢንስፔክተር ቲተስ ፊሪ በአዲስ አመት ዋዜማ ተረኛ የእስረኞች ጠባቂ ከሆነችው የፖሊስ አባል የእስር ቤቶቹን ቁልፍ በሀይል እንደቀማት ተናግረዋል፡፡
በመቀጠልም ኢንስፔክተሩ የወንድ እና ሴት የእስር ቤት ክፍሎችን በመክፈት “ወደ አዲሱ አመት ለመሻገር ነፃ ሆናችኋል” በማለት ከእስር ቤቱ እንዲወጡ እንዳዘዛቸው ቃል አቀባዩ ገልጸዋል፡፡
በስካር መንፈስ ውስጥ ሆኖ ያልተጠበቀውን ድርጊት የፈጸመው መርማሪ ኢንስፔክተር ወዲያው ከአካባቢው ለመሸሽ ቢሞክርም በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
ኢንስፔክተሩ ድርጊቱን ለምን እንደፈጸመ እስካሁን ቃሉን እንዳልሰጠ የተገለጸ ሲሆን ፖሊስ በበኩሉ ከእስረኞቹ መለቀቅ ጀርባ የስካር ስህተት ወይስ ድብቅ ዓላማ ያለው የተቀነባባረ ድርጊት የሚለውን ለማጣራት በምርመራ ላይ እገኛለሁ ብሏል፡፡
Via – አልአይን
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring