በተደጋጋሚ ሲገለጽ ከነበረው በላይ ከበድ ያለ መሆኑ የተነገረለት የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል። ይኸው በሬክተር ስኬል 5.8 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተው ታህሳስ 25 ሊነጋጋ ሰዓቱ 9:52:21 ላይ እንደሆነ ክስተቱን ይፋ በማድረግ የሚታወቁ ተቋማት ዓለም ዓቀፍ አመልክተዋል።
የመሬት መንቀጥቀጡ ማዕከል በሆነበት ስራ ተራሮቹ የመወጠርና የማበጥ ምልክት ውይም ወደ ላይ ከፍ የማለት ምልክት እንዳሳዩ ባለሙያዎች አስታውቀዋል። ባለሙያዎቹ ቀደ ሲል ከሚሰጡት የተለሳለሰ ምክር ከፍ ብለው ቅድም ዝግጅት ሊደረግ እንደሚገባ ጥቆማ እየሰጡ ነዎኦ የንዝረቱ መጠን በጨመረ ቁጥር እያስከተለ ያለው አደጋም እየከፍ በመሆኑ መንግስት ግብር ኃይል አቋቁሞ ስራ መጀመሩን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አስታውቋል።
የከሰም ስኳር ፋብሪካ በተቋም ደረጃ ከፍተኛ ጉዳት የደርሰበት ነው። ትምህርት ቤቶች፣ መንገድ፣ መኖሪያ ቤቶች፣ መተላለፊያዎች፣ ወዘተ እስካሁን በውል ያልታወቁ ጉዳት አስከትለዋል። አሁን ደግሞ እየተባባሰ በመሄዱ ፍርሃት ነግሷል። ነዋሪዎች አዲስ አበባን ጨምሮ በማህበራዊ ገጽፕቻቸው እነሚሉት ከሆነ የመሸረሻው ንዝረት የሚረብሽ ነበር። ይህን ተክትሎም ስጋቱ በርክቷል።
የመንግስት መገናኛዎች እንዳስታወቁት ከያሃ ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ከስጋቱ ቀጣና ማስወጣት ተችሏል። ይኸው በምስል የተደገፈ መረጃ እንደሚያሳየው የአገር መከላከያ ሰራዊት ሳይቀር ዜጎችን ለማሸሽ በሚደረገው ርብርብ አስተዋጾ እያበረከተ ነው።
በኢትዮጵያ ሰማይ ስር የተቃዋሚ ፖለቲካ፣ ወይም መቃወም ማለት ሁሉንም ማውገዝና፣ ማንኛውንም ጉዳይ ከፖለቲካ ዓላማ ጋር በማያያዝ መጠቀሚያ ማድረግ የተለመደ በመሆኑ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ ፍጹም ተፈጥሯዊና ከተከሰተ እጅግ ዘግናኝ አደጋ የሚያስከትል በመሆኑ ስጋት የበዛቸው ያሉትን ያህል ጉዳዩን ፖለቲካዊ ለማድረግ የሚሯሯጡ መታየታቸው ትዝብት ፈጥሯል። በየትኛውም አገር መንግስት ለመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ሆኖ ተከሶ አያውቅም። ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ይህ እየሆነ ነው። አብዛኞች ግን በጨዋነትና ኃላፊነት ወስደው መንግስት አስቀድሞ ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባው እየመከሩ ነው።
“ሽባ” የሚባለውና ሁሌ ስብሰባ የምረቃ ስነስርዓት አጃቢ የሆነው የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሰማኒያ ሺህ የሚሆኑ ዜጎችን መንግስት ከስጋት ቃጣና ማግለሉን አልተነፈሰም። የዕለት ቀለብና ፈጥኖ ደራሽ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑንና አደጋውን ቀድሞ ለመከላከል ግብር ኃይል ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑ አልስታወቀም። ይህ ሁሉ እየተሰራ ለህዝብ ከማሳወቅ ይልቅ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሰክሬታሪያት ጨምሮ በድግስና ስብሰባ ሲርመጠመጡ ማየት አሳዛኝ እንደሆነ በርካቶች እየገለጹ ነው። ይህን የኮሙኒኬሽን ክፍተት መንግስት ስለምን እንደማያርመውም ግልጽ አይደለም።

ምስል – አሁን ላይ ውሃና ቅልጥ ማዕድን እየተፋ ያለው እሳተጎሞራ የሚከልለው ስፍራ ጨምሯል። ሰፊ ቦታ በፈሳሹ እየሸፈነ ነው
የመለኪያ መጠኑን በመለየት የአደጋውን መጠን ዘርዝረው የሚያቀርቡ ተቋማት እንደሚሉት ከሆነ አሁን ላይ ኢትዮጵያ ላይ እየሆነ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ደረጃው ወደ አስጊ ደረጃ እየተሸጋገረ ነው። የመሬት ርዕደቱ መጠን ደረጃና የአደጋውን መጠን የሚያሳዩት ቁጥሮች በሬክተር ስኬል ተለይተው ሲተነተኑ ፣ ከ4.0 በታች አነስተኛ ተብሎ የተመደበ ነው። እንዲህ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ በመጠኑ የሚሰማና አልፎ አልፎ ካልሆነ በቀረ ይህ ነው የሚባል ከፍተኛ አደጋ የሚያስከትል አይደለም። ከ4.0 – 4.9 የሚመደበው አነስተኛ ጉዳት ንየሚመዘገብበት ነው። ከ5.0 – 5.9 በመጠነኛ ደረርጃ የሚመደብ ሲሆን፣ ጥራታቸውን ጠብቀው ባልተገነቡ ግንባታዎች ላይ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል። ከ6.0 – 6.9 ጠንከር ያለው ነው። ህዝብ በሚበዛባቸው አካባቢዎች በተለይም አሮጌ ወይም በደንብ ባልተገነቡ ህንፃዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል ባለሙያዎቹ ይገልጻሉ።
የከረረና አደጋው የከፋ እንደሚሆን በስጋት ትንተናው የተመለከተው ደረጃ መነሻው ልኬቱ ሲታይ ከ7.0 – 7.9 መሠረተ ልማትቶችና ግንባታዎችን ህንጻዎችን ሊያፈራርስ የሚችለው። 8.0 እና ከዚያ በላይ ብዙ ጊዜ አስከፊ የሚባለው ነው። የሰው ህይወት የሚቀጥፍ፣ ሰፊ ውድመት ሊያስከትል የሚችል ሲሆን፣ በተለይም በተከሰተበት አካባቢ ክፉኛ ጉዳት የሚያደርስና “አያድርስ” የሚባለው ዓይነት ነው።
በዚህ ትንተናና መሰረት በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ አነስተኛ ከሚባለው ተነስቶ ወደ መጠነኛ ደረጃ ያደገ እንደሆነ መረዳት ይቻላል። የአደጋው ትንታኔ እያደገ በመሄዱ ባለሙያዎች በሰጡት ምክር መሰረት አስፈላጊዎን ሁሉ ለማስድረግ መንግስት ስራ እየሰራ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት አስታውቋል። ዜጎችም አስፈላጊ መረጃ አግባብ ካላቸው ክፍሎች ሊወስዱ እንደሚገባ ዘግይቶም ቢህፕን ባሰራጨው መግለጫው መክሯል።
ህብረተሰቡ በመሬት መንቀጥቀጥ ዙሪያ በባለሙያ የሚሰጡ የጥንቃቄ መልዕክቶችን እንዲከታተልና በጥብቅ እንዲተገብር የኢፌዲሪ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አሳሰበ። የመሬት መንቀጥቀጡ እስካሁን በከተሞች ምንም ጉዳት አለማድረሱንም አስታውቋል፡፡
አገልግሎቱ እንዳስታወቀው፣ በአፋር፤ ኦሮሚያ እና አማራ ከልል አዋሳኝ አካባቢዎች ማዕከላቸውን አድርገው የተለያየ መጠን ያላቸው የርዕደ መሬት ክሥተቶች በተደጋጋሚ ተከስተዋል፡፡
ክሥተቶቹ ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጠን እና በድግግሞሽ እያደጉ ይገኛሉ። በተለይም በዚህ ሳምንት በርዕደ መሬት መለኪያ እስከ 5.8 ሬክተር ስኬል የተመዘገበ መንቀጥቀጥ መከሠቱን መረጃዎች ያሳያሉ።
መንግሥት ክሥተቶቹን በዘርፉ ባለሞያዎች በቅርብ እየተከታተለ ይገኛል። በተጨማሪም በተለይ የርዕደ መሬቱ ማዕከል (epicenter) የሆኑት አካባቢዎችን በመለየት በ12 ቀበሴዎች ላይ መንግሥት ከተለያዩ የሙያ ዘርፎች የተውጣጡ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች በቦታው በማሰማራት የጉዳቱን መጠን አሠሣ እያደረገ ይገኛል ብሏል።
በእነዚህ ቀበሌዎች ከሚኖሩ 80 ሺህ ዜጎች ቅድሚያ የሚሰጣቸውን በመለየት ነዋሪዎችን ከአካባቢው በማራቅ ለማሥፈር ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ገለጸው መግለጫው፣ በተጨማሪም ርዕደቱ በማኅበራዊ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት፤ በኢኮኖሚ ተቋማት እና በመሠረተ ልማት ላይ ሊኖረው የሚችሰውን ተጽዕኖ በመከታተል ላይ ነው ብሏል።
እስካሁን ባለው ሁኔታ በዋና ዋና ከተሞች የጎላ ተጽዕኖ ያላደረሰ ቢሆንም ዜጎች በባለሞያዎች የሚሰጡ የጥንቃቄ መልእከቶችን እንዲከታተሉና በጥብቅ አንዲተገብሩ አሳስቧል፡፡
በቀጣይም ጉዳዩን በቅርበት በመከታተል አስፈላጊ መረጃዎችን በሚመስከታቸው ተቋማት አማካይነት የሚያደርስ መሆኑን አስታውቋል።
በተመሳሳይ ዜና በአፋርና በኦሮሚያ ክልሎች ከ20 ሺህ 500 በላይ ዜጎች ከርዕደ- መሬት ስጋቱ ቀጠና ወደ ሌላ ስፈራ ተጓጉዘዋል ሲል የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ማስታወቁን ኢቲቪ አስትቃውቋል። ኮሚሽኑ በአፋር እና በኦሮሚያ ክልሎች እየተከሰተ ባለው የርዕደ- መሬት ክስተት ሁኔታና ምላሽን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።
በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ እና ዱለቻ ወረዳዎች እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ፈንታሌ ወረዳ የርዕደ መሬት ከስተት የተፈጥሮ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ደወለን ተከተሎ መንግስት የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ በእስካሁኑ ሁኔታና ምላሽ እየታየ ያለው ስራ አመርቂ ነው ብሏል፡፡
በአፋር ከልል ሁለት ወረዳዎች ማለትም አዋሽ ፈንታሌና ዱለቻ (ዱለሳ) ወረዳዎች ለችግሩ ተጋላጭ ናቸው:: በሁለቱም ወረዳዎች ማለትም በአዋሽ ፈንታሌ ከስድስት ተጋላጭ ቀበሌዎች 15 ሺህ ነዋሪዎች ተጋላጭ ሲሆኑ እስከ አሁን ሰባት ሺህ ወገኖች ከስጋቱ ቀጠና ወደ ሌላ ስፈራ ተጓጉዘዋል፡፡
በዱለቻ ወረዳ ደግሞ 20 ሺህ የሚሆኑ የሁለት ቀበሌዎች ወገኖች ተጋላጭ ሲሆኑ፣ ከነዚህ ቀበሌዎች እስከ አሁን ስድስት ሺህ 223 ህዝብ እካባቢውን ለቀዋል ሲል ኮሚሽኑ በመግለጫው ገልጿል፡፡
በአሮሚያ ክልል ፈንታሌ ወረዳ የአምሥት ቀበሌዎች ወገኖች ለአደጋው ተጋላጭ ናቸው:: በአምስቱም ቀበሌዎች 16 ሺህ 182 ሕዝብ ተጋላጭ ሲሆን እስከ አሁን ድረስ ሰባት ሺህ 350 ሕዝብ ከተጋላጨ ስፍራ ወጥተዋል ነው ያለው ኮሚሽኑ፡፡
ስምንት ሺህ 832 የሚሆኑት ቀሪዎቹ ሰዎች ደግሞ በሚቀጥሉት ቀናት ውስጥ ከስፍራው እንዲንቀሳቀሱ እየተሠራ ይገኛል ብሏል፡፡

አደጋው ሊከሰት ይችላል በተባሉባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ወገኖችን አስቀድሞ ለመታደግ በተጀመረው ዘመቻ የአገር መከላከያ ሰራዊት በዚህ መልኩ ድጋፉን እንያደረገ ነው።
ሰብዓዊ ድጋፍን በተመለከተ እስከ አሁን ለሰባ ሺህ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚሆን 11 ሺህ 550 ኩንታል ምግብ-ነክ እና ለሰባት ሺህ አባወራዎች የሚሆን ምግብ-ነከ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ወደ ስፍራው ተልኳል ሲል ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡
ይህም በገንዘብ ሲተመን ሁለት መቶ ሰማኒያ አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ስልሳ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር የሚገመት መሆኑን አስታውቋል፡፡
ክስተቱን ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲና ከሌሎች የሚመለከታቸው ተቋማት የተውጣጡ የሳይንቲፊክ ኮሚቴ፣ ያለውን ሁኔታ እየተከታተለ ሲሆን መገለጽ ያለበትን ቅድመ-ጥንቃቄዎች አስመልከቶ አስፈላጊው መረጃ ለሕዝብ በተከታታይ የሚቀርብ ይሆናል፡፡ ይህንንም ከኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ማህበራዊ ሚዲያዎችና ድህረ ገጽ መከታተል ይቻላል፡፡
የርዕደ መሬት ንዝረቱ ባለበት አካባቢ ያለ ማህበረሰብ ከንዝረቱ በፊት፣ በንዝረቱ ወቅትና ከንዝረቱ በኋላ ያለውን መወሰድ ያለባቸው ጥንቃቄ እንዲወስዱ አስፈላጊው መረጃ እየተሰጠ ይገኛል ሲልም በመግለጫው ገልጿል፡፡

ምስሉ – የመሬት መንቀጥቀጡ መቋጫዉ እንደሚታየው እንደሚሆን ሳይንቲስቶች እልየተነበዩ ነው። ይህን Africa Is Splitting Apart: A New Ocean Is Forming Faster Than Anyone Predicted ሊንክ ተጭነው ሙሉውን ትንበያ ያንብቡ
