ሙሽራ ሙሽርቲትን ይዞ ወደቤቱ ሊመለስ፣ ቤቱን በትዳር ሊያሞቅ አጃቢዎችን አስከትሎ ወደ ሙሽሪት ቤት ተኳኩሎ እየሄደ ነው። ሙሽሪትም በባህሏና ክብሯ ታጅባ የህይወትን አዲስ መስመር ልትጀምር የትዳር አጋሯ እየተጀነነ ሲገባ ለማየት ደጁ ደጅ ታማትራለች።
የሙሽራ ቤተሰቦች ልጃውን በውላቸው መሰረት ሊያስረክቡ ደግሰው እየጠበቁ ነው። ግን አልሆነም። ሙሽራውን ጨምሮ ከአንድ ቤተሰብ አራት ወንድማማቾችን የነጠቀው፣ 33 የሙሽራ ዘመድ አዝማዶችን ጭጭ ያደረገው አደጋ ይህን ሁሉ ምኞት ጸጥ አደረገው። ወደ ሴቷ ሙሽሪትን ቤት ሲበር የነበረ ሙሽራ ህልም ፈረሰ። “አይጣል” ከማለትና እጅን በአናት ላይ ጭኖ ከመጩ ውጭ ምንም ማደርግ የማያስችል አደጋ!! ሰውነትን የሚፈታተን፣ ዕምነትን የሚገዳደር አደጋ!!
የሰርግና የደስታን ቀን በቅጽበት ቀይሮ ቤተሰብን፣ መንደርንና አካባቢንና ጠቅልሎ ሲኦል ባደረገ ሃዘን ተተካ። አደጋው አጠቃላይ ዜናውን ለሰሙ ሁሉ መራር ሃዘን ሆነ። ይህ ሰባ አንድ ሰዎችን የበላው አደጋ ከአንድ መንደር 52 የሚጠጉ ሰዎች ያለቁበት ነውና ሃዘኑን በተለመደው ሃዘን ለጥራት አዳገተ።
በሳምንቱ መጀመሪያ የተሰማው ይህ እጅግ አስደንጋጭና አሰቃቂ ዜና አንድ ክፍት የጭነት አይሱዚ ተሽከርካሪ የወንድ ወገን ሰርገኞች ጭኖ ሲከንፍ የደረሰ ድንገተኛ አደጋ ነው። የጭነት መኪናው ሙሽራን ከዘመድ አዝማዶቻቸውና የሰርጋቸው ተካፋዮች ጋር አጭቆ ጭኖ ያለሙት ስፍራ፣ በእልልታ ሊቀበሏቸው እተዘጋጁበት ስፍራ አላደረሳቸውም። ሰረገኞች እየጨፈሩ በድንገት ሁሉም ነገር ተቀቀየረ።
ሰረገኞች አጭቆ የጫነው ተሽከርካሪ በድንገት ድልድይ ጥሶ ገባ። በሲዳማ ዞን በቦና ዙሪያ ወረዳ በጋላና ወንዝ ድልድይ ቁልቁል የወረደና የተከሰከሰው የጭነት መኪና ላይ ከተጫኑት ውስጥ ሰባ ሰዎች ጭጭ አሉ። በድንገት የደስታው ጭፈራ ወደ ለቅሶና ዋይታ፣ ጣርና አድኑኝ መቃተት ተለወጠ።
በቅጽበት እስከወዲያኛው የተሰናበቱ፣ በሞትና በህይወት መካከል ሆነው በሚያጣጥሩ፣ በደም ተነክረው በወዳደቁ፣ አደጋውን ዓይተው ለእርዳታ በተሰባሰቡ ሰዎች እሪታ የተዋጠው የአደጋው ስፍራ “ ለማየትም፣ ስለ አደጋው ለመናገርም፣ ዕርዳታ ለማድረግም የሚያስደነግጥ ነበር” ሲሉ የዓይን እማኝ ተናግረዋል።
በዚሁ ዘግናኝ አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ወገኖች የቀብር ስነ ስርዓት ማክሰኞ ዕለት መከናወኑን የሲዳማ ክልል ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት አስታውቋል። በአደጋው ከሰባ በላይ ሰዎች መሞታቸውንም አረጋግጧል። ቁጥር ባይገልጽም ጉዳት የደረሰባቸውና በህይወት የተረፉ ወገኖች በቦና አጠቃላይ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ አስታውቋል።
በቀብር ስነስርዓቱ ላይ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ጨምሮ በርካታ የፓርቲና የክልሉ ባለስልታናት ተገኝተዋል። የዚህ አሰቃቂ አደጋ ሰለባ ለሆኑ ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ ኮሚቴ መቋቋሙና እርዳታ ማሰባሰብ መጀመሩም ተመልክቷል።
በቀብር ስነ-ስርዓቱ ላይ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ህይታቸውን ላጡ ወገኖች ቤተሰብና ዘመዶቻቸው፣ እንዲሁም ሃዘኑ ለጎዳቸው ሁሉ “ መጽናናትን ይስጠን” ብለዋል።
የምስራቃዊ ሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ ማቴ መንገሻ (ዶ/ር) ፥ ” አደጋው የአንድ ቤተሰብና ዘመድ አዝማድ 33 ሰዎችን ከአንድ ቀበሌ የ52 ሰዎችን እንዲሁም ከአንድ ቤት የ4 ወንድማማቾችን ሕይወት የቀጠፈ ነበር ” ሲሉ የአደጋውን ክብደትና የሃዘኑንን መራራነት አሳይተዋል። ከክልሉ መንግስት ጀምሮ መላዉ ሕብረተሰብ የጤናና ፀጥታ መዋቅሩ ላደረገዉ ርብርብ ምስጋና አቅርበዋል።
የሟቹችን ቤተሰቦች ለማፅናናት እና ለማገዝ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱን ገልጸው በገንዘብና በዓይነት የተሰበሰቡና እየተሰበሰቡም ያሉ ድጋፎችን በቀጣይ ለተጓጂ ቤተሰቦች በአግባቡ የማዳረስ ስራ እንደሚሰራ ለቲክቨሃ ከተናገሩት መረዳት ተችሏል።
የጭነት አይሱዙው 11 ሰዓት አካባቢ መነሻዉን ቦና ወረዳ ሚሪዴ ገጠር ቀበሌ አድርጎ ወራንቻ ወደተባለ አጎራበች ቀበሌ የወንድ ወገን የሆኑ ከ70 በላይ ሰርገኞችን ጭኖ ወደ ሴቷ ቤት ጉዞ ላይ ነበር
ገላና ድልድይ ላይ ሲደርስ ግን ድልድዩን ስቶ ወደ ወንዝ ዉስጥ በመግባቱ እስካሁን በተጣራዉ መረጃ አስክሬናቸው ቦና አጠቃላይ ሆስፒታል የደረሰ 66 እንዲሁም ከአደጋዉ ቦታ በቀጥታ ቤተሰቦቻቼዉ የወሰዷቸዉን ጨምሮ በአጠቃላይ 68 ወንድና 3 ሴቶች በድምሩ 71 ሰዎች ሕይወት አልፏል። በ4 ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱንና አንዲት ሴት ወደ ሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል መላኳንም ዶክተር ማቴ ጨምረው ገልፀዋል።
የአደጋው ትክክለኛ መንስኤ እየተጣራ መሆኑን አስተዳዳሪው ተናግረዋል። ” በገጠር አከባቢ በሰርግ እና ደስታ ወቅት በክፍት መኪኖች ላይ ከመጠን በላይ መጫንና አልፎ አልፎም መጠጥ የመቀማመስ ሁኔታዎች ስለሚኖሩ፤ ይህ ለአደጋው አንዱ መንስዔ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል ” ብለዋል።