በሱዳን ያለው አሁናዊ ሆኔታ የሚገለጸው “ሁሉም ነገር እየተበላሸ ነው” በሚል ነው። በሱዳን እየሆነ ያለውና የሆነው ሁሉ በቃላት መገለጽ የማይቻልበት ደረጃ ደርሷል። ይህ ያለው እዛው እሳቱ ውስጥ ያለው የተመድ ተወካይ ነው። ሱዳን እንዲህ የሆነችው የራሳቸው ጥቅም ያላቸው የውጭ ኃይሎች ከሁለት አቅጣጫ ተዋጊዎቹን እየረዱ ፍልሚያ ውስጥ ከተዋቸው ነው። ከጀርባ ያሉትን ኃይሎች አሰላለፍ የሚመረመሩ ለኢትዮጵያ የታቀደው የሱዳን ዓይነት ቀውስ ይሆን? የሚል ጥያቄ ያነሳሉ።
በሱዳን በቁጥር እየገለጹ የተገደሉትን፣ የተሰደዱትን፣ የተፈናቀሉትን፣ ለከፋ ረሃብ የተዳረጉትን፣ በጅምላና በነጠላ የተደፈሩትን፣ የተረሸኑትን፣ አካላቸው የጎደለውን ወዘተ ይፋ ማድረግ አሁን ላይ ቀልድ ሆኗል። በሱዳን ሁሉም ነገር ቀዝቅዟል። እዚህም እዚያም ሞት ነው። ስደትና መፈናቀል ነው። የስልጣን ጥመኞችና ተላላኪዎች በሚያወናጭፉት አረር ህዝብ ይቆላል። እነዚህ ጦረኞች በሚቆጣጠሩት ከተማና መንደር ህጻናትን አስገድደው ይደፍራሉ። እናቶችና አዛውንት አይቀሩዋቸውም። ንብረት ይዘርፋሉ። የመንግስት የግለሰብ ሳይሉ ያገኑትን ሁሉ ያግበሰብሳሉ። የጅምላና የነጠላ እርምጃ ይወስዳሉ። ስርዓት ስለፈርሰ ሱዳን እንዲህ ሆናለች። ከምንም በላይ ህክምና አለመኖሩ በርካቶች እንዲሞቱ ምክንያት ሆኗል።
ኤችአይቪ፣ ስኳር፣ ደም ግፊት፣ አስም፣ መደበኛ የዕለት ተዕለት መድሃኒት የሚያስፈልጋቸው ዜጐች … አልቀዋል። እያለቁ ነው። ወላድ እንዴት እንደሆነች ለፈጣሪ መተው ይበጃል። 20 ሚሊዮን የሚጠጉ ህጻናት ከትምህርት ውጭ ናቸው። በጥቅሉ የተመዱ ሰው እንዳሉት በሱዳን ሁሉም ነገር ተበላሽቷል። ይህ በመሆኑ ይመስላል አሜሪካ ፉክራ አሰምታለች። ከጀርባ ያሉትን የጦርነቱ አቀጣጣዮች ትተው ተላላኪዎቹ ላይ ዝተዋል።
ዩናትድ ስቴትስ ባለፈዉ ማክሰኞ በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ጦር አዛዥ በጄኔራል መሐመድ ሐምዳን ዳግሎ (ሐምዲቲ)ና በቅርብ ቤተሰቦቻቸዉ ላይ ማዕቀብ ከጣለች በሁዋላ በተመሳሳይ ጄኔራል አል ቡርሐንና ተባባሪዎቻቸዉንም በማዕቀብ መቅጣቷ ይፋ ሆኗል።
የፕሬዝደንት ጆ ባይደን መስተዳድር ሥልጣኑን ለማስረከብ 3 ቀን ሲቀረዉ ጄኔራል አል ቡርሐንና ተባባሪዎቻቸዉን በማዕቀብ የወጡበትም ምክንያት የአሜሪካ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር አንተኒ ብሊከን አስረድተዋል። እሳቸው እንዳሉት የሱዳን መከላከያ ጦርም ልክ አንደ ፈጥኖ ደራሹ ጦር ሁሉ ሰላማዊ ሰዎችን ገድሏል።አሰቃይቷል።ሴቶችን ደፍሯልም።
የሱዳን ጦርነት፣ የአሜሪካ ማዕቀብ
የሱዳን የርስ በርስ ጦርነት እንደቀጠለ ነዉ።21ኛ ወሩን በያዘዉ ጦርነት በአስር ሺሕ የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸዉን የተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች አስታዉቀዋል።በጦርነቱ በቀጥታ ከሚሞተዉ ሰዉ በተጨማሪ ተፋላሚ ኃይላት በየደረሱበት ሰላማዊ ሰዎችን መግደል፣ ማሰር፣ ሴቶችን መድፈራቸዉን የራስዋ የሱዳንና ዓለም አቀፍ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች በየጊዜዉ እየዘገቡ ነዉ።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንዳስታወቀዉ ከ12 ሚሊዮን የሚበልጡ የሱዳን ዜጎች አንድም ከቤት ንብረታቸዉ ተፈናቅለዋል ሁለትም ተሰድደዋል።ከሱዳን ህዝብ ከግማሽ የሚበልጠዉ ማለትም 25 ሚሊዮን ሕዝብ ለከፋ ረሐብና ችግር ተጋልጧል።ሕዝቡ የምግብ፣ የመድሐኒትና የመጠለያ ድጋፍ እንዲያገኝ የሚደረገዉ ጥሪ አሁንም እንደቀጠለ ነዉ።
ሰብአዊ ቀውሱ ስር የሰደደባት ሱዳን ሶስት ሚሊዮን ዜጎቿ አገር አልባ ሆነዋል። ተሰደዋል። ለመከራ ተዳርገዋል። የተመድ የሱዳን የስደተኞች አስተባባሪ ማማዱ ዲያን ባልዴ በቀጣይ ሁለትና ሦስት ሳምንታት የተፈናቃይ ስደተኞች ቁጥር ከሦስት ሚሊዮንም ሊበልጥ እንደሚችል ለፈረንሳይዜና አገልግሎት(AFP)ተናግረዋል።
ስለዚህ አሁን የገጠመን ምናልባትም በቅርብ ዐሥርተ ዓመታት ውስጥ ካየነው ከለላ የማጣት ቀውስ የከፋውን ነው ። ያሳዝናል። ይህ ሁሉ የሚሆንባት አገር ያቺው የዛሬዋ ሱዳን ነች »
ጥቂት እውነታዎች
- ከ18 ወራት ባነሱ ጊዜያት ውስጥ ከ3 ሚሊዮን ያላነሱ ዜጎች ሀገር ጥለው መሰደዳቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል።
- ከነዚህ የሱዳን ስደተኞች መካከል 25,000 ያህሉ ባላፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ ቻድ የገቡ ናቸው።
- ድንበር እየተሻገሩ ከሚሸሹት ተፈናቃዮች መካከል 80 በመቶው ሕጻናት እና ሴቶች ናቸው።
- እርዳታ ሰጪ ተቋማት በሚፈለገው ደረጃ የሉም። የገበያ ሥፍራዎች በየጊዜው እየተደበደቡ መሆናቸውን ተፈናቃዮች አማራጭ አጥተዋል።
- ከ12 ሚሊዮን የሚበልጡ የሱዳን ዜጎች ከቤት ንብረታቸዉ ተፈናቅለዋል።
- 25 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰላማዊ ዜጎች ለከፋ ረሃብ ተጋልጠዋል።
- ከ17 ሚሊዮን በላይ ህጻናት ከትምህርት ገበታ ውጭ ሆነዋል። ሁማን ራይትስ ዋች 2025 ረፖርት
- ሁለቱም የስልጣን ጥመኞች የሚጠቀሙት እጅግ ከባድ መሳሪያ ሳቢያ 110 ጊዜ የአሳት ቃጠሎ ተመዝግቧል።
- ህጻናት ሳይቀሩ ተደፍረዋል። እየተደፈሩ ነው። የጾታ ጥቃቱ በጥቅሉ እድሜ አይመርጥም።
- የተደፈሩት እህቶች በጦርነቱ ሳቢያ የጤና አገልግሎት አለማግነታቸው ችግሩን የከፋ አድርጎታል።
- አገሪቱ ነዳለች። መሰረተ ልማቷ ወድሟል።
«ሁኔታው እየተበላሸ፤ በጣም እየተበላሸ ነው » ሲሉ የተመድ ሃላፊ የሱዳንን ችግር ይገልጻሉ። ችግሩ በቃል ሊገለጽ የማይችልበት ደረጃ ቢደርስም ሁለቱም ተዋጊዎች ስለ ስላም፣ ድርድርም ሆነ ለጊዜው ህዝብ ስለሚረዳበት አግባብ ምንም ሲናገሩ አይሰማም።
እዚህ ጋር ቆም እንበልና ስለ ኢትዮጵያ እናስብ። ላለፉት ስድስት ዓመታት በኢትዮጵያ የሆነውን እንገምግም። ዛሬ ለአገር መከላከያ ምስጋና ይግባውና አንጻራዊ ሰላም ባይሰፍን ኖሮ እንደ አጅማመሩ፣ ከጀርባ እንደነበሩት ኃይሎች ፍላጎት ምን ሊከሰት ይችል እንደነበር ሲቃኝ አስደንጋጭ ነው። አሁንም አልፎ አልፎ በኦሮሚያ፣ በከፋ ሁኔታ በአማራ ክልል እየሆነ ያለው ለሚያስተውሉ ሁሉ “ለኢትዮጵያም የታቀደው እንደሱዳን ይሆን?” የሚል ጥያቄ ያጭርባቸዋል።
የትህነግ 270 ሺህ ጦር አቋም ገባ ወጣ በሚልበት፣ የጦሩ መሪዎች አቋም ግልጽ ባልሆነበት፣ ሂድ፣ ግፋ የሚሉ ድምጾች በሚሰሙበት ሁኔታ ነቅቶ አለማሰብ ጣጣ እንዳለሚያስከትል በርካታ የወደፊቱ የገባቸው እየመከሩ ነው። አሁን ላይ ሱዳን ላይ የሆነው ሊሆን የሚችልበት ስሌቱ የዜሮ ብዜት ቢሆንም፣ ድግሱ በተለይም በግብጽና ኤርትራ በኩል ኢትዮጵያን አፈራርሶ በጎበዝ አለቆች እጅ ማስገባትና የዕልቂት አውድማ ማድረግ ነውና ከላይ በሱዳን የሆነውንንና እየሆነ ያለውን በማስላት ህዝብ እንደወትሮ አንድነቱን ሊያጠብቅ፣ ሊጠብቅ፣ ለተላላኪዎች አሳብ ጀርባ በመስጠት በህብረት ሊተጋና አገርና ፖለቲከኞችን በመለየት እንዲጓዝ ምክር የሚሰጡ አሁንም ጥቂት አይደሉም።
ሱዳን እንዳሉት ኢትዮጵያ ውስጥም ተላላኪዎች አሉ። ሱዳን እንዳለው ኢትዮጵያ ውስጥም ተላላኪዎቹ የታጠቀ ቡድን አላቸው። ልክ ሱዳን እንደሆነው ሁሉ ተላላኪዎቹን በሰፈሩባቸው ዋሻዎችና ገጠሮች እየሆነ ነው። የደቦ ፍርድ አለ። ትምህርት ቤት መማር አልተቻለም። ህክምና ማግኘት፣ መድሃኒት መጠቀምና …. የተነፈጉ ዜጎች አሉ። አልፎ አልፎ የሚወጡ የስዕልና የድምጽ መረጃዎች እንደ ዜጋ አስደንጋጭ፣ አሳዛኝ፣ ኢትዮጵያዊ ጠረን የሌለው፣ ምን እንደሚፈለግ እንኳን በግልጽ ለመረዳት የሚጓጉጥ፣ እንደው ዝም ብሎ የመንጋ እሳቤና የደንቆሮ ጩኸት የሚመስል አደገኛ ነገር ነው። ይህ የውጭ ኃይሎችን ጥቅም ለማሳካት በብሄር ስም ታጅሎ የሚቀነቀን ነውጥ እየመከነ ቢሆንም አደጋው ሙሉ በሙሉ ሊጸዳ ይችል ዘንድ ልብ ያላቸው ልብ ሊሉት ግድ ነው።
ቀደም ሲሉ የሱዳን ፈጣን ኃይል መሪ ጄነራል መሀመድ ሃምዳን ዳግሎን ይደግፉ የነበሩት ፕረዚዳንት ኢሳያስ በግብጽ አማካይነትና ሙሉ እገዛ የሙስሊም ኃይሎችን አሰልጥናና አስታጥቃ ጄኔራል አል ቡርሐን በይፋ እያገዘች ነው። ግብጽ የአየር ኃይል ድጋፍ ያካተተ ሙሉ የጦር ድጋፍ የምትሰጣቸው ጄኔራል አል ቡርሐን በሱዳን ባለው የትህነግ ኃይልም ይረዳሉ። ከዚህ ቀደም በርካታ የትግራይ ተዋጊዎች ተማርከው የሚያሳይ ቪዲዮ በይፋ በፈጥኖ ደረሻ ኃይሎች አማካይነት መሰራጨቱ ይታወሳል። ሰሞኑንንም ዳጋሎ በተመሳሳይ ኤርትራና ትህነግ ጠቅሰው ጄኔራል አል ቡርሐንን እየረዱ መሆኑን ተናግረዋል። የጄኔራል አል ቡርሐን ጦር ብልጫ የያዘውም በዚሁ በትብብር በሚደረግ ጦርነት መሆኑን አስታውቀው ዝተዋል።
የአል ቡርሐን ድርብ ድል፣ የሐምዲቲ ሽንፈት
በዉጊያዉ አዉድ ጄኔራል አብዱል ፈታሕ አል ቡርሐን የሚመሩት የሱዳን መከላከያ ጦር ባለፈዉ ሳምንት ድርብ ድል ተቀዳጅቷል።ዩናትድ ስቴትስ ባለፈዉ ማክሰኞ በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ጦር አዛዥ በጄኔራል መሐመድ ሐምዳን ዳግሎ (ሐምዲቲ)ና በቅርብ ቤተሰቦቻቸዉ ላይ ማዕቀብ ጥላለች።የአሜሪካ ባለሥልጣናት እንዳሉት እርምጃዉን የወሰዱት ሐምዲቲ የሚያዙት ጦር ባልደረቦች ሰላማዊ ሰዎችን ጎሳ እየለዩ መግደል፣ ማሰቃየት፣ ሴቶችን መድፈራቸዉንና ዘር ማጥፋታቸዉን የሚያረጋግጥ መረጃ ስለደረሳቸዉ ነዉ።

21ኛ ወሩን በያዘዉ በሱዳን የርስ በርስ ጦርነት በአስር ሺሕ የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰዎች መግደሉን የተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች አስታዉቀዋልምስል AFP
በቅጣቱ መሠረት ሐምዲቲና ቤተሰቦቻቸዉ አሜሪካ መግባት አይችሉም፤ አሜሪካ ዉስጥ የሚገኝ ሐብትና ንብረታቸዉን ማንቀሳቀስ አይችሉምም።እርምጃዉ ለአል ቡርሐንና ለተከታዮቻቸዉ ምስራች ብጤ ነዉ።ሐምዲቲ በሳቸዉና በቤተሰቦቻቸዉ ላይ የተጣለዉን ማዕቀብ ሲያብሰለስሉ አልቡርሐን የሚያዙት ጦር ዋድ ማዳኒ ላይ ሁለተኛዉን ድል አስመዘገበ።
ጦሩ አል ጀዚራ በተባለችዉ የማዕከላዊ ሱዳን ግዛት ላይ በከፈተዉ ጥቃት የፈጥኖ ደራሽ ኃይላትን ደምስሶ የግዛቲቱን ርዕሰ ከተማ ዋድ ማዳኒን ባለፈዉ ቅዳሜ ተቆጣጥሯል።ባንድ ሳምንት ድርብ ድል።
ከተማይቱን የተቆጣጠረዉን ጦር የሚያዙት የሱዳን መከላከያ ጦር ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሸምስ አል ዲን እንዳሉት ጦራቸዉ ለድል የበቃዉ ከሕዝብ የወጣ፣ ለሕዝብ የቆመና ከሕዝብ ጋር በመተባበር የሚዋጋ በመሆኑ ነዉ።
«መመኪያችን ሕዝባችን ነዉ።የምንዋጋዉ ለሕዝብና ከሕዝብ ጋር ተባብረን ነዉ።ከሕዝብ የወጣን የጦር ኃይል ነን።የዚች ሐገርና የዚሕ ሕዝብ አካል ነን።»
የድርብ ድሉ ፌስታ ግን አንድ ሳምንት አልቆየም።
የአሜሪካ ማዕቀብ በአል ቡርሐን ላይ
እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የሱዳን ተፋላሚዎችን በማደራደር፣ ለችግረኛዉ ሕዝብ ርዳታ በማቅረብና ለድርድርና ርዳታዉ ሌሎችን ለማስተባበር ብዙ መጣራቸዉን ብዙ ጊዜ የሚናገሩት የአሜሪካ መሪዎች ጄኔራል ሐምዲቲ ላይ ያደረጉትን ጄኔራል አል ቡርሐንም ላይ ደገሙት።የፕሬዝደንት ጆ ባይደን መስተዳድር ሥልጣኑን ለማስረከብ 3 ቀን ሲቀረዉ ትናንት ጄኔራል አል ቡርሐንና ተባባሪዎቻቸዉን በማዕቀብ ቀጥቷል።ምክንያት፣ የአሜሪካ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር አንተኒ ብሊከን እንዳሉት የሱዳን መከላከያ ጦርም ልክ አንደ ፈጥኖ ደራሹ ጦር ሁሉ ሰላማዊ ሰዎችን ገድሏል።አሰቃይቷል።ሴቶችን ደፍሯልም።በጥቅሉ የጦር ወንጀል ፈፅሟል የሚል ነዉ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንዳስታወቀዉ ከ12 ሚሊዮን የሚበልጡ የሱዳን ዜጎች አንድም ከቤት ንብረታቸዉ ተፈናቅለዋል ሁለትም ተሰድደዋልምስል ERRFC
«ከጥቂት ቀናት በፊት በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ጦር (RSF) ላይ የወሰድነዉን ርምጃ ታቁታላችሁ።የሱዳን መከላከያ ጦር ኃይል (SAF)ም የጦር ወንጀል አድርሷል።ሰላማዊ ሰዎችን ማጥቃቱን ቀጥሏልም።የሰላም ጥረቱ እንዳይቀጥል አደናቅፏል።ባዘጋጀናቸዉ በቡዙ የሰላምና የተኩስ ማቆም ድርድር ሂደቶች ላይ እልካፈልም ብሏል።SAFና RSF በዓለም በጣም ከፍተናዉን የሰብአዊ ቀዉስ አስከትለዋል።»
የአሜሪካን ርምጃ ሁለቱም ተፋላሚ ወገኖች አጥብቀዉ ተቃዉመዉታል።ዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ትናንት በአል ቡርሐን ላይ የወሰዱት ርምጃ ለጄኔራል መሐመድ ሐምዳን ዳግሎ ምናልባት መፅናኛ ሊሆን ይችላል።ጦርነቱን ለማስቆም ግ የሚተርከዉ ነገር የለም።የባይደን አስተዳደርም ከጋዛ እስከ ሱዳን፣ ከዩክሬን እስከ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ዲፕሎማሲዉን-ከቅጣት፣ ድርድርን ከጦርነት እንዳወነካከረ ሰኞ-አዲዮስ።
የጀርመን-አፍሪቃ ግንኙነት አዲስ የሥራ መመሪያ
የጀርመን መንግሥት ጀርመን ከአፍሪቃ ጋር ያላትን ግንኙነት ገቢር የሚያደርግበትን አዲስ የሥራ መመሪያ ሰሞኑን አዉጥቷል።መመሪያዉ ይፋ የሆነዉ በፊት ከታቀደዉ 6 ወር ዘግይቶ፣ ጀርመን በመጪዉ የካቲት ምርጫ ለማድረግ በተዘጋጀችበት ወቅት በመሆኑ ማነጋገሩ አልቀረም።
በመከባበር ላይ የተመሠረተ
በ34 ገፅ የተጠረዘዉ መመሪያ «አንዱ ሌላዉን ማክበር» የሚለዉ ፅንሐሳብ የጥቅል ግንኙነቱ ዋና ማጠንጠኛ መሆኑን ይገልፃል።ጀርመን በቅኝ አገዛዝ ዘመን አፍሪቃ ዉስጥ ላደረሰችዉ በደል አፍሪቃን መካስ እንደሚገባትም መመሪያዉ ጎላ ያለ ሥፍራ ሰጥቶታል።በጀርመን ምክር ቤት የሶሻል ዴሞክራቶቹ ፓርቲ (SPD) የዉጪ ግንኙነት ኮሚቴ ቃል አቀባይ ኒልስ ሽሚት እንደሚሉት ያለፈዉን ዘንግቶ ያሁኑን የጀርመን-አፍሪቃ ግንኘት ማዉሳት አይቻልም
«ባለፈዉ የቅኝ አገዛዝ ዘመን የተፈፀመዉን ገድፈን አሁንና ወደፊት ከአፍሪቃ መንግስታትና ማሕበረሰብ ጋር ያለንና የሚኖረንን ግንኙነት ይዘት መቅረፅ አንችልም።»
መመሪያዉ ጀርመን አፍሪቃ ላይ የፈፀመችዉን ወንጀል ማመን፣ከአፍሪቃ የዘረፈቻቸዉን ቅርሶችንና የሰዎች ቅሬተ አፅሞችን መመለስ እንደሚገባት ያወሳልም።በፍራይቡርግ ዩኒቨርስቲ የአፍሪቃ ማዕከል ኃላፊ አንድሪያስ ሜሕለር መመሪያዉ ለመከባበርና ለጋራ መተሰባሰብ ትልቅ ስፍራ መስጠቱን ያደንቃሉ።
«እንደሚመስለኝ ሰጥቶ-የመቀበል ፅንሠ ሐሳብ መካተቱ በጣም ጥሩ ነዉ።ከዚሕ ቀደም ይሕን ሐሳብ አላየሁም ነበር።»
ይሁንና ጀርመን በቅኝ ገዢነቷ ዘመን ላደረሰችዉ በደል ካሳ መስጠትና እርቅ ማዉረድን በሚያወሳዉ ክፍሉ የጠቀሳት ሐገር አንድ ናት።ናሚቢያ።ፕሮፈሰር አንድሪያስ ሜሕለር እንደሚሉት ታንዛኒያና ካሜሩንም መካተት ነበረባቸዉ።
በጀርመን ምክር ቤት የዉጪ ጉዳይ ኮሚቴ አባልና የአረንጓዴዉ ፓርቲ ፖለቲከኛ ጀሚላ ሼፈር መመሪያዉ ከዚሕ ቀደም እንደነበሩት ከላይ ወደታች የሚወርድ ግንኙነትን ሳይሆን በእኩልነት ላይ የተመሠረተ ግንኙነትን የሚያሰርፅ ነዉ ባይ ናቸዉ።
እኩልነት በዓለም አቀፍ መድረክ
የጀርመን ፌደራል ሪፐብሊክ መንግሥት አፍሪቃs በዓለም አቀፍ ፖለቲካ ከፍ ያለ ሥፍራ ሊኖራት ይገባል የሚለዉን ሐሳብ ይቀበላል።አፍሪቃ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት ዉስጥ ሁለት ቋሚ መቀመጫዎች ሊኖራት ይገባል የሚለዉን ሐሳብም ይደግፍል።የSPDዉ ፖለቲከኛ ኒልስ ሽሚት ሩሲያ ዩክሬንን መዉረሯና የጋዛዉ ጦርነት አፍሪቃ በዓለም የፖለቲካ መድረክ ያላትን ተሳትፎ አስፈላጊነት ይበልጥ ያጎላዋል ይላሉ።
«ሥለአፍሪቃ ብቻ ሳይሆን፣ የአፍሪቃ ሐገራትና ማሕበረሰብ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚኖራቸዉ ሚናም መወሳት አለበት።ሩሲያ በዩክሬን ላይ የከፈተችዉ ጥቃትና የጋዛዉ ጦርነት የዘመኑ የዉጪ ፖለቲካ ለአዉሮጳና ለሰሜን አሜሪካ ብቻ የሚተዉ ሳይሆን ሌላዉን የዓለም ክፍል የሚያሳትፍ መሆን እንዳለበት በግልፅ አሳይተዉናል።አፍሪቃ በትክክል አንዷ ናት።»
በአዲሱ መመሪያ መሠረት የጀርመን መንግስት፣ ተቋማትና ማሕበራት ከአፍሪቃ መንግሥታት ጋር ብቻ ሳይሆን ከአሐጉሪቱ የሲቪል ማሕበራትና ከወጣቶች ጋር ጠንከር ያለ ግንኙነት እንዲኖራቸዉ ያሳስባል።በተለይ የአፍሪቃ ወጣቶችን «ከጀርመንና ከአዉሮጳ ጋር ወደፊት የሚኖረዉን ግንኙነት የሚወሰኑ።» ይላቸዋል።
የአምባገነን ዝንባሌ ካላቸዉ መንግሥታት ጋርስ?
በ2019 (እግአ) የታተመዉ መመሪያ ጀርመን ከአፍሪቃ ሐገራት ጋር የሚኖራት ግንኙነት ለፀጥታና መረጋጋት ቅድሚያ ትኩረት የሚሰጥ ነበር።በአምባገነኖችና የአምባገነንነት ዝንባሌ ባላቸዉ ወገኖች ለሚገዙ ሐገራት ብዙም የተለየ አቀራረብ አልነበረዉም።
አዲሱ መመሪያ ግን ባለፉት ጥቂት ዓመታት በሳሕል አካባቢ ሥልጣን ከያዙ የጦር መኮንኖችና በአምባገነኖች ከሚገዙ የአፍሪቃ ሐገራት ጋር ጀርመን ለሚኖራትን ግንኙነት መንታ-ሥልት ቀይሷል።ከአምባገነኖችን ወይም የአምባገነት ዝንባሌ ያላቸዉ መንግስታትን በግልፅ «እየተቹ ግን መነጋገር» አንዱ ነዉ።በዚሕ ረገድ ለምሳሌ የዓየር ንብረት ለዉጥን ለመከላከል መወሰድ በሚገባቸዉ እርምጃዎች ላይ መነጋገር የግድ ያክል አስፈላጊ ነዉ።በነዚያ ሐገራት የተለያዩ አመለካከቶች፣ሐሳብን በነፃነት የመናገርና ብዝሐነትን ማበረታት-ሁለተኛዉ።
በጀርመን ምክር ቤት የወግ አጥባቂዉ የክርስቲያን ሶሻል ሕብረት (CSU) እንደራሴ ቮልፍጋንግ ሽቴፊንገር ግን «ከሩሲና ከቻይና ጋር የተጣበቁ የአፍሪቃ አምባገነኖችን መመሪያዉ እንደዘበት አልፏቸዋል ባይ ናቸዉ። «ቻይናና ሩሲያ በአፍሪቃ አሐጉር ያላቸዉን ሚና (ለመቋቋም) በመመሪያዉ በግልፅ የተባለ ነገር የለም።»
ምጣኔ ሐብት ግንኙነትን በተመለከተ ያመለጠ ዕድል
ወግ አጥባቂዉ ፖለቲከኛ ሽቴፊንገር ጀርመን ከአፍሪቃ ጋር ሊኖራት የሚገባዉ ምጣኔ ሐብታዊ ግንኙነትና ማግኘት የነበረባትን ጥቅም አጥታለች ባይ ናቸዉ።ያመለጠ ዕድል።የጀርመን ምጣኔ ሐብት የአፍሪቃ ማሕበር ኃላፊ ክርስቶፍ ካኔንጊሰርም የCSUዉን ፖለቲከኛ ሐሳብ ይጋራሉ።ካኔንጊሰር እንደሚሉት በምጣኔ ሐብቱ ረገድ የጀርመን መንግሥት ተለዋዋጩን የዓለም የምጣኔ ሐብትና የፖለቲካ ሁኔታ አጢኖ ጀርመን ከአፍሪቃ ጋር ሊኖራት ለሚገባዉ ግንኙነት ብዙም ትኩረት አልሰጠዉም።
የጀርመን ካፍሪቃ ጋር ሥለሚኖራት ግንኙነት የሚደነግገዉ መመሪያ ይወጣል የተባለዉ ባለፈዉ የግሪጎሪያኑ ሐምሌ ማብቂያ ነበር።6 ወር ዘግይቷል።በመጪዉ የካቲት 23 ደግሞ ጀርመን ዉስጥ ምርጫ ይደረጋል።በምርጫዉ አሁን በሥልጣን ላይ ያለዉ የመራሔ መንግሥት ኦላፍ ሾልስ የSPD-አረንጓዴዎቹ መንግስት ከተሸፈ መመሪያዉ ገቢር መሆኑ እንዳጠያየቀ ነዉ።
የፖለቲካ ሳይቲስት አንድሪያስ ሜሕለር ግን መመሪያዉ ሁሉንም ፓርቲዎች በአብዛኛዉ የሚያግባባ በመሆኑ መንግሥት ቢቀየርም ገቢር ሊሆን ይችላል ይላሉ።የተቃዋሚዉ የCSU ፖለቲከኛ ሽቴፊንገር ግን የሳቸዉ ፓርቲና ተባባሪዉ የክርስቲያን ዴሞክራቶቹ ሕብረት (CDU) ሥልጣን ከያዙ ሌላዉ ቢቀር ምጣኔ ሐብትን የሚመለከተዉ የመመሪያዉ ክፍል መቀየሩ አይቀርም።
ዘገባው ከጀርመን ድምጽ፣ ከሂውማን ራይትስ ዎች፣ እንዲሆንም ከተለያዩ አስተየትፕች ተወስዶ የተሰራ ነው