“ልጅ እያለሁ እንደንማኛውም ልጅ ብዙ ምኞትና ተስፋ ነበረኝ። አድጌ፣ ተመርቄ፣ ስራ ይዠ፣ ሚስት አግብቸ፣ ልጆችን ወልጀ፣ በቤተክርስቲያን በዘማሪነት እያገለገልኩ በደስታና በስኬት የመኖር ትልቅ ህልምና ተስፋ ነበረኝ። ነገር ግን ከዚህ ሁሉ አንዱም አልተሳካልኝም። ምክንያቱም 18 ዓመት ሲሆነኝ በአንድ በተረገመች ዕለት ምንም በማላውቀው ጉዳይ ፖሊሶች በዘረፋ ተጠርጥረሀል አሉና ያዙኝ። ኧረ ንፁህ ነኝ ብልም የሚሰማኝ ጠፋና ተዘርፈዋል የተባሉት ሰዎች ይመስላል ስላሉ ብቻ የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደብኝ። ያለ ጠያቂ ለ54 ዓመታት በአንድ ክፍል ውስጥ ተቆለፈብኝ።
መጀመሪያ አካባቢ ተስፋ ቆረጥኩ። ቆየት ብዬ ግን ይህ ነገር የእግዚአብሔር አላማ ይሆናል ብዬ በፀጋ መቀበል ጀመርኩ። ከዚያም ያለ አጃቢ ባንድ፣ ያለ ምንም ሙዚቃ መሳሪያ፣ በባዶ ክፍል ውስጥ በየቀኑ እግዚአብሔርን በመዝሙር ማመስገን ጀመርኩ። ብዙ አመታት ያለምንም ለውጥ ነጎዱ…
ከ54 ዓመታት በኃላ መዝገቤን በአጋጣሚ ሲያየው አላግባብ እንደተፈረደብኝ የተገነዘበ አንድ ወጣት የህግ ባለሙያ ወደእኔ መጣና ጉዳዬ እንደገና እንዲታይ(Judicial review) ሊያደርግ እንደሆነ ነገረኝ። ተስፋ ባላደርግበትም ይቅናህ አልኩት። በአጭር ጊዜ ውስጥ ጉዳዩን እንደገና አሳይቶ በ72 ዓመቴ በነፃ እንድለቀቅ አደረገኝ።
ስወጣ ግን ምንም ነገር አላገኘሁም። ቢሆንም እግዚአብሔር ይመስገን እዚያ እያለሁ በነፃነት በመኖራቸው እቀናባቸው የነበሩት ብዙዎች በህይወት የሉም። እኔ ግን ዛሬ ላይ ንፁህ አየር እየተነፈስኩ የማለዳ ፀሀይ በነፃነት እየሞቅኩ በህይወት አለሁ። በህይወት መኖር ብቻ ሳይሆን አንድ ቀን በህዝብ ፊት እዘምራለሁ ብዬ ስመኘው የኖርኩት ምኞቴ እውን ሆኖልኝ ይሄው በእናንተ ፊት ቆሜ እግዚአብሔርን ላመሰግን ስለሆነ ደስተኛ ነኝ” አለና በለስላሳ ድምፁ….
“በሀሰት በከሰሱኝ ጊዜ፣ የሚሰማኝ አጥቸ በተፈረደብኝ ጊዜ፣ ከ50 ዓመታት በላይ ያለበቂ ምግብና ልብስ፣ ያለጠያቂ ወገን በአንድ ክፍል ውስጥ በተዘጋብኝ ጊዜ፣ አለም ሁሉ በረሳኝ ጊዜ፣ አበቃልኝ ብዬ ተስፋ ቆርጨ ቀኑም ሌቱም በጨለመብኝ ጊዜ ከጎኔ ያልተለየኸው አባቴና አምላኬ እግዚአብሔር ሆይ ከልቤ አመሰግንሀለሁ!” እያለ በእንባ ታጅቦ መዝሙሩን ያንቆረቁረው ጀመር።
ይህኔ ከአወዳዳሪዎች እስከመድረክ አስተናባሪዎች፣ ከታዳሚዎች እስከጥበቃዎች አዳራሹ በሙሉ በለቅሶ ተናጋ።
መልካም ጊዜ!
©ከሀቅ እና ድንቅ ገጽ የተወሰደ
TIPS
Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security