የአገሪቱን ኢኮኖሚ እያናጋ ያለው ዋናው የተልዕኮ ወይም የውክልና ጦርነት በገዛ አገራቸው ላይ የከፈቱ፣ እነዚህኑ አካላት እያደናንቁ ሳንቲም የሚለቅሙ ሚዲያዎችና አነብናቢዎች በዋናነት ይጠቀሳሉ።
ክለውጡ ጊዜ ጀምሮ አገሪቱ የገባችበት የተቀነባበረና አሁን ገሃድ እየወጣ ያለው የተናበበ ጥቃት ኢኮኖሚውን ክፉኛ ጎድቷል። የሚገርመው የዚህ የፍጅትና የተቀነባበረ ጥፋት መሃንዲሶች ተመልሰው “ዋጋ ናረ፣ ኑሮ ተወደደኤ እያሉ መጮሃቸው ነው።
በአሻጥር ሸቀጥ፣ ነዳጅ፣ መድሃኒት፣ ማዳበሪያ ወዘተ የሚደብቁ፣ ወደ ህዝብ እንዳይደርሱ መንገድ የሚዘጉ፣ የሚዘርፉና የሚያቃጥሉ፣ ገበሬ ምርቱን አውጥቶ እንዳይሸጥ የሚከለኩትን የሚያደንቁ ዛሬ የዚህ ሁሉ ድምር የሆነውን የዋጋ ንረት “በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ” እያሉ በማቆለመጥ የአመጽ ነጋሪት ያውጃሉ። እነዚህ ወገኖች ሰሞኑን ቤንዚን ተሸክመው በየበረሃው እተደበቁ ህዝብ ለመግፈፍ ሲያደቡ የነበሩትን አሳፋሪ ሌቦች ምንም አይሏቸውም። ድርጊቱ የሴራው አንዱ አካል በመሆኑ ዝታን መርጠው የአመጽ ድምጽ ያሰማሉ። ተቆርቋሪነታቸው የህዝብ ጉዳይ ቢሆን ኖሮ ይህ አይሆንም ነበር። ህዝብ ያውቃል።
በገፊና ጎታች የተሳለጠ የጥፋት ስትራቴጂ ላይ ላዩን ጠላት መስለው ለዓመጽ ሲባል ህዝብ የሚፈጁት፣ ዛሬ አንድ መሆናቸውን ይፋ እያደረጉ ነው፣ እያደነቁ ሰባት ቀን ሃያ አራት ሰአሳት የሚጮሁ እንደሚሉት ህዝብ ማመጽ አለበት።
የጠብ መንጃው ዘመቻ አልሳካ ሲል፣ የጥቁር ልበሱና ሃይላኖትን ሽፋን ያስደረገው የጥፋት ርብርብ ሲኮላሽ ዛሬ የተያዘው አዲሱ ቅስቀሳ ደግሞ የኢኮኖሚ አመጽ ማቀጣጠል ነው። ነውጥ አስነስተው አገሪቱን ለማን ሊያስረክቧት እንደሆነ የማያስታውቁን ተላላኪዎች ይህን ይመስላሉ።
መንግስት ጎን ያለው ድክመትና በውስጡ የተሰገሰጉ ሌቦች ጉዳይ እንዳለ ሆኖ ህዝብን ተስፋ ቢስ ለማድረግ ሌት ተቀን የሚሮጡ አካላት ከዚህ ተግባራቸው ተቆጥበው አገሪቱ ወደ ሰለጠን ፖለቲካ እንድትሸጋገር ቢገፉ ብዙ ባተረፍን ነበር።
አንድ ሀቅ ( Mootii Oroo )
ከIMF ጋራ ያደረገው ረዥም ግዜ በፈጀ ድርድር ስምምነት ላይ መድረሱ እና ሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተግባራዊ መደረጉ ተከትሎ፣ አንድ አንድ አለም አቀፍ ሁኔታዎች እና ኢኮኖሚያችንን ያሳመሙ ሀገር ውስጥ የሰላም ሁኔታን ተከትሎ፣ መንግሥት አንድ አንድ አገልግሎቶች ላይ የክፍያ ጭማሪ ለማድረግ እንደሚገደድ፣ ከመንግስት ለዜጎች በድጎማ የሚያቀርቡት ምርቶች ላይ መንግሥት ድጎማውን እንደሚያነሳ ይጠበቅ ነበረ።
በዚህው መሰረት ውሃ፣ ማብራት እና ቴሌኮም ክፍያ ላይ ጭማሪ ተደርጓል። የነዳጅ ሽያጭ ላይ መንግሥት ሲያደርግ የነበረውን ድጎማ ቀስ በቀስ እያነሳ ይገኛል። ከተወሰነ ግዜ ቦሃላ ነዳጅ ከአረብ አገሮች ከተገዛበት ዋጋ ላይ ትርፍ፣ የትራንስፖርት የመሳሰሉ ወጪዎች ተጨምሮበት እንዲሸጥ እንደሚደረግ ይጠበቃል።
እነዚህ ጭማሬዎች ደግሞ ብዙ ሚልዮን ዜጎቻችን ላይ ከፍተኛ ጫና እንደሚያድሩ የሚጠበቅ ነው። ዜጋ በብዙ Suffer ያደርጋል ይሄ የሆነው አለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ሁኔታዎች ለመንግሥት አስገዳጅ ስላደረጉ እንደሆኑ ልብ በሉልኝ።
እነዚህ የዋጋ ማሻሻያዎች መንግስት እንዲያደርግ ከሚያስገድዱ ጉዳዮች መካከል ሀገራችንን ለማፍረስ የውጭ ጠላቶቻችን ያሰማሩት፣ ሸኔ ፣ፋኖ እና የማሳሰሉ የሀገር ውስጥ የጥፋት ሀይሎች ጋር እየተካሄደ ያለው ጦርነት ዋነኛ Factor ነው ።
በኢትዮጵያ እየተካሄዱ ያሉ ጦርነቶች የሚወድሙ ሀብቶች በተጨማሪ፣ ጦርነቱን ለማካሃድ መንግሥት የሚያወጣ ወጪ ሀገርን ለከፍተኛ ወጪ ይዳርጋል። ወጪውን ለመሸፈን ደግሞ መንግሥት ብዙ ገቢ መሰብሰብ አለበት፣ በሌላ በኩል ደግሞ ወጪዎቹን መቀነስ አለበት። የወጪ ቅነሳ ስርዓት ደግሞ አንዱ ድጎማዎችን ማንሳት ወይንም ድጎሞ መቀነስ አንደኛ ነው።
ጠቅላይ ሚንስትራችን በአንድ ወቅት “ድሮን የሚተኩሰው ዶላር ነው” ብሎ እንደገለጹት፣ በጦርነቱ ላይ የሚቀርቡ እያንዳንዱ ሎጂስትኮች ገንዘብ ነው፣ የሀገር ኢኮኖሚ ነው። ክላሹ፣ ታንኩ፣ መድፉ፣ የመሳሰሉት እና ተተኳሾቻቸው ….
ወታደር መልምሎ፣ አሰልጥኖ፣ አስታጥቆ ከሸኔ እና ከፋኖ ጋራ ለመዋጋት ሀገር ከጥፋት ለመታደግ መንግሥት ከፍተኛ ወጪ ነው ያለበት።
ወታደሩን ከቦታ ቦታ ማንቀሳቀስ፣ ለወታደሩ ምግብ እና ልብስ ማቅረብ ወጪው ቀላል አይደለም። እነዚ ሁሉ ከሀገር ኢኮኖሚ የሚገዙ እና መንግሥትን ለከፍተኛ ወጪ የሚዳርጉ ናቸው።
በሌላ በኩል ህዝቡ እና መንግስት ያስተለፈላቸውን የሰላም ጥሪ ተቀብሎ ከሸኔ እና ከፋኖ ወደ ሰላም የተመለሱ ልጆች በDDR Standard መሰረት ወደ ህዝቡ ለማቀላቀል እራሱ የዛሬ 6 ዓመት የኢትዮጵያ መንግስት የሚያውጀዉን አመታዊ በጀት ያህል ወጪ ይጠይቃል። ይሄ ሁሉ ወጪ የሚሸፈነው በኢትዮጵያ መንግሥት ነው።
የትግራይ ክልል DDR ለማስፈጸም የውጭ ሀይሎች ቃል የገቡት ተግባራዊ ባለማድረጋቸው መንግሥት ወጭውን ሸፍኖ ነው የትግራይ ታጣቂዎች አሰልጥኖ የሚያስፈልጋቸውን እያደረገላቸው ከህዝብ ጋር እንደቀላቀሉ እያደረጉ ያለው።
መንግሥት አሁን ተግባራዊ እያደረገ ያለውን የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች አስገዳጅ ካደረጉ ከIMF እና አበዳሪ ተቋማት ሁኔታ እና የውጪ ሀገሮች ብድር አመላለስ ጋር ተያይዞ መንግስታችን ላይ የሚፈጠሩ ጫና አሁን አላነሳም።
እነዚህ አስገዳጅ ሁኔታዎች በመኖራቸው፣ መንግስት ነዳጅ ላይ ጭማሪ አደረገ በማለት የነዳጅ ጭማሪ ምክንያት አለም የሚያውቀውን እውነት ለህዝብ መግለጽ እያተቻቸለ በህዝብ ላይ የሚያፌዙ አንድ አንድ መሃይሞች፣ በሌላ በኩል እውነታውን መግለጽ እየተቻለ በኬንያ እና በብሩንዲ ነዳጅ ከኢትዮጵያ በላይ ውድ ነው በማለት አሳማኝ ባልሆነ ህዝቡ የነዳጅ ዋጋ ጭማር እንዳይረዳ ሲያደርጉ ተመልክተናል። እነዚህ ልጆች አሁን ሁኔታውን እየቀየረ ላለው Political Propaganda ምንም የማይጠቅሙ ናቸው። ስራችንን፣ ውሳኔያችንን ከማስረዳት ከማሳወቅ ይልቅ ሰው እንዳይረዳን እና Negatively እንዲንረዳ ያደርጋሉ። ስለዚህ እነዚእ ልጆች ያመጣችሁ ሰዎች ወዳመጣችሁበት ቦታ መልሷቸው።
ህዝባችን እውነቱን ከነገርነው በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ይረዳናል፣ ሲረዳንም ኖሯል። ለምን አስፈላጊ እና ምክንያት የለሽ ምላሽ መስጠት አስፈለገ?