በትህነግና በሻዕቢያ መካከል ደግም ለመዘርጋት የታሰበው ግንኙነት ቀድሞውንም በርካታ ስጋቶች ያሉበት ቢሆንም አሁን ላይ ተሳፋ ወደማስቆረጥ መድረሱ ተሰምቷል። የትግራይ ሕዝብ ጦርነትን አስመክቶ የያዘው አቋምና፣ ትህነግ የሚያራምደውን አቋም በተግባር በመረዳት “አምልኮ ትህነግን” የሚያስወግዱበት ጫፍ ላይ መድረሳቸው ለሻዕቢያ ዕቅድ መክሸፍ ዋና ምክንያት መሆኑን ነው ዜናውን የሚከታተሉ የሚናገሩት።
ኢትዮጵያና ኤርትራ ዳግም ከታረቁ በሁዋላ የንግድ፣ የፖለቲካ፣ የጸጥታና የኢኮኖሚ ትብብር ስምምነት ተደርጎ ነበር። ይህ አዲስ ስምምነት ለሁለቱም አገር ዜጎች ተስፋ የስነቀ ቢሆንም በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መነሾ ሻዕቢያ ሁሉንም ጉዳይ መልሶ ዝግ አደረገው። ሻዕቢያ ” ትህነግ ሙሉ በሙሉ ካልጠፋ በትግራይ ጦርነት መቆም የለበትም” በሚለው አቋሙ የተነሳ የፕሪቶሪያውን ስምምነት መቃወሙን ተከትሎ የተጀመረው አዲስ ወዳጅነት እያደር ከሰመ። በመካከሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ኢትዮጵ ዕጣ ፈንታዋ በአባይ ግድብና በቀይ ባህር ላይ መሆኑ አንስተው ኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ እንዳላት ሲያውጁ ሻዕብያ ቤት ስጋት ሆነ።
የሁለቱን አገራት ፖለቲካዊ አካሄድ የሚከታተሉ በተለያዩ ሚዲያዎች እንዳሉት ኢትዮጵያ ሶማሊላንድን የባህር በር ጠይቃ በትስማማ ኤርትራንና የኤርትራን ህዝብ እንዴት ሊጎዳ እንደሚችል አይገባቸውም። ይልቁኑም የኢትዮጵያን ህዝብ ዕልህ ውስጥ የሚከት ጉዳይ እንደሆነ ይገልጻሉ።
ነብሳቸውን ይማረውና አቶ ሴኮ ቱሬ በገሃድ በድል አድራጊነት ስሜት ይፋ እንዳደረጉት ትህነግ በአገር መከላከያ ላይ በወሰደው የክህደት እርምጃ ሳቢያ ወደ ኢትዮጵያ ተንደርድሮ የመጋት ዕድል ያገኘው ሻዕቢያ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳሻው እንዲፋንን አስችሎት እንደነበር በርካቶች ይስማማሉ። መፋነን ብቻ ሳይሆን ከዘግናኝ የቡድንናን የተናጠል ግድያ ጀምሮ፣ የትግራይን ህዝብ ተራ ቁሳቁስ ሳይቀረው ዘርፏል። ቤት እያፈረሰ ማገር፣ ቆርቆሮ፣ በር፣ መስኮት የቤት ቁሳቁስ ከቲቪ እስከ ጭልፋና ድስት አግዟል። ትግራይን እንደ ክልል ሃብቷንና የገነባቸውን ሙልጭ አድርጎ ወስዷል። ማጋዝ ያልቻለውን አውድሟል። በአክሱም ከፈጸመው የጠራራ ጸሃይ ጭፍጨፋ በተጨማሪ ህጻናትና አረጋዊያን ሳይቀሩ እንደ እንስሳ ደፍሯል። በጦርነቱ ወቅት ትህነግ አገር መከላከያ ላይ የፈጸመው ክህደት በፈጠረው ቁጣ ሳቢያ ትግራይ ላይ የተፈጸመው ይህ በደል የኢትዮጵያዊያን ሁሉ ስለመሆኑ አሁን ላይ በስፋት እየተገለጸ ነው። “የልምድ አሳቢ” የሚባሉት የትህነግ ክፋዮች “በሬ ካኮላሸው” እንደሚባል ዳግም ለስልታን ሲሉ ይህንኑ አውሬ ኃይል አቅፈው ለሌላ ጥፋት እየተዘጋጁ ነው።
የትግራይ ተቃዋሚዎች፣ አክቲቪስቶች፣ በሌላ ወገን ንያሉ የትህነግ አመራሮችና የጦር መኮንኖች፣ በገሃድ እንደሚናገሩት ሻዕቢያ እነ ዶክተር ደብረጽዮን ከሚመሩት ቡድን ጋር የተቀናጀ ዘመቻ ለመክፈት እየሰሩ ነው።
ዘመቻውም ጦርነቱም ት5ግራይ መሬት ላይ
ጉዳዩን ከውጭና ከውስጥ የሚከታተሉ እንደሚሉት ከሆነ፣ ሻዕቢያ ብልጽግና የሚመራትን ኢትዮጵያ መፍራት ከጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል። በተለይም ደህነቱንና መከላከያውን ካጠናከሩ በሁውላ ” እናመሰግናለን” በማለት ለድጋፍ የመቱትን ማሰናበታቸው ሻዕቢያ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ንላይ ለመፈንቸት አቅዶት የነበረው ዕቅድ ጋሬጣ በመሆኑ አላስደሰተውም።
በተለይም የኢትዮጵያ ዓየር ኃይል አሁን ላይ ያለበት ደረጃና አቅም ሰላም የነሳው ሻዕቢያ፣ ገና ግንኙነቱ ሳይሻክር ባህር ዳር ላይ ወኪል አስቅመጦ የአማራ ልዩ ኅሃይል መሪዎችን ለዓመጽ ያደራጅ ነበር። የመረጃ ምንጮችን የሚጠቅሱ እንደሚሉት በባህር ዳር ብቸኛ ቅርንጫፍ ቢሮ የነበረው አገር ሻዕቢያ ብቻ ነው። አሁን አማራ ክልል ላይ ያለው ጦርነትን የዚያ ጥንስስ ውጤት ነው።
ሻዕቢያ ይህን የሚያደርገው አሁን ላይ ያለው የኢትዮጵያ መንግስት ” ኢትዮጵያዊነትን” ዳግም እየገነባና ግዙፍ ሰራዊት ማዘጋጀቱ፣ የወደብና ባህር በር አጃንዳውን በሰላም ካልተቻለ በኃይል ለማስፈጸም የሚችል እንደሆነ አስቀድሞ በመገምገሙ ነው። ስለሆነም ኢትዮጵያ በምንም መስፈርት ሰላም መሆን የለባትም በሚል የቆየ ስልቱ አማራ ክልል ላይ እሳት እንዲለኮስ ቢያደርግም ያሰበውን ያህላልሆነለትም።
ባለፈው ሳምንት ኡትዮሪቪው እንደሰማችው ሻዕቢያ የፋኖ ኃይሎች የሚጨበጥ ድል የማያስመዘግቡ ከሆነ ከሚልኩት እየተቀበለ የሚሰጠውን ድጋፍ እንደሚያቆም ቀደም ሲል ባስጠነቀቀው መሰረት አቁሟል። ለዚህም ይመስላል ለፋኖ የተለያዩ አደረጃጀቶች ድጋፍ የሚያደርጉ ኃይሎች አደባባይ ወጥተው ፋኖን ባሞገሱበት አንደበታቸው ” የት አለ ድልህ፣ ሃፍረት ብቻ ወዘተ” በሚሎ በሚዲያቸውና በሚጋበዙ ተባባሪዎቻቸው እያወገኡ ያሉት። አቶ ገረመው ስህሉ ለኢትዮሪቪው እንዳሉት አቶ ኢሳያስ በትህነግ ላይ አቋማቸውን የቀየሩትም በዚሁ መነሻ ነው።
ተቀማጭነታቸው አውሮፓ የሆነው አቶ ገረመእው እንደሚሉት፣ አቶ ኢሳያስ ቀደም ሲል ለትህነግ ውትወታ ጀርባቸውን ሰጥተው እንደነበር ከሻዕቢያ ቅርብ ሰዎች መስማታቸውን አስታውቀው፣ አቶ ኢሳያስ ጀርባ የሰቱትም ” ትህነግ አይታመንም” በሚል እንደሆነም ወሬውን የነገሯቸውን ጠቅሰው ምክንያቱን አስረድተዋል።
አማራ ክልል ላይ ያለው የሰላም ንግግር ጫጫታ ከዚሁ ከሻዕቢያ ፍላጎት መምከን ጋር የተገናኘ እንደሆነ መረጃ እንዳላቸው የሚገልጹት አቶ ገረመው፣ አሁን ላይ አቶ ኢሳያስ ከትህነግ ጋር ለተጀመረው ንግግር ዕውቅና ሊሰጡ መቻላቸውን አመልክተዋል።
አሜሪካ የሚኖረው በኦሮሞ የተቅዋሚዎች መንደር ዘፊ ተሳትፎ የነበረው ተባባሪያችን ባልደረቦቹን ጠቅሶ እንዳለው ከሆነ ሻዕቢያ አንዳችም ጦርነት በክልሉ ውስጥ እንዲከናወን አይፈልግም። በመሆኑም አሁን ላይ ከትህነግ ጋር እየመከሩ ያሉት ዋና ጉዳይና ስምምነት ላይ የተደረሰበት ነጥብ ጦርነቱን ትግራይ6 ላይ ጀመሮ በፍጥነት ወደ አማራ ክልል ኃይሎች በማምራት ለመቀላቀል ነው። በዚሁ ዕቅድ መሰረት ሻዕቢያ ከዛሬ ነገ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰብን በድንገት ሊቆጣጠርና በአፋር ስም ህጋዊ ጥያቄ ሊያቀርብ ይችላል የሚለውን ስጋት ይቀርፋል።
በዱባይ የሚገኘው የሻዕቢያ የስለላ ሰውና የዝግጅት ክፍላችን ተባባሪ እንደሚለው፣ ሻዕቢያ ከትህነግ ጋር አብሮ ጦርነት ቢከፍት የኢትዮጵያ መንግስት በአየር ጥቃት ታጅቦ የሚወስደውን እርምጃ የመቋቋም አቅም እንደሌለው ይናገራል። በሌላ በኩል ደግሞ በትግራይ ውስጥ አሁን ላይ ህዝብ የያዘው አቋም፣ የትግራይ ኃይሎች ግማሽ የሚሆነው ክፍል በሻዕቢያ ላይ ቂም የያዘ በመሆኑ ከአገር መከላከያ ጋር ወግነው ሊቆሙ እንደሚችሉ ግምገማ መኖሩ ሻዕቢያን ስጋት ላይ እንደጣለው ከወዳጆቹ መስማቱን ይገልጻል።
በዶክተር ደብረጽዮን የሚመራው ትህነግ ወደ መንግስት አስተዳደር እንዲመለስ አቋም የያዙት የሰራዊት አመራሮች ባለጥበቁት ሁኔታ ከህዝብ የደረሰባቸው ተቃውሞ ውጤት መጭረሻው ምን ሊሆን እንደሚችል ባይታወቅም፣ ያሰቡትን ማድረግ የሚችሉበት ቁመና ላይ እንዳልሆኑ ከትግራይ የሚወጡ የተለያዩ ዘገባዎች ያስረዳሉ። የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርም ባወጣው የምላሽ መግለጫ የደነገጠ አይምስልም።
ከጦርነቱ በፊትና በጦርነቱ ወቅት “ግፋ በለው” ሲሉ የነበሩ አፍቃሪ ትግራይ ሚዲያዎችም ለመስማት በሚከብድ ደረጃ ሲያሞካሹት የኖሩትን ” ታቦት” የሚሉትን ትህነግ ሲያበሻቅጡና ሲያወግዙ መሰማቱ ነገሩን አቶ ጌታቸው እንዳሉት እያድረግገው ነው።
በመቀለ በተደረገ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ” ታሪካዊ ሞት ሞተዋል” በማለት ንግግር ያሰሙት አቶ ጌታቸውን በመከተለ በተሰላፊዎች ዘንዳ ሲሰማ የነበረው መፈክርና ጩኸት በትግራይ ምድር ይሰማል ተብሎ የሚጠበቅ አልነበረም። ይህን የህዝብ ማዕበል አንደናው ወገን ” የተገዙ” በሚል ሊያቃልለው ቢሞክርም ሰልፉ ግን የዚያ አይነት ሽታ እንደሌለው ዓለም ዓቀፍ ሚዲያዎች ሳይቀሩ መስክረዋል።
በትግራይ ምድር እንዲጀመር የታሰበው ውጊያ በትግራይ ህዝብ ዘንድ ” ጦርነት በቃን” በሚል የዕናቶች ምልጃ ጭምር በሩ የተዘጋ መሆኑ፣ ሌላው አማራጭ በውልቃይት ቢሆንም በዛ መስመር መከላከያና ህዝብ የብረት ኃይል ስለከረቸሙት ሻዕቢያ ዕቅዱ ለጊዜው እንዳልተሳካና እንደከሸፈ ለማወቅ ተችሏል።
የትህነግ ወታደራዊ መኮንኖች ሰሞኑን ከሻዕቢያ ሰዎች ጋር በተደጋጋሚ መምከራቸው የተሰማውም በዚሁ መነሻ እንደሆነ ዜናውን ያቀበሉ አስታውቀዋል።
ይህ ሁሉ ሲሆን ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል ምንም የተባለ ነገር የለም። ይልቁንም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ሰሞኑን ፋብሪካ በመመረቅ፣ ጅምር ፕሮጀክቶችን በመገመገም ስራ ላይ ነበሩ። አሁን ላይ ደግሞ ብልጽግና አጋሮቹን አገራት ጋብዞ የፓርቲውን ስብሰባ እያደረገ ነው።
በሌላ በኩል ማንም ጤነኛ አዕምሮ ያለው ሁሉ እንደሚለው አወዛጋቢ አካባቢዎች ህዝብንና ህግን መሰረት ያደረገ መፍትሄ እስኪበጅላቸው ድረስ የተፈናቀሉ ውገኖች በአስቸኳይ ወደ መኖሪያ ቀያቸው እንዲመለሱ በጥብቅ ሊሰራ ይገባል። ህዝብን ለፖለቲካና ስልጣን ጥማት ማገት፣ ተራው የእኔ ነው ብሎ ግፍ መስራት መዘዝ ያመጣልና ጥንቃቄ እንደሚያሻው፣ ከምንም በላይ ሰብ አዊነት ሊቀድም እንደሚገባ በርካቶች እየገለጹ ነው።