አዲሱ ዓመት ከገባ በሁዋላና የ2024 መገባደጃ ላይ ኤርትራን አስመልክቶ የሚወጡ መረጃዎች ባህሪያቸውን ቀይረዋል። የካሊፎርኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካይ እንደራሴ ብራድ ሸርማን በአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ የስቴት ዲፓርትመንት (የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር) መሥሪያ ቤት ኃላፊን ቃል በተቀበለበት ወቅት ነው። በይፋ አሜሪካ የኤርትራ ተቃዋሚዎችን በገንዘብ መርዳትና ኤርትራ የምታገኘው የምንዛሬ ምንጭ ላይ ማዕቀብ ሊጣል እንደሚገባ ጠይቀው ውይይት ተደርጎበት ነበር። ጥያቄውን በማስረጃ አስደግፈው ያቀረቡት ሸርማን የኮሚቴው ከፍተኛ አባል ናቸው።
በዛው ዓመት የአሜሪካ መንግስት ሙሉ ድጋፍ ያድረገለት የኤርትራ ተቃዋሚዎች ” ኤርትራ ከኢሳያስ በሁዋላ” በሚል አጀንዳ መመከራቸው ይታውሳል። ሰሞኑን ደግሞ የኤርትራ መንግስት ከየመን ሽፍታ ብድን ሃውቲ ጋር በማበር በአሜሪካና በእስራኤል ጥቅም ላይ ያነጣጠረ ተሳትፎ እንዳለው የሚገልጽ ሰፊ ማስረጃ የታጨቀበት ጽሁፍ በእስራኤል በሚታተም ሚዲያ ይፋ መሆኑ አይዘነጋም።
Eritrea Has Become Iran’s Proxy – and a Strategic Threat to Israel and the U.S.
Eritrea has an interest in stabilizing Yemen, and the capability to do so − but its hated regime keeps it allied with Tehran. Houthi actions in the Red Sea, including attacks on ships in Eritrea’s territorial waters, breaching its sovereignty, go without condemnation
አሁን ደግሞ ከአዲስ አበባ የወጣው መረጃ እንደሚያስረዳው “ሰማያዊ ማዕበል” የሚባለው ንቅናቄ በአዲስ አበባ ቁጥራቸው ሁለት ሺህ የሚልቁ ታዳሚዎች የተሳተፉበት ውይይት አካሂደዋል። ስብሰባ ኤርትራን “የአፍሪካ ኮርያ” በሚል ስያሜ እንድትሰየምና፣ “በኤርትራ ሰዓት ቆሟል” በሚል አስደንጋጭ መገለጫ እንድትታወቅ ያደረጉታ ፕሬዚዳንት ኢሳያስን የማስወገድ አጀንዳ የያዘ እንደሆነ ተገልጿል።
የትህነግ አንድ ክፋይ የሆነውንና በዶክተር ደብረጽዮን የሚመራው ኃይል ከሻዕቢያ ጋር መግጠሙ በታሱ የትህነግ ሌላኛ ቡድን በይፋ ኡየተገለጸ ይገኛል። የትግራይ ተቃዋሚ ፓሪ አመራሮችም በይፋ ስም ጠቅሰው እነማን ከሻዕቢያ ጋር እየሰሩ እንደሆነ አመልክተዋል። ሰሞኑኑ ወታደራዊ አመራሮች መንግስት እንዲገለበጥ መወሰናቸውን ተከትሎ በመቀለና በተለያዩ ከተሞች በተደረገ ሰልፍ ከሻዕቢያ ጋር ግንኙነት መፈጠሩን ጠቅሰው አምረረው ተቃውመዋል። የሻዕቢያ ወታደሮች የትግራይ ህዝብን ዘርፈዋል። በቡድንና በተናጠል ገድለዋል። ደፍረዋል።በጅምላ አስረዋል። አውደመዋል። ይህን የቅርብ ጊዜ እውነት የረሱት እነ ደብረጽዮን ከሻዕቢያ ጋር ሆነው፣ በተለይ በጎጃም ያለው የፋኖ ኃይልና ጃል መሮ የሚመራው ቡድን በማቀናጀት ጦርነት ለመክፈት መዘጋጀታቸው መረጃው እየወጣባቸው ነው።
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በበኩላቸው ኤርትራ ኢትዮጵያን የሚተናኮል አንድም ኃይል እየረዳች እንዳልሆነ አመልክተው የኢትዮጵያ መንግስት የኤርትራ ተቃዋሚ ኃይሎችን እያሰለጠነ መሆኑን ጠቅሰው በአንከር ሚዲያ በኩል ኤርትራን ወገነው ሰፊ ትንተና ሰጥተዋ ነበር።
የኤርትራ መንግሥትን ለመለወጥ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ያዘጋጁት የተባለ ውይይት ትናንት ሰኞ ጥር 19 ቀን፣ 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ መደረጉን ከተሳታፊ ድርጅቶች አንዱ ለዶቼ ቬለ ማስታወቁ ሲገለጽ፣ ተሰብሳቢው አካል ውስጥ ወታደራዊ ኃይሎች ስለመኖራቸው የተባለ ነገር የለም” ከተሳታፊዎቹ መካከል አሰብን አካሎ የሚያዘው የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ኮንግረስ ተወካይ ይገኙበታል።
የኤርትራ መንግሥትን ለመለወጥ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ያዘጋጁት የተባለ ውይይት ትናንት ሰኞ ጥር 19 ቀን፣ 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ መደረጉን ከተሳታፊ ድርጅቶች አንዱ ለዶቼ ቬለ ዐሳወቀ ። እስከ «ሁለት ሺህ እና ከዚያም በላይ» የሚሆኑ ኤርትራዊያን በዚህ «ውይይት» መሳተፋቸው ተገልጧል ። የተደረገውን ውይይት በተመለከ፦ «የኢትዮጵያ መንግሥት ዕውቅና ሳይኖረው አልሆነም» ሲሉ የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ኮንግረስ (EANC) ሥራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት አቶ የሱፍ አብደላ ተናግረዋል ። ይህንን ውይይት አዲስ አበባ ላይ ለማድረግ እድሉን እንዴት እንዳግፕኙ የተጠየቁት አቶ የሱፍ አብደላ ይህንን ለማድረግ “እድል ተገኝቷል፣ ያንን እድል ተጠቅመን ውይይቱን አድርገናል” የሚል ምላሽ ከመስጠት በዘለለ ዝርዝር ከመናገር ተቆጥበዋል ።
የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ኮንግረስ (EANC) የተባለውና የኤርትራን መንግሥት ለመለወጥ የሚንቀሳቀስ መሆኑን የሚገልፀው ድርጅት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ የሱፍ አብደላ የፖለቲካ ትግላቸው ማጠንጠኛ የኤርትራ መንግሥት ኤርትራ ውስጥ በሚገኙ አፋሮች ላይ የሚፈጽመው ያሉትን “በደል” እና “ግፍ” ማስቀረት ነው። ለዚህም ሲባል የኤርትራ መንግሥትን ከሌሎች የኤርትራ “ብሔር ብሔረሰቦች ጋር ለመቀየር” ከኤርትራ ውጪ እንደሚንቀሳቀስ እና በትግል ላይ የሚገኝ መሆኑን ገልፀዋል
“ኤርትራ ውስጥ ፌዴራላዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ የራስን መብት ራስህ የምትወስንበት ኹኔታ ለማመቻቸት የሚታገል የፖለቲካ ድርጅት ነው።” ይህንን ለማድረግ የትጥቅ ወይስ ሰላማዊ ትግል ነው የምታደርጉት? የትግል ሜዳችሁስ የት ነው ? የሚለውን ጠይቀናቸዋል።
አማርኛ የሚናገሩት አቶ የሱፍ ድርጅታቸው “ከተለያየ” የዓለም ክፍል ላይ ያለ እና የተደራጀ መሆኑን ገልፀዋል። ይህንን እንቅስቃሴውንም ኤርትራ ውስጥ “ለነፃነት ከሚታገሉ” ካሏቸው ሌሎች አካላት ጋር ተቀናጅቶ የሚከውን መሆኑን በስልክ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል። አዲስ አበባ ውስጥ ምን መሳይ ውይይት ነው ያደረጋችሁት? ለሚለውም ምላሽ ሰጥተዋል።
“ለውጥ ማምጣት እንዳለብን [ኤርትራ ውስጥ] ሕዝባችን ተሰቃየ፣ ሀገራችን ወድሟል። ግን ይህንን መንግሥት [የኤርትራን] በአጭር ጊዜ ለውጥ ለማምጣት እና ለሁሉም የኤርትራ ብሔር ብሔረሰቦች የሚስማማ ያልተማከለ መንግሥት ለመመሥረት የሚል ሴሚናር ነበር።”
ለኤርትራ ሕዝብ የሚታገል እንቅስቃሴ ያሉት “ሰማያዊ ማዕበል” የሚባለው ንቅናቄ ያዘጋጀው በተባለው በዚህ “ሴሚናር” ወይም ውይይት ላይ ከተለያየ የዓለም ክፍል የተውጣጡ ኤርትራዊያን የተሳተፉበት መሆኑን እኒሁ ሰው ገልፀዋል። ውይይቱ አዲስ አበባ ውስጥ ሲደረግ ምን ያህል ሰው ተሳትፏል? የሚለውም ሌላኛው ያቀረብንላቸው ጥያቄ ነው።
“ተሳታፊው ብዙ ነበር። እስከ ሁለት ሺህ እና ከዚያ በላይ የሚሆን ወጣቶች እና እንግዶች ተሳትፈዋ።”
“መቼም የኤርትራ መንግሥት ጓደኛ የለውም” ሲሉ የከሰሱት የኤርትራን መንግሥት የሚቃወመው የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ኮንግረስ ሥራ አሥፈፃሚ አባል አቶ የሱፍ አብደላ፤ የኢሳያስ አፈወርቂን አስተዳደር “ዓለም ላይ ለጎረቤት ሀገሮች ችግር ነው፣ ለራሱ ሕዝብ ችግር የሆነ በአንድ ቡድን የሚመራ መንግሥት ስለሆነ ዛሬ ይህ እድል ተገኝቷል” ብለዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት በዚህ ውይይት ላይ የነበረው እውቅና ምን ድን ነው ? የሚለውንም ለአቶ የሱፍ አቅርበንላቸዋል። “ይህን ያህል ሴሚናር እዚህ ዋና ከተማ ውስጥ ሲደረግ የኢትዮጵያ መንግሥት ፈቃድ ሳይኖረው አይሆንም” ብለዋል።
የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መንግሥታት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ስልጣን መምጣትን ተከትሎ በእጅጉ ተለውጦ ሁለንተናዊ ግንኙነት ተጀምሮ የቆየ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ሁኔታው የተለወጠ ይመስላል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአስመራ በረራም ተቋርጧል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጉዳዩ ላይ ከዚህ በፊት ለቀረበለት ተደጋጋሚ ጥያቄ አሁንም በሁለቱ ሀገራት መካከል ሰላማዊ ግንኙነት መኖረን ደጋግሞ አስታውቋል።
አዲስ አበባ ውስጥ ተደረገ ስለተባለው የኤርትራ መንግሥት ተቃዋሚዎች ውይይት የኢትዮጵያን መንግሥት ሀሳብ ለማካተት ወደ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሠ ቱሉ ብንደውልም ልናገኘቸው አልቻልንም። የኤርትራ መንግሥትም እስካሁን በይፋ የወጣ ያለው ነገር ስለመኖሩ የወጣ መረጃ የለም ሲል ዶችቬሌ ዘገባ ያስረዳል።