አወዛጋቢው የአሜሪካ 47ኛ ፕሬዚዳንት ከአራት ዓመት በሁዋላ ዳግም ነጩ ቤተመንግስትን ተርከበዋል። ዶናልድ ትራምፕ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው ቃለ መሃላ ፍጽመዋል። በዓለ ሲመታቸው ከመካሄዱ አስቀድሞ ለወዳጆቻቸውና ደጋፊዎቻቸው ያስተላለፉት መልዕክት በዓለም ዙሪያ መነጋገሪያ ሆኗል።
ስልጣን እንደተረከቡ አገራቸው አሜሪካ ከዓለም ጤና ድርጅት አባልነት እንድትወጣ የሚያደርገው ሂደት የምትጀምርበትን ትዕዛዝ በፊርማቸው አስተላልፈዋል። ከባለፈው የስልታን ዘመናቸው ጀመሮ ድርጅቱ የኮቪድ ወረርሽኝን በአግባቡ አልተወጣም በማለትና አንቶኒ ፋውቺን በገሃድ አብረው ወንጀል ሰርተዋል በማለት ሲቃወሙ የነበሩት ትራምፕ፣ ባይደን ያሳለፉዋቸውን ት ዕዛዞች ሙሉ በሙሉ አምክነዋል።
አሜሪካ ዳግም መወለዷን ያስታወቁት ዶናልድ ተራምፕ፣ ስራቸውን እንደጀመሩ የዩክሬንና ሩሲያን ጦርነት ቀጥ እንደሚያደርጉ፣ የመካከለኛው ምስራክቅን ትርምስ እንደሚያረግቡ፣ የተፈራውን ሶስተኛውን የዓለም ጦርነት እንደሚያስቀሩ በሙሉ ልብ ሆነው ተናግረዋል። ይሩሲያና ዩክሬን እጅ አዙር ጦርነት የአሜሪካን በጀትና ኢኮኖሚ በእጅጉ የበላ በመሆኑ የፕሬቪዳንቱ ንግግር ቭላድሚር ፑቲን ቀደም ሲል ከሳቸው ጋር ለመገናኘት ቀጠሮ መያዙን ካስታወቁት ጋር ተገጣጥሟል። ጦርነቱ ኢኮኖሚያቸውንና ሰላማቸውን ያናጋባቸው የአውሮፓ አገራት ዜጎች ይህን የትራምፕን ንግግር በተስፋ እየጠበቁ እንደሆነ የሚገልጹ አስተያየቶችን በማህበራዊ ሚዲያዎች እያሰራጩ ነው። በጥርጣሬ ያዩም አሉ።
ሞገደኛው ትራምፕ ስራቸውን በይፋ ከመጀመራቸው ቀደም ብሎ ለህዝብ ያወጇቸው ጉዳዮች ያለምንም ማቅማማት በዓለ ሲመታቸው እንድተከናወነ ትዕዛዝ የሚሰጡበት ነው። ከምንም በላይ የዓለም የመጪው ትውልድ ፈተና የሆነውን የጾታ ጉዳይ “በእኔ የስልታን ዘመን በአሜሪካ ላይ ሁለት አይነት ፆታ ብቻ ይኖራል እሱም ወንድ እና ሴት ብቻ ነው” ሲሉ የሁለት ጾታ ጉዳይ ያከተመለት መሆኑን ይፋ አድርገዋል።
ሰውየው በዚህ አላበቁም። አከል አድርገው “ ልጆቻችን ልክ እንደ ማሽን ጾታቸውን የሚመርጡበት ጊዜ አብቅቷል” ሲሉ አውጀዋል። በስመ ዕድገት ከፍተኛ በጀት መድበው ለሶስትና ሁለት ዓመት ህጻናት በመዋያቸው አጽደ ግቢ ውስጥ ወይም በመዋለ ሕጻናት ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሁለት ጾታ ትምህርት ለሚሰጡ፣ ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው ህጻናቶች ፊት እየተሳሳሙና ነወር ሲፈጽሙ እንዲታይ ህግ ላወጡ የአውሮፓ ጥቃቅን መንግስታት የትራምፕ ውሳኔ መሪር ሆኖባቸዋል።
ሁለት ጾታ መከለከላቸው ብቻ ሳይሆን ፆታቸውን የቀየሩ ወንድም ሆነ ሴቶች ለፆታቸው እውቅና እንደማይሰጥና ላደረጉትም ተግባር በስራቸው ጨምሮ በተለያዩ ሁኔታዎች ላይ እገዳ እንደሚጣልባቸው ይፋ ማድረርጋቸው አድሮ የሚያስነሳው ቅሬታ ለጊዜው ባይተነበይም ሰውየው ማምረራቸውን የሚያመላክት ነው። እንደ እሳቸው አባባል እንዲህ ያለው ውሳኔያቸው አሜሪካን ከሞራል ውድቀት የሚታደግ ነው።
ቂመኛና ያሰቡትን ለማድረግ ዋጋ እንደሚከፍሉ የሚነገርላቸው ትራምፕ፣ “የአሜሪካ ወርቃማ ጊዜ አሁን ይጀምራል” ሲሉ የባይደን አስተዳደር አሜሪካን ቁልቁል እንደነዳት አሳይተዋል። በዚሁ ንግግራቸው “የቁልቁል ጉዞ አክትሟል” በማለት ደጋፊዎቻቸውን አስደምመዋል።
አሜሪካን ዳግም ገናና ለማድረግ ወገባቸውን ማጥበቃቸውን ሲያስታውቁ ” አሜሪካን አስቀድማለሁ፣ ከአሁን በኋላ የአሜሪካ ማሽቆልቆል ያበቃል፣ በፈጣሪ ፈቃድ የተረፍሁት አሜሪካን ዳግም ታላቅ ለማድረግ ነው፣ ዛሬ (ጃንዋሪ 20/2025) አሜሪካ ነጻ የወጣችበት ቀን ነው” በማለት ቀኑን በታሪክ እንዲታሰብ አቅጣጫ አመላክተዋል።
ሁሉንም እንደሚያፈራርጡት በተናገሩበት ንግግራቸው የፕሬዚዳንት ጆሴፍ ኬኔዲና ወንድማቸው፣ እንዲሁም የዶክተር ማርቲን ሉተር ኪንግ ግድያ በቀናት ውስጥ ለህዝብ ይፋ እንደሚሆን ሲናገሩ አድምጮቻቸው ጩኸታቸው ወደር አልነበረውም። ትራምፕ በድንገት የተገደሉትን ታላላቅ ሰዎች አንስተው ማን እንደገደላቸና እንዴት እንደተገደሉ አደባባይ እንደሚያሰጡት ሲያስታውቁ በርካቶች ተገርመዋል። በጉጉት የሚጠበቅም ጉዳይ ሆኗል።
የሜክሲኮ የእጽ አዘዋዋሪዎችን በይፋ የውጭ ሽብርተኛ ድርጅት ብለው ፍርጀዋቸዋል። የፓናማ ካናልን እንደሚያስመልሱ ዝተዋል። ድንበሯ የተከበረ፣ ብሄራዊ ጥቅሟ የተጠበቀ፣ ለሰላም እየሰራች ጠንካራና ግዙፍ የመከላከያ ኃይል የሚኖራት አሜሪካ ዳግም የምትከበርና የምትደነቅ አገር እንደምትሆን ቃል ገብተዋል።
ጦርነትን የሚያሸንፍ ብቻ ሳይሆን ጦርነት ውስጥ የማይገባ ትልቅ ወታደራዊ ኃይል እንደሚገነቡ ሲያስታውቁ፣ “ገልፍ ኦፍ ሜክሲኮን ወደ ገልፍ ኦፍ አሜሪካ እለውጠዋለሁ” በሚል ማህተም አስረግጠዋል።
እንደ እሳቸው ገለጻና ዕምነት “ሕይወቴ የተረፈው አሜሪካን ታላቅ እንዳደርግ ነው ” በማለት ግድያ ተሞክሮባቸው መትረፋቸውን አስታውሰዋል። ፈጣሪ ያተረፋቸው አሜሪካንን የተከበረች፣ ገናና፣ ወደ ቀድሞ ኃያልነቷ እንዲመልሱ እንደሆነ በልበ ሙሉነት ተናግረዋል።
“ህይወቴ የተረፈው የአሜሪካን ታላቅነት እንድጠብቅ ነው። አሁን ታላቋን አሜሪካ ወደ ሰገነቷ አመልሳለሁ፣ ያለምንም ዘር እና ቀለም ልዩነት አሜሪካውያንን ሁሉ በነፃነት አገለግላለሁ፣ ዛሬ የነፃነት ቀን ብላችሁ ጥሩት” ሲሉ በዘረኝነት ለሚከሷቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።
የ45ተኛው እና 47ተኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወጣቱን የ39 አመት ጄዲ ቫንስን ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ በዓለ ሲመት ተከናውኗል።
ትራምፕ ፍትህ፣ ህግና እና ስርዓት በአሜሪካ በአግባቡ እንዲከበር እንደሚሰሩ ሲያስታውቁ፣ እንዳሉት ወረቀት አልባ ስደተኞች ላይ የማያወላዳ እርምጃ እንደሚወሰድ ባማስታወቅ ነው።
“በደቡብባዊ የአሜሪካ ግዛት የአስቸኳይ ጊዜ አውጃለሁ” ያሉት ትራምፕ፣በዚህ አዋጅ ሳቢያ የስም ቅየራ እና ወታደራዊ ዘመቻ እንደሚካተትበት አስታውቀዋል።
የመሳሪያ አያያዝ ስርዓታችን በአግባቡ እንዲሆን እሰራለሁ” ሲሉ ህግ እና ስርአት አሁን በአግባቡ ወደ እያንዳንዱ መኖሪያ በክብር መምጣቱን አመልክተዋል።
ስለ ህግ መከበርና የአሜሪካንን ጥቅም ስለማስቀደም ደጋግመው ሲናገሩ ጣታቸውን ስደተኞች ላይ የሚቀስሩት ትራምፕ፣ ሚሊየን ህገወጦች ወደ መጡበት እንደሚመለሱ በማስታወቅ ነው። ተግባሩን “ወረራ ነው” ሲሉ አውግዘው “ሜክስኮ ላይ የነበረንን ፖሊሲ በድጋሜ እመልሳለሁ” ሲሉ የአፈጻጸሙን ፍንጭ ተናግረዋል። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወረቀት አልባ ስደተኞችን እንደሚመልሱ ሲያስታውቁ በታላላቅ እርሻዎች ማን ድንች እንደሚለቅምላቸው አማራች አላነሱም። ስወየው ይህን ማለት ከጀመሩበት ቀን አንስቶ ቢያንስ በታላላቅ እርሻዎች ላይ ችግር እንደሚፈጠር የሚናገሩ ብዙ ናቸው።
“የእኔ መንግስት የአሜሪካን የመፈፀም እና የማድረግ አቅም በመጨመር ጠንካራ መንግስት ይገነባል” ያሉት ትራምፕ፣ አሜሪካ በኢነርጂ፣ በምርታማነት፣ በተሽከርካሪዎች ፈጠራ ላይ አቅም ያለው አካሔድ እንደምትከተል ገልጸዋል። መንገድን ጨምሮ ትልልቅ መሰረተ ልማቶች እንደሚገነቡ በማስታወቅ፣ “ የአሜሪካ የብልፅግና የእድገት እና የመነቃቃት ጊዜ አሁን ነው። እኔ ለመረጣችሁኝም ላልመረጣችሁኝም ላገለግል የመጣሁ ነኝ” ብለዋል።
“አሜሪካ ለጠላቶቿ አትተኛም ትልቁን ወታደራዊ አቅምም ይኖረናል። የአሜሪካ የ4 አመት የሽንፈት ጊዜ እቀለብሰዋለሁ ብለዋል። የእኔ ፖሊሲ ሰላም ነው ። መካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት መቋጫውን ያገኛል። በሞኝነት ሠርተን ያስረከብነውን የፓናማ ቦይ እመልሰዋለሁ። የአሜርካ ወርቃማ ጊዜ ዛሬ ጀምሯል” ሲሉ ቀድሞ የተናገሩትን በበዓለ ሲመታቸውም ደግመውታል።
በተመሳሳይ ከሹመታቸው አዋጅ በሁዋላ ትራምፕ ቲክቶክ ለሚቀጥሉት 75 ቀናት ከእገዳ ነፃ የሚሆንበትን ትዕዛዝ አስተላልፈዋል። ቲክቶክ የትራምፕን ውሳኔ አመስግኖ ተቀብሏል። መተግበሪያው ለሰዓታት አሜሪካ ውስጥ መሥራት አቁሞ የነበረ ሲሆን ነገር ግን አሁን አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። ትራምፕ በውሳኔያቸው እንዳሉት የእፎይታ ጊዜ የቲክቶክ እናት ኩባንያ የአሜሪካ አጋር እንዲፈልግ ጊዜ የሚሰጥ ነው። የመመሪያው ዝርዝር ይፋ እንዳልሆነ ቢቢሲ ዘግቧል።
ከዚህ ቀደም ቲክቶክ መዘጋት አለበት የሚለውን ሐሳብ የደገፉት ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት በርካታ ሰዎች ቲክቶክን ተጠቅመው እንዳይዋቸው በመናገር አቋማቸውን ቀይረዋል።
የሜክሲኮ ባሕረ ሰላጤን የአሜሪካ ባሕረ ሰላጤ ብሎ መሰየም፣ የዋጋ ግሽበትን መከላከል፣ የባይደን ፖሊሲዎችን መሻር፣ ከፓሪስ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት መውጣት፣ የኢነርጂ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣ በካፒቶል አመፅ ለተሳተፉ ሰዎች ይቅርታ ማድረግ ይገኙበታል።
ትራምፕ በፌደራ ተቋማት ላይ ዕገዳና ቁጥጥር ጥለዋል። የመንግስትን ወጪ ብክነት ለመገደብና ለመቆጠር
ዲፓርትመንት ኦፍ ገቨርንመንት ኤፊሸንሲ አሊያም ዶጅ የተባለ መሥሪያ ቤት እንዲቋቋምአዘዋል። ይህም ተቋም በቢሊየነሩ ኢላን መስክ እንዲመራ አድርገዋል። የስፔስኤክስ እና ቴስላ ባለቤት መስክ 20 ገደማ ሠራተኞችን ቀጥሮ የሚያስተዳድርበት የመንግስት ቢሮ ይዘጋጅለታል።
ከዚሁ ጋር ተያያዞ የሳቸው መንግስት ሙሉ በሙሉ ሁሉንም ስልጣን እስኪቆጣጠር ድረስ ከጦር ሰራዊቱና አንዳንድ መስሪያ ቤቶች በስተቀር የፌዴራል ቅጥር እንዲቋረጥ አዘዋል። የፌዴራል መሥሪያ ቤት ሠራተኞች ከዚህ በኋላ ከቤት መሥራት አይችሉም የሚል ትዕዛዝ አስተላልፈዋል። ሰራተኞች ቢሮ ገብተው መስራት ግዴታ ይሆንባቸዋል።
ኢትዮሪቬውን ይረዱ ዘንድ ልናስታውስዎ እንወዳለን። እዚህ ላይ ይጫኑ DONATE US as partner from USD 1
በቲሌግራም ይከተሉን ቴሌግራም – https://t.me/+f_kxmaPjD-9jYTdk