ወርቅ ለማውጣት ሲባል ያልተፈቀዱ ኬሚካሎችን የሚጠቀሙ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ቢሮው አሳሰበ!
በትግራይ ክልል ወርቅ ለማውጣት ሲባል ያልተፈቀዱና ማህበረሰቡ ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ ኬሚካሎችን የሚጠቀሙ አካላት ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ እንደሚገባ የክልሉ የመሬትና ማዕድን ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ፍስሃ ግርማይ ለኢፕድ እንደገለጹት፤በክልሉ የነበረው ጦርነት የማዕድን ዘርፉ ላይ ህገወጥ ተግባር እንዲስፋፋ አድርጓል።
በዚህም ህገወጥ ማዕድን አውጪዎች ወርቅ ለማውጣት ያልተፈቀዱና ማህበረሰቡ ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ ኬሚካሎች ሲጠቀሙ ቆይተዋል።ይህም በክልሉ ወንዝ፣ የእንስሳት ሃብት እና በማህበረሰቡ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱንና እያደረሰ መሆኑን ተናግረው፤ በክልሉ በህገወጥ መንገድ የማዕድን ንግድ ላይ የሚሳተፉ እና ማህበረሰቡ ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ኬሚካሎችን የሚጠቀሙ የማዕድን አውጪዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።
ይህንን ለመፍታት የቁጥጥር መመሪያ ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል ያሉት አቶ ፍስሃ፤ ከዚያም ተጠያቂነትን የማስፈን እና ህገወጥ ማዕድን አውጪዎችን ለህግ የማቅረብ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
በቀጣይ ደግሞ ለማዕድን አውጪዎች የሚሰጠው ፈቃድ ይቆማል ብለዋል።በማዕድን ዘርፉ ህጋዊ ያልሆኑትን ወደ ህጋዊ ሥርዓት የማስገባት ሥራ እየተሰራ ሲሆን በዚህም በ30 ማህበራት የታቀፉ ወጣቶች በህጋዊ መንገድ እንዲንቀሳቀሱ ተደርጓል።
ለነዚህም ህጋዊ ፍቃድ፣ የመሥሪያ ቦታና ሌሎች ድጋፍ ተደርጎላቸው ወደ ሥራ ገብተዋል ብለዋል። ይህ እንቅስቃሴ በክልሉ የማዕድን ሀብት ላይ ሲታይ የነበረውን ህገወጥ ተግባር እንዲቀንስ እና ወደ ብሔራዊ ባንክ የሚገባው የወርቅ ክምችት እንዲጨምር አድርጓል ብለዋል።
Via EPA
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring