ወታደራዊ ብቃቷን በሚያሳይ እርምጃዋ ታይዋን በ2000 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ኢላማዎችን ለመምታት የሚያስችል ዘመናዊ (ኪንግቲያን) ሃይፐርሶኒክ ሚሳኤል ይፋ አድርጋለች።
በሀገሪቱ በቹንግ ሻን ብሔራዊ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት [NCSIST] እንደተመረተ የተገለፀው ዘመናዊ የጦር መሳሪያው በታይዋን የመከላከያ ብቃት ላይ ትልቅ አቅም የሚፈጥርና፣ ከቻይና በኩል እየጨመረ የመጣውን ወታደራዊ ግፊት መቋቋም እንዲችል ጉልበት እንደሚሆነት ተነግሯል።
የኪንግቲያን ሚሳኤል ታይዋን በፍጥነት እየጨመረ በመጣው የዘመናዊ የጦር መሳሪያ በማምራት ሂደት ውስጥ ተወዳዳሪ ሆና ለመቀጠል ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ተብሏል። እ.ኤ.አ. በ2024 መገባደጃ ላይ በስፋት መመረት የጀመረው ሚሳኤሉ አሁን ላይ ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል።
የመጀመሪያዎቹ ምርቶች ቀድሞውኑ ወደ ታይዋን አየር ኃይል ሚሳይል ክፍሎች የገቡ ሲሆን፣ ይህ ማለት ኪንግቲያን ሚሳኤል ምሳሌያዊ ብቻ ሳይሆን ለጦርነት ዝግጁ የሆነ መሳሪያ መሆኑን እንደሚያሳይ ተገልጿል።
በተለይ ኪንግቲያንን አስፈሪ የሚያደርገው የሃይፐርሶኒክ ችሎታው ከማች 6 በላይ ፍጥነት ያለው መሆኑ ነው። ሚሳኤሉ በዚህ ፍጥነት በደቂቃዎች ውስጥ ብዙ ርቀት መሸፈን መቻሉ የማንኛውንም ባላንጣ ኢላማ በአጭር ጊዜ በመምታት በጦርነት ወቅት ጨዋታ ቀያሪ ሚና እንደሚኖረው ይጠበቃል።
ሚሳኤሉ የሚንቀሳቀሰው በራምጄት ሞተር ሲሆን ይህ ቴክኖሎጂ ውስብስብ የሆነ የተርባይን ሲስተም ሳያስፈልገው ረጅም ርቀት በከፍተኛ ፍጥነት እንዲቆይ ያስችለዋል። ይህ የሞተር ንድፍ ውጤታማ ብቻ ሳይሆን ሃይፐርሶኒክ በረራን ለማስቀጠል ወሳኝ ነው ተብሏል።
የሚሳኤሉ አካል የተገነባው በከፍተኛ ፍጥነት ምክንያት የሚፈጠረውን ከፍተኛ የሙቀት መጠን ለመቋቋም የሚያስችል የሴራሚክ ውህዶችን ጨምሮ የላቀ የተቀናጁ ቁሳቁሶችን በመጠቀም ነው።
ሚሳኤሉ የተገጠሙለት መሳሪያዎች የተራቀቁ የአየር መከላከያ ስርዓቶችን ለማምለጥ በጣም አስፈላጊ ናቸው፤ ይህም ኪንግቲያን በተጨናነቁ አካባቢዎች ውስጥ ከጠላት ኢላማ በመሰወር አስተማማኝ እንዲሆን ያደርገዋል።
ተለምዷዊ ሚሳኤል ስርዓቶች፣ ብዙ ጊዜ በቋሚ ማስጀመሪያ ጣቢያዎች የተገደቡ ናቸው የታይዋን አዲሱ ኪንግቲያን ሚሳኤል ግን ከተለያየ ቦታ በመነሳት ጥቃት ማድረስ ይችላል።
ይህ ተንቀሳቃሽነቱ ሚሳኤሉቱን በቅድመ-ምት ላይ ያለውን መትረፍ ከመጨመር በተጨማሪ በጦርነት ወቅት ተለዋዋጭ ስልታዊ የመልሶ መደራጀት ሁኔታዎች ሲኖሩ በፍጥነት መንቀሳቀስ እንዲችል ያግዛል።
የሞባይል ማስጀመሪያ ስርዓቶችን በመጠቀም ታይዋን የኪንግቲያን ሚሳኤል በመከላከያ ስልቷ ውስጥ ማስገባቷ ተለዋዋጭ እና ሊተነበይ የማይችል የጠላት አደጋ ስያጋጥም ፋጠን ምላሽ እንድትሰጥ ከማስቻሉ በተጨማሪ ከተለያዩ ቦታዎች የሚቀጡ የጠላት ኢላማ ጥረቶችን በማክሸፍ ውጤታማነት ሥራ እንደሚሠራ ይጠበቃል።
ታይዋን ወደ ሃይፐርሶኒክ ቴክኖሎጂ መግባት እንድትችል ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ያደረገችው ስልታዊ ስምምነት ጉልህ እገዛ እንደነበረው ተነግሯል፣ በዚህም ወሳኝ የሚሳኤሉን አካላት ጨምሮ የቴክኖሎጂ እውቀትን እንድታገኝ አስችሏታል ተብሏል።
የአሜሪካ የመከላከያ ተቋም (ፔንታጎን) የሚሳኤሉ ስፋት እና ትክክለኛነት ታይዋን ዋና ዋና የኢንዱስትሪ ማዕከላትን እና የቤጂንግ ወታደራዊ ጭነቶችን ጨምሮ በቻይና ውስጥ ጥልቅ ስትራቴጂካዊ ቦታዎች ላይ እንድታነጣጥር አስችሏታል ብሏል።
ይህም የሀገሪቱን የመከላከያ አቅም ማሳደጉ እንደለ ሆኖ፣ በታይዋን የባህር ወሽመጥ ላይ እየተካሄደ ያለውን ውጥረት ያባብሰዋል ተብሏል።
የኪንግቲያን ሚሳይል በቴክኖሎጂ አቅሙ በታይዋን የመከላከያ አስተምህሮ ውስጥ ስልታዊ ለውጥን ያመጣ የተባለለት ስሆን፤ በሃይፐርሶኒክ ችሎታዎች ላይ ኢንቬስት በማድረግ ታይዋን የመከላከያ አቅሟን ከማሳደጓ ባሸገር አስፈላጊ ሆኖ ስገኝ ኢላማቸውን የጠበቁ ጥቃቶችን የመፈፀም ችሎታዋን እያሳየች ትገኛለች ተብሎለታል።
ይህ እድገት በታይዋን ወታደራዊ ስትራቴጂ ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ፣ ጥቃትን በመከላከል እና ማንኛውም ጠላት ከታይዋን ጋር ግጭት ውስጥ ከመግባቱ በፊት ሁለት ጊዜ ማሰብ እንድችል መልዕክት የሚያስተላልፍ እንደምሆን ተገልጿል።
ታይዋን የውትድርና አቅሟን እያጠናከረች ባለችበት ወቅት፣ የኪንግቲያን ሃይፐርሶኒክ ሚሳኤል ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ እና በቀጠናው መረጋጋትን ለማስጠበቅ ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ተብሏል።
ሚሳኤሉ አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት ላይ የዋለ ሲሆን፣ መሳሪያው ታይዋን በምስራቅ እስያ ያለውን የሃይል ሚዛን ለማስጠበቅ እንደሚያግዛት ተነግሯል።
ክብረአብ በላቸው ጥር 1/2017(ጋዜጣ+)
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring