የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ስር በመተዳደር ላይ ይገኛል፡፡ ዞኑ በክልሉ አንፃራዊ ሰላም እና መረጋጋት ከሚታይባቸው አከባቢዎች በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱት አንዱ ነው፡፡ አከባቢው 1983 ዓ/ም በህውኃት መራሹ ኢህአዴግ መንግስት ትግራይ ክልል ተብሎ በሚጠራዉ ክልል፤ ህዳር 29/1987 የፀደቀው የኢፌዴሪ ህገ መንግስት ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት፣ ያለ ህዝቡ ፍላጎት እና ፈቃድ ህገ-ወጥ በሆነ መልኩ መካለሉ የሚታወቅ ነው፡፡ ከለውጡ በኃላ ጥቅምት 24/2013 ጀምሮ በተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ ማህበረሰቡ ከትህነግ-ወያኔ ነጻ በመሆን፤ ተጠሪነቱ ለአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሆነ ከወልቃይት ጠገዴ ማንነት እና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ መሰረት ያደረገ የዞን አስተዳደር በማደራጀት ራሱን በራሱ እያሰተዳደረ ይገኛል፡፡
ትህነግ-ህውኃት በፕሪቶርያው የዘላቂ ሰላም እና ተኩስ ማቆም ስምምነት በኋላ በ30 ቀናት ውስጥ ትጥቅ በመፍታት አከባቢው ወደ ዘላቂ ሰላም፣ መልሶ ግንባታ/Rehabilitation and restoration/፣ ሀገራዊ መግባባት እና አገር ግንባታ እንዲመለስ ግዴታውን መወጣት ሲገባው፤ ላለፉት 40 ዓመታት በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ላይ አማራዊ ማንነቱን ምክንያት በማድረግ እና ለታላቋ ሀገረ ትግራይ ምስረታ ምቹ ይሆን ዘንድ የፈፀመው የዘር ማፅዳት ወንጀል በካደ መልኩ ብቻ ሳይሆን በቀጣይ ለመፈፀም ያቀዱትን ዘር ፍጅት እቅድ በሚያሳብቅ መልኩ፤ በሀገሪቱ ህግ እና ስርዓት የሌለ በስመ ተፈናቃይ የክልል ሉዓላዊነት እና ግዛት ማስመለስ በሚል የውንብድና እና ማጭበርበር ባህርይ በመጠቀም በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ የዳግም ወረራ እና ጦርነት ስጋት ፈጥሮ ይገኛል፡፡
የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ህግ እና ስርዓት ተከትሎ የወልቃይት ጠገዴ ማንነት እና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ በማቋቋም ህጋዊ እና ፍትኃዊ የሆነ የአማራ ማንነት ጥያቄ ለፌደሬሽን ምክር ቤት እና በወቅቱ ለነበረው የትግራይ ክልል መንግስት ታህሳስ 7/2008 ዓ/ም ለትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳደር፣ ለትግራይ ክልል ህውኃት ፅ/ቤት፣ ለትግራይ ክልል ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ፅ/ቤት በፅሁፍ እና በአካል በመቅረብ ጥያቄውን አቅርበዋል፡፡ ሆኖም ግን ይህ ተከትሎ የሰጠው ምላሽ አፈና እና ግድያ ነበር፡፡ ሐምሌ 05/2008 ዓ/ም የወልቃይት ጠገዴ ወሰን እና አስመላሽ ኮሚቴ በጎንደር ከተማ አመራሩ ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት እና በሽብር ወንጀል በመክሰስ እስከ ለውጡ ጊዜ ድረስ የፖለቲካ እስረኛ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡
በለውጡ መንግስት በመላ ሀገሪቱ የነበሩ የማንነት እና ወሰን ጥያቄዎችን ምላሽ ለመስጠት የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮምሽን የተቋቋመ ሲሆን ትህነግ-ወያኔ በወልቃይት ጠገዴ አማራ ማህበረሰብ ያደረሰውን ዘር ማፅዳት ወንጀል ተጠያቂ ላለመሆን ይህን በሀገሪቱ ፓርላማ በአዋጅ የተቋቋመውን ኮሚሽን በ100% ድምፅ ውድቅ በማድረግ ወደ ክልሉ ገብቶ ምንም ዓይነት ስራ እንዳይሰራ፤ ለህግ እና ስርዓት ተገዢ አለመሆኑ አስመስክሮ አልፏል፡፡
ትህነግ-ህውኃት ለውጡን ባለመቀበል ክልላዊ ዲፋክቶ ስቴት [Defacto state] በሚመስል ሁኔታ ጥቅምት 24/2013 ዓ/ም ማዕከላዊ መንግስቱን በኃይል ለመቆጣጠር እና ለ30 ዓመታት የነበረው አንባገነናዊ የኢህአዴግ ስርዓት ለመመለስ ጦር መስበቁ የሚታወስ ነው፡፡ ይህን ተከትሎ በተለይ በወልቃይት ጠገዴ አማራ ማህበረሰብ ማንነት ተኮር የማይካድራ ጅምላ ጭፍጨፋ እና የሁመራ ንፁኃን አሰቃቂ ግድያ ከመፈፀም ባሻገር፤ ሀገሪቱ ለ2 ዓመታት የዘለቀ የእርስበርስ ጦርነት በመክተት ከባድ አገራዊ ኪሳራ አስከትሏል፡፡ ጦርነቱን ተከትሎ የፕሪቶርያ ስምምነት መፈራረም ቢቻልም፤ ትህነግ-ህውኃት የስምምነቱ ዋና ግብ እና ትኩረት የነበረው DDR በታቀደው መልኩ ለሁለት ዓመታት ሳይፈፀም እንዲቆይ ከማድረግ አልፎ በቅርቡ የተጀመረው የትግራይ ቀድሞ ተዋጊዎች ትጥቅ ማስፈታት ሂደት እንዳይቀጥል <
ይህ የአመፅ እና ግርግር ተግባር መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እና ሰላም ወዳድ የሆነው የዓለም ማህበረሰብ ሊቃወመው ይገባል፡፡ እንዲሁም የኤፌዴሪ መንግስት የወልቃይት ጠገዴ እና ጠለምት አማራ ማህበረሰብ የዘመናት የአማራ ማንነት ጥያቄ ምላሽ/እዉቅና በመስጠት እና በጀት በመፍቀድ ሀገሪቱ የጀመረችውን የሰላም ግንባታ የተሟላ እንዲሆን ጥሪያችን እያቀረብን በስመ ተፈናቃይ የሚሰበከውን <
የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አማራ ምሁራን ማህበር
ጥር/2017 ዓ/ም
ሁመራ