” ጉዳዩ ዓለም አቀፍ የወንጀል ገጽታ ያለው ነው ” – የውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር
” በህገወጥ ዓለምአቀፍ ደላሎች ተታለው ወደ ማይናማር ፣ ታይላንድ፣ ቻይና ድንበር አዋሳኝ አካባቢዎች ወደሚገኙ ህገወጥ ካምፓች ተወስደው የሚገኙ ዜጎችን ለማስመለስ በመንግስት የተጀመሩ ጥረቶች ቀጥለዋል። ጉዳዩ ዓለም አቀፍ የወንጀል ገጽታ ያለው ነው” የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው
እስካሁን በምናደርገው እንቅስቃሴ የ19 ሀገራት ዜጎች ተመሳሳይ በህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ተታለውና ታግተው ወደ ማይናማር በመግባት ለከፋ ችግር የተዳረጉ መሆኑን ለመረዳት ችለናል።
ኢትዮጵያውያንን በተመለከተ በማይናማር 380 የሚል ቁጥር ተጠቅሷል ይሄ የቁጥር የተወሰደው እዚህ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተለያዩ ዜጎች ልጆቻቸው ታግተው እዚህ መጥተው ካመለከቱት ነው።
በዚህ መሰረት ክትትል ለማድረግ እንዲረዳን ቶኪዮ ለሚገኘው ኤምባሲያችን የተላለፈው ቁጥር ይህ ነው። ትክክለኛው የታጋቾች ቁጥር አይታወቅም።
ቶኪዮ የሚገኘው ኤምባሲያችን ከማይናማር ኤምባሲ ጋር ዜጎቻችንን ለማዳን በትብብር እየሰራ ነው። የ380 ዜጎች ስም ዝርዝር እና ፓስፖርት ኮፒ ቶኪዮ ለሚገኘው የማይናማር ኤምባሲ እንዲደርስ ተደርጓል።
የማይናማር መንግሥት ታጋቾችን ለመልቀቅ ጠረት በማድረግ ላይ ሲሆን ከአጋቾች አምልጠው ለመንግሥት እጅ የሚሰጡ ዜጎች ምህረት በማድረግ በነጻ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ትብብር በማድረግ ላይ ይገኛል።
ፈታኝ የሆነው ዋናው ጉዳይ የታገቱት ዜጎች የሚገኙት በማይናማር እና ታይላንድ መካከል በሚገኙ ከማይናማር መንግሥት ቁጥጥር ውጭ በሆኑ ስፍራዎች መሆኑ ነው። ይህ ስራውን አክብዶታል።
ሌላው ፤ በዚህ ኢሰብዓዊ ወንጀል ኢትዮጵያውያን እና የውጭ ሀገራት ሰው አዘዋዋሪዎች ተቀራርበው እየሰሩ መሆኑ ነው።
እስካሁን መንግሥት ከዓለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅቶች ጋር ጭምር ባደረገው ጥረት በ6 ወር ውስጥ 34 ዜጎች ከአጋቾች ነጻ ወጥተው ወደ ታይላንድ እና ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ ተደርጓል።
ከአጋቾች አምልጠው ህጋዊ ሰነድ ስለሌላቸው በእስር ቤቶች ታስረው የነበሩ 7 ዜጎቻችንም በምህረት እንዲለቀቁ ማድረግ ተችሏል።
ዜጎችን የመታደጉ ስራ ብዙ ጥረትን የሚጠይቅ በመሆኑ ቶኪዮ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ሚስዮን በተጨማሪ በኒዉዴልሂ የሚገኘው ኤምባሲም ተልዕኮ ተሰጥቶት መንቀሳቀስ ጀምሯል ” ብለዋል።
NB. አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ወጣቶች ደህንነቱ ወዳልተጠበቀ ስፍራ እየሄዱ ያሉት ከስራ ቅጥር ጋር ተያያዥ በሆኑ የማተለያ ስልቶች በመሆኑ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስበዋል። የችግሩን ምንነት እና አስከፊነት ህብረተሰቡ እንዲያውቅ የማድረጉን ስራ ሁሉም ባለድርሻ አካላት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።
tikvah
TIPS
Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security