በአዲስ የመመዘኛ መስፈርት ዳግም ከተመዘገቡ 273 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ አንዳቸውም መስፈርቱን እንዳላሟሉ የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ገለፀ፡፡
ባለስልጣኑ አዲስ ባወጣው መመዘኛ 273 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሲመዘገቡ 84ቱ ባለመቅርባቸው መሰረዛቸው ይታወሳል፡፡
በባለስልጣኑ የፈቃድ አሰጣጥና የጥራት ኦዲት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ውብእሸት ታደለ÷ ተቋማቱ መስፈርቱን እንዲያሟሉ ተጨማሪ የ45 ቀናት የጊዜ ገደብ መቀመጡን ተናግረዋል።
በተጨማሪ የጊዜ ገደብ ተማሪዎች መመዘኛውን አሟልተው ወደሚገኙ ተቋማት ተዛውረው እንዲማሩ ማድረግን ጨምሮ የተለያዩ አማራጮችን ባለስልጣኑ እንደሚጠቀም አመልክተዋል።
ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ቆይታ ያደረጉ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በዘርፉ አስቀድሞ የተሰራበት ባለመሆኑ መመዘኛ መስፈርቶችን ማሟላት ለግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ፈታኝ በመሆኑ የባለድርሻዎች እገዛ እንደሚያስፈልጋቸው ተናግረዋል፡፡