ስመ ጥሩ እንግሊዛዊ ሳይንቲስት ስቴቨን ሃውኪንግ እ.አ.አ በ1995 ዓለም ከ30 ዓመታት በኋላ ምን ልትመስል ትችላለች የሚል ጥያቄ ቀርቦለት ነበር፡፡
የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት 2025 ዛሬ መግባቱን አስመልክቶ የፊዚክስ ሊቁን ትንበያዎች ከ30 ዓመት በኃላ በምልሰት እንቃኛቸዋለን፡፡
የቲዎሬቲካል ፊዚክስ ሊቁ በ30 ዓመታት ውስጥ የሚጠበቁ ግዙፍ ለውጦች ብሎ ካነሳቸው ጉዳዮች ውስጥ አንዱ በየዘርፉ የቴክኖሎጂው መፍላት ነው፡፡ ሃውኪንግ የበይነ መረብ ጥቃት፣ የኮምፒዩተር ቫይረስ እና የመረጃ ምንተፋዎች እንደሚስፋፉ የተናገራቸው ትንበያዎች ባለ ጥቁር ምላስ ሊያስብሉት ይችላሉ፡፡
ሌላኛው ኢንተርኔትን መሰረት ያደረገ የርቀት ህክምና አገልግሎት ትንበያው ሲሆን ሊቁ ስልጡን ሮቦት ሀኪሞችን የምናይበት ጊዜ ሩቅ አይደለም ብሎ ነበር፡፡ ይህ የሃውኪንግ ትንበያ ሙሉ በሙሉ ባይሳካም በተለያዩ የዓለም ሀገራት ጅማሮዎች ግን ተስተውለዋል፡፡
የሰው ልጅ ከህዋ ላይ ውድ ማዕድናትን ወደ ምድር ማጋዝ እንደሚጀምር በፊዚክስ ሊቁ የተሰጠው ትንበያ፤ ናሳን ጨምሮ የተለያዩ የጠፈር ምርምር ማዕከላት ከጨረቃ መጡ የተባሉ ድንጋዮችን በሙዚየም እስከማሳየት ቢደርሱም እስከ ማዕድን ቁፋሮ ስለመድረሳቸው ግን መረጃ ማግኘት አይቻልም፡፡
በህዋ ላይ ማዕድናት ያማውጣት ስራ ባይጀመርም፤ እድሉ ግን አሁንም እንዳለና በህዋ ላይ ያሉ ሰው ሰራሽ ቁሳቁሶች ለጠፈርተኞች እንቅስቃሴ እክል መሆናቸው ይገለጻል፡፡
ሳይንቲስቱ በትንበያው ከ30 ዓመታት በፊት ሊከሰት ይችላል በሚል ያቀረበው ሌላኛው ጉዳይ በሰዎች እጅ ቺፕ በማስገባት ገንዘብ ከባንክ መክፈያ ማሽን ማውጣት የሚቻልበት ቴክኖሎጂ በወደፊቱ የባንክ ዘርፍ ተግባራዊ ይሆናል የሚል ነበር፡፡
የሳይንቲስቱ ግምቶች እውን ሆነው ማይክሮቺፕ በሰውነት ውስጥ በመቅበር ባንኮች የባንክ አገልግሎት መስጠት፤ በጣት አሻራ እንዲሁም ስካን በማድረግ ደንበኞች ገንዘባቸውን ማንቀሳቀስ የሚችሉበት ዘመን እውን ሆኗል፡፡
ቢቢሲ በዓለም አቀፍ ፕሮግራሙ ሳይንቲስቱ ስቴቨን ሃውኪንግ ያስቀመጣቸው ትንበያዎች በርካቶቹ እውን መሆናቸውን ቢገልጽም፤ የትላልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እና የማህበራዊ ሚዲያ መስፋፋትን መዘንጋቱን አስታውሷል፡፡
በላሉ ኢታላ etv
TIPS
Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security