የክሬን እሮብ እለት የተጠናቀቀውን የነዳጅ ጋዝ የመተላለፊያ ውል ለማደስ ፈቃደኛ ባለመሆኑ በዩክሬን በኩል ወደ በርካታ የአውሮፓ ሀገራት የሚላከው የሩሲያ የተፈጥሮ ጋዝ ውል ሳይታደስ ተቋርጧል።
ዩክሬን ከሩሲያ ጋር በቀጠለው ወታደራዊ ግጭት ምክንያት ለአምስት ዓመታት ያህል የቆየውን የተፈጥሮ ጋዝ የመተላለፊያ ስምምነቱን እንደማታድስ አስጠንቅቃ ነበር።የሩሲያ የተፈጥሮ ጋዝ ማጓጓዝን አቁመናል፤ ይህ ታሪካዊ ክስተት ነው። ሩሲያ ገበያዋን እያጣች ነው፣ የገንዘብ ኪሳራ ይደርስባታል እንዲሁም አውሮጳውያን የሩሲያን የተፈጥሮ ጋዛ መጠቀምን ለመተው ወስነዋል ሲሉ የዩክሬን ኢነርጂ ሚኒስትር ጀርመን ጋሉሽቼንኮ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። የሩስያ ኢነርጂ ድርጅት ጋዝፕሮም ባወጣው መግለጫ ከቀኑ 8 ሰአት በሞስኮ አቆጣጠር መሰረት ወደ አውሮፓ የሚላከው ጋዝ የመተላለፊያ ስምምነቱ ያለፈበት በመሆኑ ተቋርጧል ብሏል።
በዩክሬን ወገን በኩል እነዚህን ስምምነቶች ለማደስ በተደጋጋሚ እና በግልጽ ቢጠየቅም በእምቢታ በመፅናቱ ጋዝፕሮም ከጃንዋሪ 1 ቀን 2025 ጀምሮ በዩክሬን ግዛት ውስጥ የተፈጥሮ ጋዝ ለማጓጓዝ ቴክኒካዊ እና ህጋዊ መብት ተነፍጓል ሲል ጋዝፕሮም ቴሌግራም መልእክት መተግበሪያ ላይ ያወጣው መግለጫ ያሳያል።ዩክሬን የሩስያን የተፈጥሮ ጋዝ በግዛቷ በኩል ወደ ስሎቫኪያ፣ ሞልዶቫ እና ሃንጋሪን ጨምሮ ወደ ተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት እንዲሰራጭ ስታደርግ ቆይታለች።የአውሮፓ ህብረት ለኪየቭ የሚያደርገውን ድጋፍ በመተቸት ላይ የሚገኙት የስሎቫኪያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሮበርት ፊኮ ባለፈው ሳምንት ወደ ሞስኮ ተጉዘው ከፑቲን ጋር በጋዝ ፍሰቱ መቆም ዙሪያ አስቀድመው መክረዋል።
አርብ እለት ፊኮ መንግስታቸው ዩክሬን የጋዝ ማጓጓዝ ሂደቱ እንዲቆም የምታደርግ ከሆነ ስሎቫኪያ ለዩክሬን የምታቀርበውን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦቶችን ማቆምን እና በመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ አጸፋዊ እርምጃዎችን እንደምታስብ ተናግረዋል። “የዩክሬን ፕሬዝዳንት የአንድ ወገን ውሳኔ መቀበል ሙሉ በሙሉ ምክንያታዊነት የጎደለው እና የተሳሳተ ነው” ሲሉ ፊኮ ብራሰልስ ለሚገኘው ህብረቱ በጻፈው ደብዳቤ ላይ ገልፃዋል። “በተወሳሰበ የኢኮኖሚ ጊዜ ውስጥ ትልቅ የፋይናንሺያል ተፅእኖን” የሚያስከትል መሆኑን በመቃወም ተፈፃሚ እንዳይሆን ተማጽነዋል።
የተፈጥሮ ጋዝ መቋረጡ ዩክሬንን በምታዋስናት ሞልዶቫ ውስጥ ከባድ ችግርን ይፈጥራል። ወደ አውሮፓ የሚወስደው የሩሲያ ጥንታዊ የጋዝ መስመር መዘጋቱ እ.ኤ.አ. በ 2014 ሩሲያ ክሬሚያን በመያዙ ምክንያት ለአስር አመታት የቆየውን ከባድ ውጥረት ይበልጥ ያባብሰዋል። እ.ኤ.አ. በ 2022 በዩክሬን ወታደራዊ ግጭት ከተቀሰቀሰ በኋላ አማራጭ ምንጮችን በመፈለግ የአውሮፓ ህብረት በሩሲያ ኃይል ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ ጥረቱን በእጥፍ ጨምሯል።ሩሲያ አሁንም በጥቁር ባህር በኩል ባለው የቱርክ ሰርጥ የተፈጥሮ ጋዝ ወደ ውጭ ሀገራት መላኳን ትቀጥላለች።
Vua Addis_Reporter
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring