” ድርድር ሳይሆን ውይይት ነው”!
እስክንድር ነጋ አወዛጋቢ ሰው መሆን ከጀመረ ወዲህ ስለእርሱ ምንም ነገር ብዬ አላውቅም::
እስክንድርን ማወደስም ሆነ ማውገዝ የማልፈልገው ሁለት አይነት ተቃራኒ ሰብዕና ያለው ሰው ሆኖ ስለሚያስቸግረኝ ነው::
አልሚም አጥፊም የሆነ የታቃረነ ሰብዕና!!!
እስክንድር በፅናቱ ! እስክንድር በታማኝነቱ! እስክንድር ለቆመለት ዓላማ ያለው ቁርጠኝነት ! እስክንድር በከፈለው ዋጋ! እስክንድር ባለው ትህትና ያለኝ አመለካከት አወንታዊ ነበር ለማለት እችላለሁ:: አሁን ባለው ሁኔታ ግን በእርሱ ላይ ያለኝ አመለካከት ሙሉ በሙሉ ተቀይሯል::
እስክንድር ባለደራስን መሰረትኩ ብሎ የህዝብ ገንዘብ ሰብስቦ ከሀላፊነት ሲሸሽ ግራ ገብቶኝ ነበር:: የአዲስአበባ ልጆችን ሰብስቦ ሁሉንም ነገር በመበተን ፓርቲውን ለቀቅኩ ሲልም ግርምታ ያልፈጠረበት ሰው የለም::
በኃላም ግንባር የሚል የዳቦ ስም አውጥቶ የፋኖን ትግል በቆረጣ ለመጥለፍ ሲሞክርና በሌለ ሰራዊት ድርጅት መሰረትኩ ሲልም ጤንነቱ አጠራጥሮኛል::
ግንባሩ በፋኖዎች ተቀባይነት ሲያጣ ደግሞ እርሱ ራሱ ባሰማራቸው የፖለቲካ ደላሎች ታጣቂዎችን በገንዘብ ሲገዛና ውሸት ሲጀምር እስክንድር ማንነቱ የተምታታበት ሰው መሆኑን ተረዳሁ::
የተወሰኑ ሚዲያዎችን የፕሮፖጋንዳ አፈቀላጤ በማድረግ ከዐማራ ሕዝባዊ ግምባር ወደ ህዝባዊ ሰራዊት ከዚያም ወደ ህዝባዊ ድርጅት እያለ ፍሬቻ ሳያሳይ ሲተጣጠፍና ህዝቡን ግራ ሲያጋባ ሰውየው ያልተገባ የታላቅነት ስም እንደተጎናፀፈ ገባኝ::
ይህን ሁሉ የተምታታ ነገር በመመልከት እስክንድር ነጋ መርህ የሚባል ነገር ያልፈጠረበት ሰው መሆኑን ለመረዳት ይቻላል::
በባልደራስም ሆነ በፋኖ ስም ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ለመሰብሰብ የተቻለው በእስክንድር ነጋ ስም መሆኑን ልብ ይሏል:: ይህም ሆኖ ግን እርሱም ሆነ አጫፋሪዎቹ ገንዘቡ የት እንደገባ መግለጫ ለመስጠት አይፈልጉም ነበር::
እነዚህን ሁኔታዎች በማጤን እስክንድር ታማኝ ነው የሚለው ሀሳብ ትክክል እንዳለሆነ ተገንዝቤያለሁ::
በእነዚህ አሉታዊ ጉዳዮች ሳቢያ ህዝቡ በእስክንድር ላይ አመኔታ እንዳይኖረው አድርጎታል ብየ አምናለሁ::
እስክንድር ዛሬ የሰጠው ቃለምልልስ ደግሞ ግራ ያጋባል::
ድርድር ሳይሆን ውይይት በሚል የተምታታውን መግለጫ ያስተጋቡት እስክንድርና ብሩክ ይባስ ህዝብን ሲያደናግሩ ተደምጠዋል:: ብሩኬ እንኳ ድሮም የተምታታበት ጋዜጠኛ እንደሆነ አውቃለሁ::
ከሁሉም በላይ የገረመኝ ግን የእስክንድር ውሸት ነው::
ሕዝባዊ ድርጅት የሚባለው የእነስክንድር ምናባዊ ጦር በጣም ጠንካራና የተሻለ ሀይል በመሆኑ እንዲሁም አንድነት በመፍጠሩ በዓለምአቀፉ ማህበረስብ ዘንድ ተቀባይነት አግኝቷል ማለቱ “ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት ” በመሆኑ ፈገግ አሰኝቶኛል::
” ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ” የሚለውን ብሂልም አስታውሶኛል:: The fact is on the ground.
ስማቸው ሃሜት fb.