የሻዕቢያን የማይቀየር ማንነት ቁልጭ አድርጎ በታሪክና ትንቢት ለትውልድ ያስቀመጠው ኦሮማይ የተሰኘው የጋዜጠኛና ደራሲ በዓሉ ግርማ መጽሃፍ በተደጋጋሚ እንዲተረክና በተለያዩ የአገር ውስጥና የዓለም ታላላቅ ቋንቋዎች ሊተረጎም እንደሚገባ ተጠየቀ። “ኦሮሚያን አንብቦ ወይም አድምጦ የተረዱ ሁሉ መጨረሻ ላይ የሚደርሱበት ድምዳሜ ሻዕቢያ መጥፋት አለበት የሚል ብቻ ነው” ሲሉም ጥቆማውን ጥያቄውን ያቀረቡት አመልክተዋል።
ጥያቄውን ያነሱት ኦሮማይ በእንግሊዝኛ መተርጎሙን በዜና የሰሙ ወገኖች ናቸው። በዓሉ ግርማ በረቂቅ ብዕሩ ሻዕቢያ ከየት ተነስቶ የት እንደደረሰ፣ በእባብ የሚመሰሉ መርዘኞች ስብስብ እንደሆነ፣ ይህ ዕባባዊ ባህሪው እንደማይለቀው፣ ኢትዮጵያዊያን በየዋህነት የሚያደርጉትን በመርዘኛ ተግባራቸው እየገለበጡ ለጥቃት የሚጠቀሙ፣ ኢትዮጵያን የማፍረስ ሴራቸውና ውጥናቸው ሳያሳካ እንደማይተኙ ያስረዳበት መጽሃፍ እንደሆነ ያስረዳሉ።

“አሁን ላይ ሻዕቢያን አስመልክቶ የተወሰኑ መንሸዋረሮች ያሉት ኦሮማይን በቅጡ ካለመረዳት የተነሳ ነው። ሻዕቢያ መፍትሄ እንዳለው አድርገው እየሰሩና እግሩ ስር የሚንከባለሉት ኦሮሚይን በቅጡ ባለማንበባቸው ወይም ባለመረዳታቸው ሳቢያ ነው። ይህ ምንም ዓይነት ጥናት አያስፈልግም” በማለት ትውልድ ሁሉ የሻዕቢያን ማንነት፣ ኢትዮጵያ ላይ ያለውን አቋም፣ እንዴት በሴራ የተካነና የዋህነትን በክፋት መርዝ ለውሶ የሚናደፍ፣ እስከመቼውም ሊቀየር የማይችል የእፉኚቶች ስብሰብ መሆኑን እንዲያውቅ በተለያዩ ቋንቋዎች በተደጋጋሚ ሊተርክ እንደሚገባው ይገልጻሉ።
ጥያቄውን ካነሱት መካከል አንዱ የሆኑት የማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያው አቶ ይርጋለም አሰፋ ” ሻዕቢያ መርዙን ምላሱ ስር ደብቆ በጠራራ ጸሐይ እንደሚንከላውስ ተናዳፊ እባብ ዓይነት ነው” ይላሉ። ለዚህም ማስረጃው ሻዕቢያን እንደ ፊልም ቁልጭ አድርጎ የሳለው ኦሮማይ መሆኑን አመልክተው ተደጋጋሞ ሊተርከና ትውልድ ሻዕቢያን በወጉ እንዲረዳው መደረግ እንዳለበት ያምናሉ። ይህ ቢሆን “ሻዕቢያ እግር ስር የሚንደባለሉት ትውልዱን አያሳስቱትም። እነሱም የዚያን ያህል ድፍረት አይኖራቸውም”
ስለሺ አበበ የተባሉት ሌላው አስተያየት ሰጪ የሻዕቢያን ሴራና ዕባብነት ለመረዳት ሻዕቢያን “ክጃለሁ” ብሎ አዲስ አበባ የገባውንና በመጽሃፉ የተገለጸውን “ስዕላይ በራኺ” ማየት በቂ ነው። የስዕላይ ባህሪ ያነበበ የሻዕቢያ ሰዎችን መሰሪነት፣ በምንም መልኩ ሊታመኑ እንደማይችሉ፣ ይህ ባህሪያቸው ከቶውንም እንደማይቀየር ማሳያም እንደሆነ ይገልጻሉ። አሁን ሻዕቢያ ዙሪያ የተኮለኮሉት ሁሉ ይህን ቢረዱ የኢትዮጵያ መከራ የሚያበቃበትን ጊዜ እንደሚያሳጥረው ይናገራሉ።
ጋዜጠኛና ደራሲ በዓሉ ግርማ በ1975 ዓ.ም ለኅትመት የበቃው ኦሮማይ መጽሃፍ ይህ ትውልድ ሻዕቢያን እንደፊልም በግላጭ እንዲያየው ከማድረግም በላይ ብሄራው ቁጭትን እንደሚያነሳሳ ጥያቄውን ያቀረቡት ወገኖች ይገልጻሉ። እነዚህ ወገኖች እንደሚሉት ኦሮማይን ለታሪካ ለትውልድ በተለያዩ ቋንቋዎች ማሳተም ብቻ ሳይሆን በፊልምና በዘጋቢ መልክም ሊሰራ እንደሚገባ ይጠቁማሉ። ከዛም አልፎ በቤተ መዘክር አንድ ተራኪ ምስል ተበጅቶለት ትውልድ ሁሉ ሊማርበት እንደሚገባ ምክር ይሰጣሉ። “ኢትዮጵያዊ ነን የሚሉ የጥበብ ሰዎችም ታሪካዊ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባ ነበር። ስራቸው ነው። ይመለከታቸዋል” ሲሉ ወቀሳና ጥቆማ ያቀርባሉ።
ሲያስረዱም ” የኢትዮጵያ ዕዳ የሆነው ሻዕቢያ በሁሉም ኢትዮጵያ ከተሞች ውስጥ በነበረው በቤተሰብ አደረጃጀት ልጆቻቸውን ከዕባብነቱ በሚመነጨው መርዘኛ የሃሰት ትርክት መንደፉን ይጠቅሳሉ። ስለዚህም ሻዕቢያ ለነደፋቸው ከተቀበሉት ማስተካከያ፣ ለኢትዮጵያዊያን ግን ሻዕቢያ በትክክልም መርዘኛ እባብ መሆኑ በማሳየት እሱ ካልጠፋ ሰላም ሊገኝ እንደማይቻል አቋም የሚይዙበት ይሆናቸዋል” ብለዋል።
ሃሳቡን ያነሱት ክፍሎች “የበዓሉ ግርማ ታላቅ ድርሰት የሆነው ኦሮማይ ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ መተርጎሙ ተሰማ” በሚል ፋና የዘገበውን ዜና ተመልክተው አድንቀዋል። ቢዘገይም ይህን ላደረጉ ምስጋና እንደሚገባቸው ገልጸዋል። ዓለምም ሆነ አፍሪካዊያን ሻዕቢያን ጠንቅቀው እንዲያውቁት እንደሚረዳቸው ገልሰዋል። ይሁን እንጂ በቂ እንዳልሆነ አመልክተዋል።
በተለይ በአረብኛ ባስቸኳይ ተተርጉሞ ሊሰራጭ እንደሚገባ አሳስበዋል። አረብ አገራት ሻዕቢያ ታማኝ ወዳጅ ሊሆን እንደማይችልና በዚሁ ባህሪው ተገልሎ ” በኤርትራ ሰዓት ቆሟል” እስኪባል የተገለለ፣ አምራች ዜጎች በቅርቡ የሚነጥፉባት አገር የተሸከመ የሽፍታ ስብሰብ መሆኑ ለመረዳት እንደሚያግዛቸው አመልክተዋል። ቢቻል በፈርንሳይኛ፣ በጀርመንኛና በቻይንኛ ቢተረጎም ጥቅሙ የጎላ መሆኑ አስረድተዋል።
ሻዕቢያ እንዲፈጠር ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ በውክልናና በተላላኪነት ኢትዮጵያ ላይ የሚዘምቱ ታጣቂዎችን ሲያሰለጥን፣ ሲያደራጅና፣ ሲያዘምት መኖሩ ይታወሳል። አሁንም ይህንኑ ተግባሩ እንደገፋበትና መረጃዎች እየወጡበት ነው። ከለውጡ በሁዋላ የተፈጠረውን ሰላም ተንተርሶ አማራ ክልል ውስጥ ሴል መስርቶ ቀውስ ማስነሳቱንም በመረጅ አስደግፈው እያጋለጡት ነው። ይህ ሳያስቆጫቸው አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሰሞኑን የኢትዮጵያ መንግስት የሻዕቢያ ተቃዋሚዎችን እያሰለጠነ ነው ሲሉ ከመሳይ ጋር በመሂን እየተቀባበሉ ክስ አሰምተዋል። አስተየቱን የሰጡት እነዚህን ወገኖች “ሻዕቢያ እግር ስር የሚንደባለሉ”ሲሉ ከሚገልጿቸው መካከል ናቸው።
በርካታ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በውጭ አገር ስለሚኖሩ፣ ሻዕቢያን እንዲያውቁት ይህ ሊደረግ እንደሚገባው አጥብቀው ያሳሰቡት እነዚሁ ክፍሎች፣ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ይህን መሰሉን ስራ ህግና ደንብ አክብሮ ቢሰራ እንደሚበጀው አመልክተዋል። ህብዝ በተለይም ወጣቱ ትውልድ ስለ ሻዕቢያ በቂ መረጃ ቢያገኝ በዚህ ደረጃ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ነፍጥ አንጋች እየፈለፈለ ችግር ሊፈጥር እንደማይችል አክለው ያስረዳሉ።
የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት በቀናነት በሚፈጽሙት ነገር ሁሉ ግብረ መልሱ በተለያየ መልኩ ጥቃት እንደሆነ በደፈናው ያስረዱት ወገኖች፣ ይህ ትውልድ እንደቀደመው የሚታለል እንዳልሆነ ማሳየትና በብሄራዊ ቁጭት ነቅቶ አገሩን እንዲታደግ ኦሮማይ በተደጋጋሚ በብዛት ህዝብ በሚያዳምጣቸው መገናኛዎች ትክክለኛው ሰዓት ተመርጦ ሊተረክ ይገባል። የብሄራዊ ጥቅም ጉዳይ የታጨቀበት በመሆኑ መጽሃፉ በትምህርት ቤቶች የክርክር መድረክ፣ በተለያዩ የውይይት አውዶች ላይ መጋገሪያ እንዲሆን አገር ወዳድ የሆኑ ሁሉ ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባም ጠይቀዋል።
ፋና እንዳለው ኦሮማይ ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ የተረጎሙት ዴቪድ ደ ጉስታ እና መስፍን ፈለቀ ይርጉ ናቸቅ። በ1970ዎቹ የታተመውው ኦሮማይ በስነ-ፅሁፍ ስልቱና በይዘቱ የተዋጣለት ድርሰት መሆኑን በርካታ ደራሲያንና ሃያሲያን መስክረውለታል። በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተተረጎመው ኦሮማይ 400 ገፅ ያለው ሲሆን በእንግሊዝ ሀገር መታተሙን ይፋ ያደረገው ጋርዲያን ነው።
የተረጎመውን መጽሃፍ መነሻ በማድረግ ሻዕቢያን የሚዲያ አጀንዳ በማድረግ ረገድ ኢትዮጵያዊያን ምሁራን ብዕራቸውን ሊያነሱ እንደሚገባም መክረዋል። በራሳቸው ጥምረት ውስጥ የበኩላቸውን እንደሚያደርጉም አመልክተዋል። በእነሱ መረዳት ሻዕቢያ እስካለ ኢትዮጵያ ሰላም አታገኝም። ኦሮማይን አንብበው የተረዱ ሁሉ ድምዳሜያቸው ተመሳሳይ እንደሆነም አመልክተዋል።
በቴሌግራም ይከተሉን https://t.me/+f_kxmaPjD-9jYTdk