እሳተ ጎሞራ ከመሬት ገጽታ በታች ያለ የማግማ (በከፍተኛ ሙቀት የቀለጠ አለት፣ ጠጣር ነገር )ክምችት ፈንድቶ ወደ ውጭ በተራራ ወይም በላይኛው የመሬት ክፍል ላይ የቀለጠ አለት ( ላቫ) ሆኖ ሲፈስ የሚፈጠር ነው። እሳተ ጎሞራዎች ለመፈንዳት ከባድ እፈና (ጫና) እና ማግማ አንድ ላይ ሲልሆን የሚከሰት ነው። እፈናው ጫናው ሲበረታ ተራራው ወይም ወደ የመሬት የላይኛው ክፍል እንዲፈነዳ ይገደዳል። ከሚፈሰው ቅልጥ ነገር ውስጥ ለማዳበሪያ ቁልፍ ንጥረ ነገር የሆነው ድኝ አንዱ ነው። ይህ ከዊክፒዲያ የተሰሰደና ማሻሻያ የተደረገበት ነው። ስባለሙያውም እንዳሉት ይህ ክስተት እስካሁን አልሆነም ።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስ ሕዋ ሣይንስ እና አስትሮኖሚ ተቋም የሴስሞሎጂ ትምህርት ክፍል ኃላፊ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ ሣይንስ መምህርና ተመራማሪ አታላይ አየለ (ፕ/ር) የመሬት መንቀጥቀጡ ጊዜ ቆጥሮ መናገር ባይቻልም እንደሚቆም አመለከቱ። ባለሙያው ይህን ያሉት ዛሬ እሳተጎሞራ መፈንዳቱን የሚያሳይ መረጃዎች መሰራጨታቸውን ተከትሎ ነው።

ምስል / ትክክለኛ የሳተ ጎሞራ የሚያሳይ Erta Ale | Danakil Depression
ዛሬ በአፋር ክልል፣ በዱለቻ ወረዳ በዶፋን ተራራ ላይ የተከሰተው ጭስ እና እንፋሎት የሚመስል ነገር እሳተ ገሞራ ሳይሆን በሙቀት አካባቢ ያለው የእንፋሎት ውኃ በኃይል እየተወረወረ በመውጣቱ የተፈጠረ ክስተት እንደሆነ ባለሙያው አመልክተዋል። አንዳንድ ወገኖች መተነፈሱ ፋታ የሚሰጥ፣ በበጎ ጎኑ የሚታይ እንደሆነ እየገለጹ ነው።
የመሬት መንቀጥቀጥ ከሚፈጠርባቸው ምክንያቶች አንዱ በመሬት ውስጥ ያለው ቅልጥ አለት መውጫያ ሲያጣ እንቅስቃሴው በመሬት ውስጣዊ አካል ውስጥ በሚፈጠር እንቅስቃሴ ስለሆነ መተነፈሱ አድሮ የሚተፋው ቅልጥ አለት ሆኖ መጠኑ ከበዛ የራሱ አደጋ ሊያስከትል ቢችልም መተንፈሱ ጥሩ እንደሆነ ግንዛቤያቸውን በማህበራዊ ሚዲያ ያጋሩ አሉ።
ኢቲቪ ያናገራቸው ባለሙያ በተፈጠረው ሁኔታ እሳት እንዳልታየ ገልጸዋል። ይሁን እንጂ ወደፊት ቅልጥ ዓለት ሊረጭ እንደሚችል አመላካች ሊሆን እንደሚችል ጥቆማ ሰጥትተዋል።
ከመስከረም ወር ጀምሮ በአዋሽ ፈንታሌ አካባቢ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ንዝረቱ እየተሰማ ነው። ህዝብም ጭነቀት ውስጥ ገብቷል።
ከሰሞኑን በሬክተር ስኬል ከፍ ያሉ የመሬት መንቀጥቀጦች በፈንታሌ እና ዶፈን አካባቢ ተከስተዋል። ይህን ተከትሎ ከፍተኛ ባይሆንም በንብረት ላይ ጊዳት ደርሷል። በጎዳናዎች ላይ መሰነጣጠቅ ታይቷል።
የመሬት መንቀጠቀጡ በተደጋጋሚ መከሰቱ በአካባቢው እንዲሁም ንዝረቱ በሚሰማባቸው አካባቢዎች ጫና እየፈጠረ ነው። በተለይም በአካባቢው በነበሩ በባህላዊ መንገድ የተሠሩ ቤቶች፣ ለወትሮውም እንኳን የመሬት መንቀጥቀጥ ነፋስ መቋቋም ስለማይችሉ ጉዳት አጋጥሟቸዋል።
በተደጋጋሚ እየደረሰ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች እየተሰማ ነው። በተለይም እንደ አዲስ አበባ ባሉ ትላልቅ ህንጻዎች በሚገኙባቸው አካባቢዎ፣ አደጋ ከደረሰ ጥፋቱ የከፋ ስለሆነ ዜጎች አስቀድመው ሊወስዱ ስለሚጋባቸው ጥንቃቄ ተደጋጋሞ በባላሙያዎች እየተጠቆመ ነው።
- ቁምሳጥን ላይ የሚቀመጡ ውድ እና ተሰባሪ እንዲሁም ተቀጣጣይ የሆኑ ዕቃዎችን መሬት ላይ ማስቀመጥ፣
- ቅጽበቱ እስኪያልፍ ማዕዘን አካባቢ መቆም፣
- ጠረጴዛ ስር እና ጭንቅላትን መከላከል በሚያስችል ቦታ መከለል መደረግ ካለባቸው ቅድመ ጥንቃቄዎች መካከል የሚጠቀሱና ሁሉም ሊያውቃቸው የሚገባው ናቸው።
የመሬት መንቀጥቀጥን መተንበይ አይቻልም ያደጉ ሀገራት የጥፋት መጠኑን ሕዝባቸውን በማስተማር እንዲሁም በሕንፃ አሠራር ቴክኖሎጂ መቀነስ ችለዋል። አሁን ላይ እየተከሰተ ያለው ተደጋጋሚ የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ማብቃቱ አይቀርም፤ ነገር ግን መች እንደሚያበቃ ማወቅ አይቻልም ። ” ሲሉ ባለሙያው ለኤኤምኤን ገልጸዋል።
የመሬት መንቀጥቀጥን መከላከልና ማስቆም የሚቻል የሚመስላቸው የክልሉን መንግስትና ፌደራልን እየወቀሱ ነው። ቤተመንግስት ከመታደሱም ጋር በማያያዝ ፖለቲካም እየሆነ ነው።
በተለያዩ የማህበራዊ ገጾች ሰዎች ቤታቸውን ጥለው ሜዳ ላይ መተኛታቸውን፣ በአንዳንድ ቦታዎች ቁጥራቸው ጥቂት የሆነ በአንድና በሁለት ባጃጃ አቅራቢያቸው ወዳለ ሌላ ቀበሌ የሚጓጓዙ ሰዎችን የሚያሳይ ምስልም እየታየ ነው።
በባህላዊ መንገድ የተቀለሱ ጎጆዎችና አውላላ ሜዳ ወይም በረንዳ ስር ፈልጎ መተኛት አደጋ ቢደርስ ጉዳትን ከመቀነስ አኳያ ይህ ዜና የሚያሰራጩ ያብራሩት ነገር የለም። ይሁን ነጂ ” መንግስት ዳተኛ ነው። ለህዝቡ አልደረሰም” የሚል የንፅጽር ወቀሳ እያሰራጩ ነው።
የመሬት መንቀጥቀጥን በተከሰተ ቁጥር ቀድሞ በመዘገብ ” ሼር አድርጉ” ወዘተ እያሉ የላይክና ሰብስክራይብ መገበያያ ያደረጉትም አሉ። ሰፊ የማህበራዊ ተከታታይ ያላቸው ወገኖች ህዝብን ኃላፊነት ወስደው ለማስተማር ባለያዎችን፣ ተመሳሳይ ችግር ያጋጠማቸውን አገራት ተሞክሮ ጊዜ በመውሰድ ለማቅርብ ሲተጉ አይታይም።
በቂና ጥልቅ ነው ባይባልም፣ የመንግስት ሚዲያዎች የሚጽፉትን ቆራርጦ ከማሰራጨት በዘለለ የተሰራና የሚጠቀስ ማስተማሪያ ሲቀርብ አልታየም። ቲክቫክ ኢትዮጵያ በዚህ በኩል የተሻለ ሆኖ መታየቱን በርካቶች ይመስክሩለታል።
እንደተለመደው ዛሬም በሬክተር ስኬል ሲሰፈር 5.2 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ተመዝግቧል። ይህ ተደጋጋሚ ክስተት ትላንት ለሊትም ጉብኝት አድርጓል። የተመዘገበውም በሬክተር ስኬል 5.0 ነው። በጥቅሉ ተደጋጋሚ የተለያየ መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ በተለያዩ ቦታዎች ተስተውሏል። ይህ እየቆየ በውስን ቦታዎች መሬትን የሚንጠው አደገኛ ክስተት ከልምድ እንደታየው ጉዳቱ እጅግ ዘግናኝ፣ አደጋው ጥልቅ፣ ሃዘኑ ከዳር እስከዳር የሚያናጋና በቀላሉ የማይለቅ፣ አንዳንዴም ባለሙያው እንዳሉት የት ተጀምሮ የት እንደሚያበቃ ለመተንበይ ስለሚያስቸግር ፊትን ወደ አምላክ መመለስ እንደሚሻልም የሚመክሩ አሉ።
ዓለም ላይ በአስከፉነቱ የሚታወቀው የመሬት መንቀጥቀጥ እንደ ትልቅ ዜና “ሰበር” እየተባለ የማህበራዊ ሚዲያ ማድመቁ “ምን ይሆን የሚያስደነግጠን?” የሚል ጥያቀኤም እያስነሳ ነው። ከሁሉም በላይ የኃይማኖት አባቶች የአዋጅ ጸሎት ማስታወቅ ሲገባቸው ድባቴ ውስጥ መግባታቸው ያስገረማቸው ጥቂት አይደሉም። ትላንት ለሊቱን ከደረሰው መንቀጥቀጥ በተጨማሪ በተደጋጋሚ በሬክተር ስኬል 4.7, 4.5, 4.7 , 4.5 , 4.5, 5.2 የተመዘገቡ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአሜሪካ ጆኦሎጂካል ሰርቬይ መረጃ አመልክቷል።
5.2 ሆኖ የተመዘገበው ከፍተኛው መሆኑ ተመልክቷል። ይኸው ክስተት አዲስ አበባን ጨምሮ የተለያዩ አካባቢዎችን እየናጠ ነው።
ዘገባው ከተለያዩ ሚዲያዎችና ማህበራዊ ገጾች የተወሰደ ነው።