ካናዳ ነገሮችን እንደየ አመጣጣቸው ማስተናገድ ትችላለች ጉልበተኛንም ፈርታ የምትሸሽ ሳይሆ የምትቋቋም ናት ሲሉ ካርኒ ተናገሩ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በካናዳ ላይ የ25 በመቶ ቀረጥ መጣላቸውን ተከትሎ ቀጣዩ የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን ግንባር ቀደም ተወዳዳሪ የሆኑት ማርክ ካርኒ ሀገራቸው ‘ጉልበተኛን ፈርቶ የሚያቀረቅር ሳይሆን የሚጋፈጥ ” ነው ብለዋል።
የ59 ዓመቱ ተፎካካሪ ካርኒ በጥር ወር ለካናዳ ገዥ ሊበራል ፓርቲ መሪ እጩ መሆናቸውን ያሳወቁ ሲሆን በቀድሞ ስራቸው የካናዳና የእንግሊዝ ባንክ ገዥ ነበሩ።
በአሁኑ ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶን ለመተካት ከሚወዳደሩት አምስት እጩዎች አንዱና እስካሁን ድረስ በሊበራል የፓርላማ አባላት መካከል ትልቁን የድጋፍ ድምፅም አግኝቷል ።
ለመሪነትም የሚደረገው ውድድር መጋቢት 9 ይጠናቀቃልም ተብሏል ።
በፉክክሩ የሸነፈው አካል በፍቃደኝነት የለቀቀውን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ቱሩዶን ስፍራ ወክሎ ጠቅላይ ሚስትርም የፓርቲ መሪም እንደ ሚሆን ተዘግቧል።
ስለ ታሪፉ የተጠየቁት ካርኒ “ፕሬዝዳንት ትራምፕ ምናልባት ካናዳን እጠቀልላለሁ ብለው ያስባሉ።እኛ ግን ጉልበተኛን እንቃወማለን፣እንጋፈጣለን እንጂ ወደ ኋላ አናፈገፍግም ።አንድ ሆነን አፀፋውን እንመልሳለን “ብለዋል ።
የቀድሞው የእንግሊዝ ባንክ ገዥ በበኩላቸው የታሪፉ ጭማሬው ‘በዓለም ዙሪያ የአሜሪካን ስም ያጠለሻል” ሲሉ ሃሳባቸውን ሰንዝረዋል።
“እንዲህ አይነቱ ውሳኔ የዋጋ ግሽበትን ያስከትላል ፣የእድገት እንቅፋት ይሆናል ፣ የወለድ ምጣኔን ከፍ እንዲል ያደርጋል ዋሽንግተንም ይህንኑ ነው እያደረገችው ያለው “ብሏል።
አክለውም አሜሪካ ከቅርብ የንግድ አጋሯ ጋር እና የንግድ ስምምነቶችን ከፈፀመቻቸው ሀገራት ጋር ይህን መሰል ተግባር ስትከውን ከአሥር ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ይሄ “ለሁለተኛው ጊዜ ነው” ብሏል።
የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች አዲሲ የተጣለው ታሪፍ በካናዳ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል እና ለአሜሪካውያን ከፍተኛ ዋጋ እንደሚያስገኝ ጠቁመዋል።
ታሪፍ የትራምፕ የኢኮኖሚ ራዕይ ዋና አካል ነውም ብለዋል።የአሜሪካን ኢኮኖሚ ለማሳደግ እና የታክስ ገቢን ለማሳደግ እንደ አማራጭ ይወስዱታል ሲሉ ጠቁመዋል ።
ተሰናባቹ ትሩዶ፤ የካናዳ ምላሽ ለተጣለው አዲሱ ታሪፍ ‘ጠንካራ’ እና ‘አፋጣኝ’ ይሆናል ብለዋል ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው።
ልኡል ወልዴ
ጥር 24 ቀን 2017 ዓ.ም
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring